Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must See: በ ፲፱፻፲፩ በመላው ዓለም ለተከሰተው የህዳር በሽታ (ስፓኒሽ ፍሉ) ኢትዮጵያ ውስጥ ምን ዓይነት ሕክምና ይሰጥ ነበር ?

Post by Thomas H » 10 Aug 2022, 08:58

ከ 103 ዓመት በፊት በመላው ዓለም የተከሰተውን የህዳር በሽታ (ስፓኒሽ ፍሉ) ወረርሺኝ ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ያወጣው ማስታወቂያ !!!
፩.
ለዚህ ለዛሬ በሽታ ነጩን የባሕር ዛፍ ቅጠሉን እየቀቀላችሁ ማታ ስትተኙ በላቦቱ ታጠኑ፡፡ ደግሞ የባሕሩን ዛፍ ቅጠል እርጥቡን በብዙ አድርጋችሁ በቤታችሁም ውስጥ በየደጃችሁም እያነደዳችሁ አጭሱበት።
፪.
አይነ ምድራችሁን ሳትቆፍሩ አትቀመጡ አይነ ምድር ተቀምጣችሁ ስትነሡ ባይነ ምድራችሁ ላይ የባሕር ዛፍ ቅጠል ጣሉበት ያልጣላችሁበት እንደሆነ ከአይነ ምድራችሁ ላይ እንደ ገና በሽታ ይነሣል።
፫.
ባትታመሙም ብትታመሙም ውሀ እያፈላችሁ በውስጡ ጨውእየጨመራችሁ ጠዋትና ማታ አፉችሁን ተጉመጥመጡ ፣
፬.
ውሻ ድመት በቅሎና ፈረስ ሌላም ይህን የመሰለ ሁሉ በሞተባችሁ ጊዜ ሽታው በሽታ ያመጣልና ቅበሩት።
፭.
ሰው የሞተችሁ እንደሆነ መቃብሩን በጣም አዝልቃችሁ ሳትቆፍሩ አትቅበሩ በጣም ሳትቆፍሩ የቀበራችሁ እንደሆነ አውሬና ውሻ እያወጣ ይበላዋል ሽታውም ከዛሬው የበለጠ በሽታ ያመጣብናል።
፮.
በቤቱ ሰው የታመመበት ሰው ወደ ማዘጋጃ ቤት ድረስ እየመጣ አለዋጋ መድኃኒቱን ይውሰድ በማናቸውም ምክንያት የሚያድን እግዚአብሔር' ነው። ነገር ግን የሚያድን እግዚአብሔር ነው ብሎ መድኃኒት አላደርግም ማለት እግዚአብሔርን መፈታተን ይሆናልና መድኃኒት አናደርግም አትበሉ መድኃኒትንም የፈጠረልን እግዚኣብሔር' ነው፡፡
፯.
ደግሞ ከመቃብር ላይ በሽታ እንዳይነሣ ብሎ መንግሥታችን በቸርነቱ ብዙ ኖራ በየቤተክርስቲያኑ አስመጥቶልናልና በመቃብሩ ውስጥ ሬሳውን አግብታችሁ በላዩ ጥቂት አፈር ጨምራችሁ በአፈሩ ላይ ኖራውን አልብሱና ከዚያ በኋላ አፈር መልሱበት ኖራው የሬሳውን ሽታ ያጠፋውና በሽታ እንዳይነሣ ይሆናል። ሕዳር ፳ ፲፱፻፲፩ ፡ ዓመተ ምሕረት አዲስ አበባ።
የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዲረክተር
ኅሩይ ፡ ወ ፡ ሥ ።