1. የተዋቂ ሰዎች እና መሪዎች ግድያ ተበራከተ ምሳሌ (ኢንጅነር ስመኘው : ጀኔራል ሰዓረ : አርቲስት ሃጫሉ : ዶ/ር አምባቸው...)
2. ጦቢያ በቀጠናው : በአህጉሩ እና በዓለም መድረኮች የነበራት ተሰሚነት እየሟሸሸ እና እየጠፋ ሄደ
3. ኢኮኖሚዋ በዓለም ካሉ በፍጥነት ከሚያድጉ ሀገሮች ተርታ ወርዶ ቁልቁል ተፈጥፍጦ ኤርትራዊያን በተሰማሩበት ህገ ወጥ ንግድ ኮንትሮባንድ : የዶላር ጥቁር ገበያ እና ዘረፋ ምክንያት የዜጎች በኑሮ ውድነት መጠበስ አስከትሏል
4. ፀጥትዋ ደፍርሶ ከርስ በርስ ግጭት አልፎ ወደ የዘር ጭፍጨፋ ጦርነት (genocidal war) እና መበታተን ገባች
5. ሉአላዊነት የሌላት በሁሉም አቅጣጫ በኤርትራ ጭምር ዳር ድንበሯ ተደፍሮ ግዛቶቿ በወራሪዎች ተይዘዋል
6. በሰላም ማስከበር ከዓለም አንደኛ በአፍሪካ አንደኛ የነበረችበት ደረጃ ተባራ ሰራዊቷ ይቅርና የሌሎች ሰላም ሊያስከብር የገዛ ሀገሩ ዜጎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ የሚፈፅም ሰብአዊ መብት ጣሽ ተብሎ ከሰላም ማስከበር ተልእኮ ተባሮ ለራሷ ሰላም አስከባሪ የሚያስፈልጋት ሀገር ኾናለች::
7. ከዓለም ትላልቅ ሀገራት እና ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር የነበራት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግኑኝነት ጠፍቶ ችጋር የጠበሳት የአለም ጭራ ኮኸነችው የኢሳያሷ ኤርትራ ጋር ተጣብቃ ቀርታለች::
8. የኤርትራን ፈለግ በመከታል በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ትልልቅ የኢኮኖሚ እና የዲፕሎማሲ ማእቀቦችን አስተናገደች::
9. ወጣቶቿ ድህነትን በመታገል ህይወታቸውን ለመቀየር ከመታተር ወጥተው በጦር ሜዳ የሚያልቁባት ኾነች
10. ዜጎች : ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ያለፍርድ የሚገደሉባት ፡ የሚታፈኑባት እና የሚሳደዱበት ሀገር ኾነች::
ይቀጥላል...
Please wait, video is loading...