ጠቅላይ ሚንስትሩ ለኣማራ እንደ ግለሰብ ሳይሆን እንደ ማህበረሰብ ያላቸውን ከፍተኛ ጥላቻ ጠፍተው በተከሱቱበት ዕለትም ደግመውታል። ትላንት መንግስታቸው ግራ ቀኙ ሲጠፋው … “ተነሱ ህዝባዊ ጦርነትን በህዝብ ነው የምንመክተው! ህፃን አዋቂ ሳትል … ጠመንጃ - ሳንጃ፣ ዱላ - ቢላዋ ሳትመርጥ ያለህን ይዘህ ዝመት!” ብለው እንዳላስቀሰቀሱት፤ ዛሬ ላይ የ 70 አመቱን ሚልሽያ ሳይቀር “ለሀገር ዕድገት ጠንቅ ነው” ሲሉ ዘልፈውታል።
ከኣንድ ወር በፊት … “የሚበጀን መንግስት ቢለዋወጥ እንኳ በቋሚነት ሊያገለግሉ የሚችሉ የመንግስት ተቋማትን መገንባት ነው” ብለው በመከሩበት መድረክ … "እናንተ ምን አግብቶአቹህ ነው ስለ ህወሃት አሸባሪነት የምታወሩት? ህወሃትን አሻባሪ ያለው አምና የነበረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንጂ እናነተ አይደላችሁምና አያገባች ሁም!” በማለት … የትላንቱ ለዛሬው መሠረት አይሆንም ብለው ሲሞግቱ የሚደመጡት ጠቅላይ ሚንስትር ጊዚያዊና artificial እንጂ ኣንድም ዘላቂ ባህርይ እንደሌላቸው ጠንቅቄ አውቃለሁ።
የሚያስገርመኝ ግን በኣማራው ለኣማራው ተወክለናል ብለው ኣማራው እንደማህበረሰብ በጠቅላይ ሚንስትሩ ሲሰደብና ሲዘለፍ አፋቸውን ከፍተው የሚስቁት ናቸው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚንስትሩ “የምዕራብ ጎጃም ገበሬ በበረዶና ዶፍ ዝናብ ተመቷል፥ ይህን ሰምተዋል?” ብለው በተከበሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ ላይ ሲዘብቱ፥ ሰብሉ ለወደመበት ገበሬ ከማዘን ይልቅ የጠቅላይ ሚንስትሩን ፌዝ ለማድመቅ ከፊት ተቀምጠው ይስቁ የነበሩት አቶ ደመቀ መኮንንና የብአዴን ተወካዮች ነበሩ። ዛሬ ደግሞ … ኣማራው እንደ ክልል ተጠቅሶ ከህፃን እስከ አዋቂው ሲዘለፍ የጠቅላይ ሚንስትሩን ስድብ በፈገግታ የሚያደምቁት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ናቸው። በእውነት … ህወሃትንም ሆነ የዚህን መንግስት ችሎታ ማድነቅ ካለብኝ፦ እነዚህን የመሳሰሉ ኣሳማዎች ከየትና ከምን ውስጥ ቆፍረው እያወጡ የማህበረሰቡ ተወካይ፣ የክልሉ ፕሬዚደንት አድርገው እንደሾሙዋቸውና እንደሚሾምዋቸው ነው።