Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

LiVE:- Ethio 360 "ይሄንንስ ጉድ ምን ስያሜ እንስጠው?" “22 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ጨምሮ 61 ሰዎችን ቀብሬያለሁ” ከጊምቢው ጥቃት የተረፉ አባት አቶ መሐመድ የሱፍ

Post by Wedi » 02 Jul 2022, 13:33

LiVE:- Ethio 360 "ይሄንንስ ጉድ ምን ስያሜ እንስጠው?"
:oops:
“22 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ጨምሮ 61 ሰዎችን ቀብሬያለሁ” ከጊምቢው ጥቃት የተረፉ አባት አቶ መሐመድ የሱፍ 😢 ምንጭ ቢቢሲ አማርኛ/BBC Amharic


https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n3kygd0kko

:oops:

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: LiVE:- Ethio 360 "ይሄንንስ ጉድ ምን ስያሜ እንስጠው?" “22 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ጨምሮ 61 ሰዎችን ቀብሬያለሁ” ከጊምቢው ጥቃት የተረፉ አባት አቶ መሐመድ የሱፍ

Post by Wedi » 02 Jul 2022, 13:49

በኦሮሚያ ክልል አብይ አህመድ እና ሽመልስ አብዲሳ በሚመሩት ገዳይ ቡድን በአንዲ ቀን ብቻ 22 ልጆቻቸው እና የልጅ ልጆቻቸው ተጨፍጭፈው የተገዱሉባቸው አቶ መሐመድ የሱፍ

የቢቢሲ አማርኛ ዘገባን ከዚህ በታች አንብቡት!!

https://www.bbc.com/amharic/articles/c4n3kygd0kko

*******************************************


“22 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ጨምሮ 61 ሰዎችን ቀብሬያለሁ” ከጊምቢው ጥቃት የተረፉ አባት

2 ሀምሌ 2022,

ቅዳሜ፣ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ወለጋ ዞን፣ ጊምቢ ወረዳ፣ ቶሌ ቀበሌ በተፈፀመው ጭፍጨፋ በርካታ ነዋሪዎች የቤተሰብ አባላቶቻቸው ተገድለውባቸዋል።

ከእነዚህ ነዋሪዎች መካከል አቶ መሐመድ የሱፍ አንዱ ናቸው።

የ64 ዓመቱ መሐመድ፣ ከትውልድ አካባቢያቸው አማራ ክልል፣ ሀርቡ ወረዳ ወደ ወለጋ የሄዱት በ1990 ዓ.ም እንደሆነ ይናገራሉ።

አካሄዳቸው በወቅቱ በአካባቢው የነበረውን ድርቅ ሽሽት ነበር።

ወደዚያ ሲያቀኑ በወጣትነታቸው እድሜ ያገቧትን ባለቤታቸውንና ስድስት ልጆቻቸውን ይዘው ነበር። እዚያም ከሄዱ በኋላ በሕጋዊ መንገድ መሬት ተመርተው፣ ተገቢውን ግብር እየከፈሉ በግብርና ሥራ ተሰማርተው ይኖሩ ነበር።

እዚያም ተጨማሪ ልጆችን አፍርተዋል። የልጅ ልጆችንም አይተዋል።

“ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ስጋት አልነበረም።ለፍተን፣ አርሰን ነበር የምንኖረው” የሚሉት አቶ መሐመድ፣ ቅዳሜ ዕለት የደረሰባቸው ግን ከውስጣቸው የማይወጣ ሐዘን ጥሎባቸው አልፏል።

የዚያን ዕለት አካባቢው በታጣቂዎች ሲወረር “ሴቶችና ሕጻናትን አይገድሉም ብለን ልጆቼም የልጅ ልጆቼም እኔ ቤት ተሰባስበው፣ በር ዘግተው ተቀመጡ። እኔ ደግሞ በቆሎ ማሳ ውስጥ ተደበቅኩ” ይላሉ የነበረውን ሁኔታ ሲያስታውሱ።

ከዚያም ከግማሽ ቀን በላይ የዘለቀው የጥይት ተኩስ ጋብ ሲል ወደ ቤታቸው ማምራታቸውን አቶ መሐመድ ይናገራሉ።

ቤታቸው ሲደርሱ ግን በሩ ወለል ብሎ ተከፍቶ ነበር።

ወደ ውስጥ ዘልቀው ሲገቡ ትተዋቸው የወጡት የቤተሰብ አባላቶቻቸው ቤት ውስጥ አልነበሩም።

“ከዚያ እዚህም፣ እዚያም እየባዘንኩ ፍለጋ ያዝኩ” ይላሉ።

በፍለጋቸው ከልጅነት የትዳር አጋራቸው፣ ከልጆቻቸው እናት ጋር መንገድ ላይ ተገናኙ። ባለቤታቸው ጎናቸውና መዳፋቸው ላይ በጥይት ተመትተው በደም ተለውሰው ወደ ቤት እያቀኑ ነበር።

“በድንጋጤ ተውጠን ነበር። ‘ልጆቹስ?’ ብዬ ጠየቅኳት” ይላሉ አቶ መሐመድ።

በአቅራቢያው የሚገኝ መስጊድ አጠገብ እንደተገደሉ ነገሯቸው። ሲበሩ ከቦታው ደረሱ።

የተረፈ ግን አልነበረም።

“አራስ ልጅ ሳይቀር አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ተደራርበው አገኘኋቸው” ይላሉ ሳግ እየተናነቃቸው።

እርሳቸው እንደሚሉት ቤተሰቦቻቸው የተገደሉት ከሚኖሩበት መንደር፣ ጨቆርሳ ስልሳው ወደሚባለው መንደር ተወስደው አቅራቢያ በሚገኝ መስጊድ አጠገብ ነው።

“የእኔን ቤተሰቦች ጨምሮ በዚህ ቦታ በአንድ ላይ የተጨፈጨፉት 42 ናቸው” ይላሉ።

አቶ መሐመድ አሁንም እንባቸው አላባራም።

“የመጀመሪያ ልጄን ሰሚራ መሐመድን ከአምስት ልጆቿ ጋር፣ አሚናት መሐመድ ከአራት ልጆቿ ጋር፣ አመት መሐመድ፣ ሰዓዳ መሐመድ፣ ፋጢማ መሐመድ ከአምስት ልጆቿ ጋር፣ መሬማ መሐመድ ከሁለት ልጆቿ ጋር ተገድለውብኛል” ይላሉ።

አቶ መሐመድ እንደሚሉት ሌሎች የእህት ልጆቻቸውም የተገደሉባቸው ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው 6 የቤተሰብ አባላቶቻቸውም ነቀምትና ጊምቢ ሆስፒታል ሕክምና ላይ ይገኛሉ።

ከተገደሉት ውስጥ በዕድሜ ትልቋ የመጀመሪያ ልጃቸው የ40 ዓመቷ ሰሚራ መሐመድ ስትሆን በእድሜ ትንሹ ደግሞ የአራት ቀናት ዕድሜ ያላት የእህታቸው ልጅ መሆኗን ተናግረዋል።

“ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ለመቅበር በማስኩት ጉድጓድ 61 ሰው ነው አብሮ የተቀበረው” የሚሉት አቶ መሐመድ፣ ሙሉ ቤተሰቡን አጥቶ ብቻውን የቀረው ብዙ ነው ብለዋል።

“አርሰን በመብላታችን እንጅ፣ አንድም የደረስንባቸው ነገር የለም። የአማራ በመሆናችን ብቻ ነው የገደሉን” ሲሉም ጥቃቱ እዚያ በሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ መሐመድ ቤታቸው፣ መጋዘናቸው እና ንብረታቸው በእሳት ወድሞባቸዋል።

አሁን ላይ ከእሳት በተረፈው ቤት ውስጥ ከሞት ከተረፉ ቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀምጠው እንዳሉም ለቢቢሲ ገልጸዋል።

“በሐዘን ደም እየተፋሁ ነው ያለሁት፤ አዕምሮዬም አይሰራም” የሚሉት አቶ መሐመድ፣ እንዴት ሆናችሁ ብሎ የጠየቃቸው የመንግሥት አካል አለመኖሩ ደግሞ ሐዘናቸውን እንዳበረታው ተናግረዋል።

እርሳቸው እንደሚሉት አሁንም አካባቢው ከስጋት ነጻ አይደለም።

“ የት ነው የምትሄዱት ብለው ያዙን እንጂ መንግሥት እንዲያወጣን ነው የምንፈልገው። የምንወዳቸውን ልጆቻችንን እና ቤተሰቦቻቸንን ጓሯችን ላይ ቀብረን ምን ላይ ነው የምንኖረው?” ሲሉም ይጠይቃሉ።

“የተረፉ ሴቶችና ሕጻናት በእግራቸው አካባቢውን ለቀው መውጣት ይዘዋል” ሲሉም ያክላሉ።

ቢቢሲ ስማቸውን የማይጠቅሳቸው አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን፣ በሰኔ 11ዱ ጭፍጨፋ ከተገደሉት መካከል አብዛኞቹ ነፍሰ ጡር፣ ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው፣ መሐመድ የሱፍ የሚባሉት ነዋሪም 22 ልጅና የልጅ ልጆቻቸውን አጥተዋል ሲሉ አረጋግጠዋል።

ቀብር ላይ እንደተሳተፉ የገለጹት ባለሥልጣኑ፣ ከተገደሉት የአቶ መሐመድ ቤተሰቦች መካከል የሁለት ዓመት ተኩል፣ የሰባት ዓመት እና የ10 ዓመት ሕጻናት እንደሚገኙበት አክለዋል።

ባለሥልጣኑ ስለነበረው የደኅንነት ስጋት ቀደም ብሎ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳልደረሳቸው ተናግረው፣ ታጣቂዎቹ ግን በአካባቢው በሚገኝ በርሃ ውስጥ ከሦስት ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ እየኖሩ ነው ብለዋል።

“ለአንድ ወር ያህልም በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ጉዞ ሲያደርጉ ተመልክተናል። ወደ ደንቢዶሎ ነው የሚጓዙት ይባል ነበር። ከግንቦት ወር ወዲህ ግን ምንም መረጃ አልነበረንም” ሲሉም ባለሥልጣኑ ተናግረዋል።

ባለሥልጣኑ “ከወረዳው ጋር አንገናኝም፣ መንገድ ዝግ በመሆኑ ወደ ወረዳ ብንጠራም አንሳተፍም። በአጋጣሚ የፀጥታ ኃይሎች ሲመጡ ብቻ ነው በቀበሌው የምንንቀሳቀሰው” ሲሉም ያለውን የደኅንነት ስጋት አስረድተዋል።

“ቅዳሜ ዕለት ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት አርብ ዕለት የፀጥታ ኃይሎች ቀበሌውን ለቀው ሲወጡ ነበር። ምክንያቱን ስንጠይቅ ግን ይህ ነው ተብሎ አልተነገረንም፤ በፍራቻ እና በጥርጣሬ ውስጥ ነበርን” ብለዋል።

በአሜሪካ የአማራ ማኅበር ሰኔ 11 ቀን በተፈጸመው በዚህ ጥቃት በርካታ ነዋሪዎች ሙሉ ቤተሰባቸው አሊያም አብዛኞቹ የቤተሰብ አባላቸው እንደተገደሉባቸው ገልጾ፣ በጨቆርሳ የሚኖሩት መሐመድም ዘመድ አዝማዶቻቸውን ጨምሮ 31 የቤተሰብ አባላቶቻቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በጭፍጨፋው የተገደሉ ሰዎች ቁጥርን በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት 338 ናቸው ያለ ሲሆን፣ በአሜሪካ የአማራ ማኅበር ደግሞ አሃዙን ወደ 600 እንደሚጠጋ አመልክቷል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የዐይን እማኞች እና ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች እንዲሁም መንግሥት ጥቃቱን የፈጸመው ‘ሸኔ’ በመባል የሚታወቀው ታጣቂው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት እንደሆነ ገልጸዋል።

ቡድኑ ግን ለጥቃቱ የመንግሥት ኃይሎችን ተጠያቂ አድርጓል።

መንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የአማራ ብሔር አባላት ላይ ተፈጽሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ አብዛኞቹ ሴቶችና ሕጻናት በተገደሉበት ጥቃት በርካታ ቤቶች በማቃጠላቸው ቢያንስ 2000 ሰዎች ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ብሏል።

ጥቃቱን ተከትሎ ኮሚሽኑን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች በጭፍጨፋው ዙሪያ ፈጣን፣ ገለልተኛና ዝርዝር ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ከተከሰተው እንዲሁም በጋምቤላ “በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አጣርቶ እንዲያቀርብ” አዟል።

በተጨማሪም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለሙያዎች በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ውስጥ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ እንደሚመረምሩ ተነግሯል።


Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: LiVE:- Ethio 360 "ይሄንንስ ጉድ ምን ስያሜ እንስጠው?" “22 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን ጨምሮ 61 ሰዎችን ቀብሬያለሁ” ከጊምቢው ጥቃት የተረፉ አባት አቶ መሐመድ የሱፍ

Post by Wedi » 02 Jul 2022, 17:29

tekeba wrote:
02 Jul 2022, 17:21
Wedi/Tarik don't try to deceive anyone you are fooling yourself mother fuxcker
ጋላ tekeba this is BBC Amharic report. not mine. :P

Post Reply