Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12530
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

ሰበር ዜና : ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሐይል በጎጃም በኩል አባይን ተሻግሮ ወለጋ ከሰሞኑ በሰፊው እየገባ ነው!!

Post by Thomas H » 06 Jul 2022, 20:45

Andinet Zeleke Bekele

·
ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሐይል በጎጃም በኩል አባይን ተሻግሮ ወለጋ ከሰሞኑ በሰፊው እየገባ ነው!!
******************************
ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሐይል ከጎጃም ቡሬ ከተማ በሲኖ-ትራክ እና በባስ እየተጫኑ የሁለቱን ክልሎች ድንበር የሆነውን አባይ ወንዝ ድልድዩን እየተሻገሩ ወለጋ እየገቡ እንደሆነ የአይን እማኞች እየተናገሩ ነው፡፡ ይህንን ወታደራዊ ዘመቻ አማራ ክልል ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር በተስማማው መሰረት በፍጥነት እየፈጸመው ይገኛል፡፡ ይህ ኦሮሚያ ክልል አካል የሆነውን ወለጋን የመውረር የቆየ የተስፋፊዎች ምኞት እና አጀንዳ ኢህገመንግስታዊ ነው፡፡
ከዚሀ በፊት ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሐይል ወደ ኦሮሚያ ክልል በተደጋጋሚ ተሻግረው ሲገቡ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ሆኖም በድንበር ከተማዎች በሆኑት ጉትን እና መሰል ቀበሌዎች ላይ ከኦሮሚያ ልዩ ሐይል ጋር ጦርነት በመግጠም ተሸንፈው ይመለሳሉ፡፡ ይህ ኦሮሞ ጠል ታጣቂ ሐይል በወለጋ ስለማይፈለግ፤ ህዝቡ ጭምር ነበር ተዋግቶ የሚመልሳቸው ፡፡
ነገር ግን ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወለጋን ለመቆጣጠር በተመኙት መሰረት፤ በአደባባይ ለመግባት ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር 'መተጋገዝ' በምትል ብልጣብልጥነት ከተስማሙ ቦኋላ፤ በመከላከያ ተደግፈው ከጎጃም ቡሬ በቀጥታ ተሳፍረው ወለጋ እየገቡ ነው፡፡ አመጣታቸው በጣም ብዛት ያለው መሆኑ በአይን እማኞች እየተነገረ ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መረጃ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማወቅ አለበት፡፡
ባጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ሰፊ ቁጥር ያለው ፋኖ እና የአማራ ልዩ ሐይል ከጎጃም በመምጣት በወለጋ ሰፍሮ ከመከላከያ ጋር አብሮ በመሆን ከኦነግ ጋር እየተዋጋ ይገኛል፡፡ ፋኖ እና የአማራ ሚሊሻ በኦሮሞ እና በተጋሩ ጥላቻ ያበዱ ታጣቂ ሐይሎች ስለሆኑ፤ ንጹሐን የኦሮሞ አርሶአደሮችን ልክ ትግራይ እንደፈጸሙት፤ ዘር ተኮር ጭፍጨፋ፤ የወለጋ ህዝብን በቀዬው እንዳይፈጁት፤ ከፍተኛ ስጋት ተደቅኖ ይገኛል፡፡ ይህ ትክክለኛ መረጃ ስለሆነ ጉዳዩን በአንክሮ ተከታተሉ!