Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በጎሳ ካድሬ ስድብ ሆረስን ማሸማቀቅ የማይታሰብ ነው፣ የድጋይ ጠጠር ቆሎ አይደለምና!

Post by Horus » 03 Jul 2022, 21:46

እዚህ ፎረም አይም ሆነ ሌላ ሳይበር ገጻ ላይ 1 ሺ 1 ፌክ ስሞችን በመጠቀም 24/7 የሚዘላብዱ በእኔ ሆረስ ዘንድ ማንኛውም ተራ ባዶ አብስትራክት ምስሎች ናቸው ። ለእኔ ቁሳዊ አካላ ያላቸው፣ በዚያ አካል ላይ አንጎል የተሸከሙ ፊዚካል ፍጡራን አይደሉም ። ማናልባት ከስማቸው ጀርባ የሚያስብ እንሰአ ካለና ፋይዳ ያለው ሃሳብ ከለጠፈ እኔ መልስ የምሰጠው ለዚያ ሃሳብ እንጂ መኖር አለመኖሩን ለማላውቀው ምስል ምልክት አይደለም ።

ይህን በተመለከተ ከትላንት ወዲያ ለአበረ የነገርኩትን ደግሜ ይህ ከዚህ በታች ለጥፌዋለሁ!

"እንደ ምታውቀው የሰው ልጅ ቋንቋን ከሪያሊቲ አብስትራክት ለማድረግ የቻለ ፍጡር በመሆኑ አንዲት የታወቀች የሃርቫርድ የህጻናት ኮግ ኒቲቭ ሳይንቲስት ምን ትል ምሰለህ፤ "With language anybody can create anything". ይህም ማለት አንድ ምንም አይነት እውነት በውስጡ ያልያዘ አረፍተ ነገር ጽፈን እንደ መረጃ ወይም ፋክት ለማሰራጨት እንችላለን ። ይህም በመሆኑ ይህው እዚህ ፎረም ላይ ሁላችንም በብዕር ስለምንጠራ ከስማችን ጀርባ ያለው ቁሳዊ ሰው ማ እንደሆነ አይታወቅም ። ደግሞ ያ በመሆኑ አንድ ወንድ እንደ ሴት፣ አንድ አማራ እንደ ትግሬ፣ አንድ ኦሮሞ እንደ ጉራጌ ሆኖ በማስመሰል ለመጻፍ ይችላል ።

ለዚህ ችግር እኔ የራሴ መፍትሄ አለኝ። ጸሃፊው በኔ ሃሳብ ላይ አንድነት፣ ቅዋሜ ወይም ሂስ አድርጎ ከሆነ ለዚያ መልስ እስጣለሁ ። የተቃዋሚዬን ሃሳብ ለመለወጥ ሳይሆን አንባቢ ትምህርት ወይም መረጃ እንዲያገኝበት ። ጸሃፊው የማይስማማኝ፣ የማውቀው ተጻራሪዬ ከሆነም እንዲሁ የምሰጠው መልስ ለሱ ሳይሆን አንባቢ የተለየ አመለካከት እንዲያገኝ ብቻ ነው ።

ስለዚህ DDTን ምክንያታዊ ሃሳቢ እንዲሆን የምመልስለት፣ እሱ የጻፈው ነገር እንደ ማስተማሪያ በመጠቀም ለሌሎች አንባቢዎች መረጃ ወይም ትህምህርት ለመስጠት ነው። በዚህ ዘዴ መሰረት እውነት የሚጽፉም፣ ዉሸት የሚጽፉም፣ ስህተት የሚናገሩም ትክክል ነገር የሚሉም ማስተማሪያ ይሰጡኛል ማለት ነው። ለሁሉም ለጣፊ አልመልስም። አንድ ለራሴን ፋይዳዊ ነው የምለው መልዕክት ማስተላለፊያ እድል ሲፈጥሩልኝ ብቻ ነው ዝብዝብ ውስጥ የምሄደው ።"

ስለዚህ እናንት ህልው አልባ ለሆናችሁ የወያኔና ሌላ ጎሳ ካድሬ ምስሎች ያለኝ ምክር ግዜያችሁን አታባክኑ! ሆረስ አይሸማቀቅም! ሆረስ በሳይንስ እንጂ ይሉኝታ የሚገዛ ሰው አይደለም! ምንም ሰው/ምስል ሆረስን ቢሰድብ ሺ ግዜ የሚሰቀጥጥ የስድብ ምላሽ መጠበቅ አለበት !!!