Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30654
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አደባባይ ሚዲያ በጉራጌ ክልል ጥያቄ ላይ ድንቅ የ2 ሰዓት ፕሮግራም! መሰማት ያለበት!

Post by Horus » 10 Aug 2022, 14:25

ጉራጌ ያማኞች ምድር! ጉራጌ የምድረ ከብድ፣ የምሁር ኢየሱስ፣ የገድራ ቆጠር አገር !

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: አደባባይ ሚዲያ በጉራጌ ክልል ጥያቄ ላይ ድንቅ የ2 ሰዓት ፕሮግራም! መሰማት ያለበት!

Post by Za-Ilmaknun » 10 Aug 2022, 16:26

የ ኦህዴድ መኳንንት ህገመንግስቱን አትንኩብኝ እያሉ ፥ ህገመንግስታዊ ጥያቄዎችን ለማፈን መንጠራወስ ትርፉ ፥ ግጭትና እልቂት ነው።

የህገመንግስቱን ህጸጽ በአፈጻጸም ለማረም መሞከር አደጋ ይጋብዛል።

ጉራጌ ክልል ቢሆን ድንቅ ክልል ይገነባል። ብዙ ኢንደስትሪ ገንብቶ ለመላው ኢትዮጵያ ምርቶችን ያቀርባል፥ ምናልባትም ፥ ባጭር ጊዜ ታላቅ ለውጥ ይሚታይበት አካባቢ ሊፈጠር ይችላል፥ ተረኛው ጣልቃ ገብቶ ካላደናቀፈው።

ወላይታም ይሁን ሌላው ክልል ለመሆን ከፈለገ መሆን መብቱ ነው። የጎሳ ክልል አደረጃጀት ያውም በአሉታዊ እይታ የተቃኘ፥ ለሃገር ብተና ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ይችል ይሆናል። ያም ቢሆን የችግሩን ምንጭ እስካልደረቀ ድረስ ችግሩን ማዘግየት እንጂ ማስቀረት አይቻልም።

To bounce back up , one has to touch the bottom. We are going down faster and it won't be too long before we hit the bottom as a society.

Horus
Senior Member+
Posts: 30654
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አደባባይ ሚዲያ በጉራጌ ክልል ጥያቄ ላይ ድንቅ የ2 ሰዓት ፕሮግራም! መሰማት ያለበት!

Post by Horus » 10 Aug 2022, 17:05

Za-Ilmaknun wrote:
10 Aug 2022, 16:26
የ ኦህዴድ መኳንንት ህገመንግስቱን አትንኩብኝ እያሉ ፥ ህገመንግስታዊ ጥያቄዎችን ለማፈን መንጠራወስ ትርፉ ፥ ግጭትና እልቂት ነው።

የህገመንግስቱን ህጸጽ በአፈጻጸም ለማረም መሞከር አደጋ ይጋብዛል።

ጉራጌ ክልል ቢሆን ድንቅ ክልል ይገነባል። ብዙ ኢንደስትሪ ገንብቶ ለመላው ኢትዮጵያ ምርቶችን ያቀርባል፥ ምናልባትም ፥ ባጭር ጊዜ ታላቅ ለውጥ ይሚታይበት አካባቢ ሊፈጠር ይችላል፥ ተረኛው ጣልቃ ገብቶ ካላደናቀፈው።

ወላይታም ይሁን ሌላው ክልል ለመሆን ከፈለገ መሆን መብቱ ነው። የጎሳ ክልል አደረጃጀት ያውም በአሉታዊ እይታ የተቃኘ፥ ለሃገር ብተና ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር ይችል ይሆናል። ያም ቢሆን የችግሩን ምንጭ እስካልደረቀ ድረስ ችግሩን ማዘግየት እንጂ ማስቀረት አይቻልም።

To bounce back up , one has to touch the bottom. We are going down faster and it won't be too long before we hit the bottom as a society.
የክልል ጥያቄን ከስረ መሰረቱ የሚነዳው ፍላጎት የመሬት ጥያቄ ነው ። የማንነት፣ ባህል፣ እና የፌደራል ባጀት ጉዳዮች በተበላሸው የመሬት ስሪት ላይ ተጨማልቀው ነው ይህን ሁሉ ቀውስ ያመጡት ወያኔዎች ። መሬት ላይ ለሚኖረው ሕዝብ ትልቁ ትግል መሬት መቀማማትና የድምበር ግፊያ ነው።

ለፓርቲ ካድሬዎች እና የጎሳ ከበርቴዎች የባጀት ቁጥጥርና የመሬት ቁጥጥር ነው ገፊ ሞቲቫቸው ። መሬትን በመንግስት ስም ይዘው ያን መሬት በመቸብቸና በማከራየት ሳይሰሩ መክበሪያ መሳሪያ ነው ።

ለምሁራና እና አባቶች በዚያ መሬት ስለተሰበሰቡት ሰዎች ቋንቋ፣ ማንነትና ባህል ህልውና ነው።

ለሰራተኛው ነጋዴው ሰርቶ ከባሪው ብሄራዊ ከበርቴ የንብረቱ ዋስትና መሰረት ነው ። ጂማ፣ አዋሳ፣ ሻሸመኔ ፎቅ የሰሩ ጉራጌዎች ባንድ ለሊት ነው ሙሉ ህይወት የለፉበትን የተነጠቁት ።

እነዚህ ፍላጎቶች ሁሉ ዘመናዊ ፍትሃዊ መልስ የሚያገኙት ኢጎሳዊና የዜጋ ሴራ ሲፈጠር ነው ። አቢይ ያን ሴራ መቀበልም መምራትም አልቻለም ። ኢትዮጵያ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነች ፣ እስከዚያ ጉራጌ እንደ ሰርዓቱ የራሱን ቁራሽ መሬት መጠየቅ የግድ ይለዋል።

አንተ እንዳልከው አዲስ ጨዋታ እስከ ሚመጣ አሮጌውን መጫወት ግድ ስለሆነ።

Post Reply