Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7983
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Good News for the Great people of Gurage!! በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

Post by Wedi » 04 Aug 2022, 10:00

Good News for the Great people of Gurage!!

በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

:P
Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Good News for the Great people of Gurage!! በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

Post by Sam Ebalalehu » 04 Aug 2022, 12:17

wedi, I am amazed with your current fascination in የደቡብ ክልል ፖለቲክስ። የመጨረሻ ሙከራ ምናልባት የአጎቶችህን ፖለቲካ ነፍስ ለመዝራት። የቅማንት ነገር አልሆነም። የአገው ጉዳይ አልተሳካም። ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞችን ማስገደል ወደ እርስ በርስ እልቂት እንደታሰበው አልመራም። እና ሰሞኑን ደቡብ ኢትዮጵያ ድንኳን ተክለሀል።
የሚቀናሀ አይመስለኝም።

Right
Member
Posts: 2796
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Good News for the Great people of Gurage!! በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

Post by Right » 05 Aug 2022, 00:08

Wedi,
why not? If Tigrai with 3 million people can be killil so is Gurage.
Either scrap the Killil system or let them be killil. It is their constitutional right.

Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Good News for the Great people of Gurage!! በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

Post by Horus » 05 Aug 2022, 02:02

wedi,
ባንድ በኩል የኦሞ ክልል የተባሉትና ስም የለሹ ማዕከላዊ ክልል የተባሉት እነስልጤ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ዞኖች በሁለት ክልል ለመኖር ማስማማታቸው ጥሩ ነው። ውጥረቱን በትንሹ ከጉራጌ ያነሳዋል ። ምክኛቱም ስልጤ ወላይታና ሃዲያ ክልል ካልሆንን ያሉ ግዜ ደቡብን ምን ማድረግ ስለቸገራቸው ብልጽግናዎች ተገናግጠው ነበር።

ይህ ማለት ግን ግፊቱ ከጉራጌ ተነሳ ማለት አይደለም ። ከላይ ያሉት በ2 ክለስተር የተጨፈለቁት ድሮ በምክር ቤታቸው ክልል ለመሆን የወሰኑ ነበሩ። በብልጽግና በትር ነው እንደ ገና በመሰብሰብ አዲስ አቋም የያዙት ። በተመሳሳይ በጉራጌ ምክር ቤት ላይ ተመሳሳይ ግፊት እያደረጉ ነው። ልዩነቱ ጉራጌ በ4ቱም እርከን (የሽማግሎች ሸንጎ፣ የጉራጌ ምክር ቤት፣ የጉራጌ ዞን አስተዳደር እና የጉራጌ ወጣት (ዘርማ/አርዴ) አራቱም ጽኑ ሙሉ አቋም አላቸው ። በጉራጌ ከክልልነት ውጭ የሚታሰብ ነገር የለም ።

ለዚህ ነው ምንም ጉዳይ ምንም ችግር በሌለበት የአሽቸኳይ ግዜ አዋጅ በጉራጌ የተጣለው ። ነገር ፍለጋ፣ ህዝቡን አስነስተው በጸጥታ ሳቢይ ጉራጌን ለመግዛት፣ ለመጨፍለቅ ነው ። ይህ ሕዝባችን በውል የገባው ነገር ነው። አሸባሪው መንግስት እንደ ሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል።

የጉራጌ ጥያቄ አሁን ያለው በፌዴርሽን ምክር ቤት በይግባኝ ሰሚ ጠረጴዛ ላይ ነው። ለ3 አመት መልስ ሳይሰጥ የተቀመጠበት በብልጽግና ማለትም ባቢይ የሚታዘዘው ፌዴራል ምክር ቤት ተብዬ ነው። ጉራጌ ሌላ ስብሰባ ምንትሴ አያደርግም። አሁን ኢትዮጵያ በምትገዛበት ሕገ መንግስት መሰረት ሁሉንም ነገር አሏልቶ ጥያቄውን ካስገባ 3 አመት አልፏል።

ጉራጌ ቁጭ ብሎ መልስ እየጠበቀ ነው ። በቃ! ህጉ የሚለው አንድ ዞነ የክልልነት ጥያቄ ባስገባ ባመት ውስጥ ሬፈረንደም ያደርጋል ይላል። ይህን ጥሰው ነው የድፍን ጉራጌን ጥያቄ በሃይል ለመግታት የሚጥሩት!

ያገር አባቶች፣ የሁላችንም የበላዮች ይህን የጉራጌ ውሳኔ ለመሻር የሚሞክርን አውግዘዋል! ነገሩ ሁሉ እዚህ ላይ ነው ያለው! ጉራጌ እንደ 1 ሰው ቆሞዋል!

Wedi
Member+
Posts: 7983
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: Good News for the Great people of Gurage!! በደቡብ ክልል የሚገኙ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ!!

Post by Wedi » 05 Aug 2022, 05:04

Horus wrote:
05 Aug 2022, 02:02
wedi,
ባንድ በኩል የኦሞ ክልል የተባሉትና ስም የለሹ ማዕከላዊ ክልል የተባሉት እነስልጤ 10 ዞኖችና 6 ልዩ ዞኖች በሁለት ክልል ለመኖር ማስማማታቸው ጥሩ ነው። ውጥረቱን በትንሹ ከጉራጌ ያነሳዋል ። ምክኛቱም ስልጤ ወላይታና ሃዲያ ክልል ካልሆንን ያሉ ግዜ ደቡብን ምን ማድረግ ስለቸገራቸው ብልጽግናዎች ተገናግጠው ነበር።

ይህ ማለት ግን ግፊቱ ከጉራጌ ተነሳ ማለት አይደለም ። ከላይ ያሉት በ2 ክለስተር የተጨፈለቁት ድሮ በምክር ቤታቸው ክልል ለመሆን የወሰኑ ነበሩ። በብልጽግና በትር ነው እንደ ገና በመሰብሰብ አዲስ አቋም የያዙት ። በተመሳሳይ በጉራጌ ምክር ቤት ላይ ተመሳሳይ ግፊት እያደረጉ ነው። ልዩነቱ ጉራጌ በ4ቱም እርከን (የሽማግሎች ሸንጎ፣ የጉራጌ ምክር ቤት፣ የጉራጌ ዞን አስተዳደር እና የጉራጌ ወጣት (ዘርማ/አርዴ) አራቱም ጽኑ ሙሉ አቋም አላቸው ። በጉራጌ ከክልልነት ውጭ የሚታሰብ ነገር የለም ።

ለዚህ ነው ምንም ጉዳይ ምንም ችግር በሌለበት የአሽቸኳይ ግዜ አዋጅ በጉራጌ የተጣለው ። ነገር ፍለጋ፣ ህዝቡን አስነስተው በጸጥታ ሳቢይ ጉራጌን ለመግዛት፣ ለመጨፍለቅ ነው ። ይህ ሕዝባችን በውል የገባው ነገር ነው። አሸባሪው መንግስት እንደ ሆነ ጠንቅቀው ያውቁታል።

የጉራጌ ጥያቄ አሁን ያለው በፌዴርሽን ምክር ቤት በይግባኝ ሰሚ ጠረጴዛ ላይ ነው። ለ3 አመት መልስ ሳይሰጥ የተቀመጠበት በብልጽግና ማለትም ባቢይ የሚታዘዘው ፌዴራል ምክር ቤት ተብዬ ነው። ጉራጌ ሌላ ስብሰባ ምንትሴ አያደርግም። አሁን ኢትዮጵያ በምትገዛበት ሕገ መንግስት መሰረት ሁሉንም ነገር አሏልቶ ጥያቄውን ካስገባ 3 አመት አልፏል።

ጉራጌ ቁጭ ብሎ መልስ እየጠበቀ ነው ። በቃ! ህጉ የሚለው አንድ ዞነ የክልልነት ጥያቄ ባስገባ ባመት ውስጥ ሬፈረንደም ያደርጋል ይላል። ይህን ጥሰው ነው የድፍን ጉራጌን ጥያቄ በሃይል ለመግታት የሚጥሩት!

ያገር አባቶች፣ የሁላችንም የበላዮች ይህን የጉራጌ ውሳኔ ለመሻር የሚሞክርን አውግዘዋል! ነገሩ ሁሉ እዚህ ላይ ነው ያለው! ጉራጌ እንደ 1 ሰው ቆሞዋል!
ወላይታ ራሱ ክልል መሆን አለበት!! የወላይታ ህዝብ ክልል ለመሆነ ጥያቄ ቢያወርብም በኦሮሞሙማ ከፍተኛ ግድያ እና ሰቆቃ እየደረሰበት ይገኛል!! የወላይታ ህዝብ የጠየቀው በህገመንግስቱ የተቀመጠውን እና ለሲዳማ የትፈቀደውን መብት እንጅ አዲስ ነገር አይደለም!!

በነገራችን ላይ ወላይታ ሶዶን አዋሳ ዮኒቨርስቲ ተማሪ ሳለሁ ለጉብኝት ሂደን ጎብኝቻታለሁ፡፡ እጅግ ደስ የምትል ከተማ ናት፡፡

በወላይታ ሰዶ የገጠመኝ እስቂኝ ነገር የሚከተለው ነው፡፡ ያው ተማሪ መሆነ ያው ችግር ነው፡፡ እናም Farm Africa የሚባል አንድ ድርጅት የመጨረሻ አመት ተማሪዎችን በእጣ እያወጣ የተወሰኑትን ወደ ተላያዮ ቦታዎች እየወሰደ ያስገበኛል፡፡ በዚያን ግዜ በቀን የሚሰጠን የውሎ አበል ወደ 30 ብር አካባቢ ነበር፡፡ እናም እኛም ለጉብኝት ወደ ወላይታ ሶዶ ሄድን፡፡ ከጓደኛችን አንዱ ገንዘብ ለመቆጠብ ፈልጎ ወላይታ ሶዶ ውስጥ አንድ ሆቴል ለምሳ ከገባ በኋላ ምግብ ሲያዝ ለአስተናጋጁ "ቀለል" ያለ ምግብ ነው መመገብ የምፈልገው ብሎ ይለዋል፡፡ ከዚያም አስተናጋጁ ለሁላችን እንጀራ በሆነ ወጥ ሲያመጣልን "ቀለል" ያለ ምግብ ብሎ ላዘዘው ጓደኛቸን ደግሞ ፓስታ ያመጣለትና ይመገባል፡፡ በመጨረሻም ዋጋው ሲመጣ እኛ ለተመገብነው እንጀራ በወጥ አነስ ያለ ዋጋ ስንከፍል፣ ፓስታ የተመገበው ጓደኛችን ደግሞ እኛ ከከፈልነው ወደ እጥፍ የሚጠጋ እንዲከፍል ተደረገ፡፡ ጓደኛችን "ቀለል" ያለ ምግብ ሲል በዋጋው ውድ ያለሆነ ማለቱ ነበር፡፡ አስተናጋጁ ደግሞ "ቀለል" ያለ ምግብ ሲል ለሆድ የማይከብድ ማለቱ ነበር፡፡ ፓስታ የተመገበውው ጓደኛቸን የተመገበው ፓስታ ክፍያው ውድ ሲሆንበት እና ያልጠበቀው ነገር ስለሆነበት እጅግ በጣም ተናዶ ሲከራከር ስናይ እኛም ሁኔታውን እያየን በሳቅ ልምንፈነዳ ደረሰን ነበር፡፡

ሀሳብን በግልጽ አለመናገር የሚያመጠዋን ጣጣ ተመልከትልኝ!! :lol: :lol:

Post Reply