Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30662
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ወርቅ በእሳት እንደ ሚፈተን ሁሉ ጉራጌም በክልል ጥያቄ እየተፈተነ ነው

Post by Horus » 10 Aug 2022, 03:21

ጉራጌ ክልላዊ መንግስት ወይም ሪጅናል እስቴ ለመሆን ጥያቄ በማንሳቱ አዲስ የህሳቤና የፖለቲካ እድገት ደረጃ ውስጥ ገብቷል ። ምን ማለቴ ነው?

አንድን ሕዝብ ፎርማል በሆነ መንግስትና ግዛት ስር ለመሰብሰብና እስቴት ወይም እራሱን የፖለቲካ ማህበረሰብ ለማድረግ ከሁሉ አስቀድሞ አገር ወይም ቴሪቶሪ ይፈልጋል ።

ስለዚህ የጉራጌ መሪዎች ፣ ከሽማግሎች እስከ ወጣቶች ድረስ ግልጽ ሆነው ማወቅና ለመግለጽ መቻል ያለባቸው ጉራጌ የክልል መንግስት ሲሆን የጉራጌ አገር ወይም መሬት ዳር ድንበር ምን እንደ ሆነ ነው ።

ቀጥሎ ያለው የጉራጌ ሕዝብ እነማን ናቸው? የሚለው ነው። ለምሳሌ ፋሲል የኔአለም ባደረገው ዘገባ አንድ ሰው ከመስቃን ጉራጌ ክለስትር ደግፎ የሚተነትን ሰው አለ ። ያ ሰው ስለ ስልጤ፣ ስለ ማረቆ፣ ስለ ቀቤና፣ ያነሳል ።

አንድ ባንድ ላንሳቸው። ይህ ሰው ስለ ክስታኔ ጉራጌና ስለ ክስታኔ ጉራጌነት የሚያወራው ባብዛኛው ዉሸትና ኔጋቲቨ ነው። ክስታኔ ምንም ከሃዲያ ወይም ማረቆ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም።

ክስታኔ ከስልጤና መስቃን ወንድማማች ቋንቋ ነው። መስቃንና ክስታኔኛ አንድ ናቸው ለማለት ይቻላል። ነገር ግን ጉራጌ አይደለሁም ብሎ የተለየው ስልጤ ነው፣ በዉሸት ማለት ነው። እናም አሁን ጉራጌ ክልል ልሁን ሲል አይ ጉራጌ ክልል ከሆነ እንደ ስልጤ ከመስቃን እርቃለሁ ምናምን ማለት በፍጹም ተቀባይነት የለውም ።

አይምሮ ያለው ስልጤ ቢኖር ስልጤ በጉራጌ ክልል አንድ ትልቅ ዞን መሆን ነው ለማነንቱም ለእድገቱም እጅግ ጠቃሚ ነገር። ስልጤ ከሃዲያ ጋር መለጠፉ ምንም የሚያመጣው ፋይዳ የለም ።

ወራቤና ቡታጀራ ተፎካክረው የሚያድጉ ከተሞች ናቸው ። ይህ የሚሆነው ወራቤ የጉራጌ ከተማም ሆነ አልሆነ ነው።

የመስቃን ቡታጀራ ትልቅ ፉክክሩ ከወልቂጤ ጋር ነው ። ይህ ምንም ችግር የለውም ። ጉራጌ የክልልነት ሬፈረንደም ሲያደርግ ዋና ከተማ ማ ይሁን? ታዳጊ ከተማ ማን ይሁን የሚለውን የጉራጌ ሕዝብ ይወስን! ቡታጀራ ሌላ አዋሳ የመሆን ፖቴንሻል ያለው ከተማ ነው ። ይህ የሚሆነው ግ ን ቡታጀራ የታላቁ ጉራጌ ህዝብ ከተማ ስትሆን እንጂ የሆነ ክለስትር ውስጥ ስትርመጠመጥ አይደለም ! በዚህ መስቃኖች አስቡበት!

ነገር ግን ለዋና ከተማነት ውድድር ሲያደርጉ እንዲያውም የጉራጌን ክልልነት መቃወም ታሪክ ይቅር የማይለው ስህተት ነው። መስቃን እስከነክብሩ የጉራጌን ክልልነት መደገፍ አለበት ።

ማረቆና ቀቤና ምርጫቸው ከሆነ ልዩ ዞን ይሁኑ፣ ምርጫቸው ከሆነ የጉራጌ ዞን መሆን ይችላልሉ።

ይህም ሆነ ያ ጉራጌ ነኝ የሚል ሰው ጉራጌ በክለስተር ተጨፍልቆ ይጥፋ ካለ ያ ሰው ጉራጌ አይደለም ።

ስለዚህ ሁለተኛው የሪጅናል እስቴትነት ጥያቄ ፈተና የክልሉ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን በግልጽ ዲፋይን ማድረግ አለበት ።

ሌላው የመስቃኑ ተናጋሪ የአዲስ አበባን ጉራጌ ሃይልና ሃብት ዝቅ ዝቅ ለማድረግ ይሞክራል ። ጉራጌ ሁለት እግሮች አሉት! አንድ እግሩ ያገር ቤት ጉራጌ ነው! ሌላው እግሩ ያዲስ አበባ ጉራጌ ነው ። ይህን የማያውቅ ሰው ጉራጌ ሳሆን ማርቆ መሆን አለበት! ማለትም አዲሳባ ብዙ ሕዝብ የሌለው ማለት ነው!