Page 1 of 1

የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 09 Aug 2022, 22:51
by Horus
የጉራጌ ገዢ ሕግ፣ መጀምሪያ የፈጣሪ ቃል ነው! ከፈጣሪ (እዝጌር፣ አላህ፣ ጎይታ) ቀጥሎ የጉራጌ ባሊቅ ቃል ነው ። የጉራጌ ባሊቅ የጉራጌ አባት ነው ። የነዚህ ሰነቻዎች የነዚህ ሽማግሎች ሸንጎ የጉራጌ ሴራ ምንጭ ነው። የቀሩት የፖለቲካ ዝብዝቦች ሁሉ ለዚህ ሴራ ተገዥ ናቸው ። በጉራጌ ቤት የመጨረሻው የሞራል ልዑላን እነዚህ አበው ናቸው ። አቢይና ብልጽግና የማያሸንፉት ትግል ከሰላማዊው ፍቅር ከሆነ ጉራጌ ጋር ጠብ ባይጭሩ ይመከራሉ! ይህ ያልታሰበበት የእብሪተኞች ጠብ መጫር እራሱ ፒፒን በጅጉ ያስከፍለዋል ። ጆሮ ያለው ይስማ!! ጉራጌ ክልል ነው! ኬር ለኢትዮጵያ! ሰብኛ ማለቅ ዬሁን!




Re: የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 09 Aug 2022, 23:26
by Horus
የኢዜማው ግርማ ሴፉ እራሱ ለጉራጌ ሕዝን ጥያቄ መሪነት መስጠት አቅቶት የፒፒ መልካም ፈቃድ የፖሊቲካ ተመጽዋች ታሪክዊ በሆነው የጉራጌ ሕዝብ ጥያቄና ንቅናቄ ላይ ቀዝቃዛ ዉሃ ሊቸልስ ቃጣው ።

የጉራጌ ክልል ዋና ከተማ የት ይሁን ወልቂጤ፣ ቡታጀራ ወይስ ጉብሬ የሚለው እጅግ ቀላል የጉራጌ ሽማግሎች ሸንጎና ምክር ቤት በቀላሉ የሚፈቱት ጉዳይ ነው ። የጉራጌ ክልል እስከ 16 የሚደርሱ ዞኖች ይኖሩታል እነዚህ ግዙፍ ዞኖች እያንዳንዳቸው ከተማ አላቸው። ሁሉም የሚያድጉና የሚፎካከሩ ይሆናሉ! ጉራጌ ባብዛኛው በራሱ ሃብት ነው እነዚህን ከተሞች የሚገነባው ።

ለምሳሌ ያሜሪካ ዋና ከተማ ማለት የመንግስት መቀመጫ ይሆነው የቢሮ ከበርቴዎች መናሀሪያ ማለት ነው ዋሽንግተን የሚባል እጅግ ትንሽና የማይረባ ከተማ ነው። ግዙፎቹ ያሜሪካ ከተሞች እነ ኒው ዮርክ ቺካጎ፣ የመሳሰሉት ናቸው ። እራሱ የኒው ዮርክ እስቴት ዋና ከተማ ኔው ዮርክ ሲቲ አይደለም፣ አልበኒ የሚባል መንደር ነው ።

የጉራጌ ክልል በህዝብ ውሳኔ አንድ ዋና ከተማ ይመርጣል ። ይህ ጥያቄ በሪፈረንደሙ ውስጥ አንድ ጥያቄ ማድረግ ብቻ ነው ። ከዚያ በተረፈ ወልቂጤ ሆነ ቡታጀራ ሆነ ጉብሬ ሆነ እምድብር ወይም ትንሿ ቡዪ (ቡ ኢ) ሁሉም በራሳቸው ያድጋሉ ይመነደጋኡ ።

ግርማ ሴፉ የመንግስት ደሞዝተኛ መሆኑን አሳበቀበጥ ይህን ተራ የህዝብ ውሳኔ ጉዳይ የሰማይ ስባሪ ከሚያክለው የጉራጌ ህልውናና ራስ ገዝነት ጋር እንድ ችግር መጥቀሱ የህዝባችን ጥያቄ ተቃዋሚዎች ምን ያህል ደካማና መሰረተ ቢስ ምክኛት ላይ እንደ ሆኑ ያሳልያል ።


Re: የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 15 Feb 2024, 02:47
by AbyssiniaLady


What a title, crazy delusional elderly listro.

Re: የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 15 Feb 2024, 17:43
by AbyssiniaLady

Re: የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 15 Feb 2024, 17:54
by TesfaNews
WUUUURAAGEEE

Re: የጉራጌ ሕዝብ ቀይ መስመር!

Posted: 19 Feb 2024, 15:54
by AbyssiniaLady