Page 1 of 1

ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ! አበሻ = አቢሲኒያ = ኢትዮጵያዊ = ቀይ ሕዝብ !

Posted: 01 Jul 2022, 00:35
by Horus

Re: ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ!

Posted: 01 Jul 2022, 01:03
by Horus
This is guy is wrong. ይህ ቸግ ይባላል። ፍጥምጥም ማለት ነው ። ሰርግ አይደለም። ልጃገረዶቹ ቀንዣዠ ይባላሉ ጸጉራቸው በውፋ ቅቤ ተሸፍኖ! ድሮ ወንዶችም ያደርጉት ነበር ። ለምሳሌ አጼ ምኒልክ ብዙውን ግዜ ጸጉራቸው ዉፋ ቅቤ ተገርጎላቸው በሻሽ ከታሰረ በኋላ ነው ባርሜጣ የደርጉ ነበር ። ይህን ባህል የያዙት ምናልባት እናታቸው ጉራጌ ስለነበሩ ይሆናል ። ምኒልክ በብዙ መንገድ ስብዕናቸው እንደ ጉራጌ ፐርሰናሊቲ ዘና ያለ ለሰው የሚመቹ ሰው ነበሩ!


Re: ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ!

Posted: 01 Jul 2022, 02:00
by Horus
ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ የሚለው ስንኝ በከፊል ከሰርግ ዘፈን የወሰድኩት ነው ። ላማቶች ለምራቶች እነዚህ ቀያይ ኮረዳዎች አናታቸው ላይ ቅቤ ይደረግላቸው ማለት ነው። ቅቤ ለውበትም ከክብርም አናት ላይ ይደረጋል ። ሽማግሎች አባቶች እናቶች አናት ላይ ሲደረግ ልክ ቡልኮና ካባ እንደ ሚደረብላቸው የመከብራቸው ፣ የፍጽምናቸው፣ የስኬታቸው ማመልከቻ ነው። በሃይማኖትም ቅብዓ ቅዱስ ሲባል ያው ነው። በተረፈ ቅቤ የልምላሜ፣ የርጥብነት፣ የወላድነት ምልክት ነው ። ብሻ ማለት በጉራጌኛ ቀይ ማለት ሲሆን ባረብኛም ብሻ ነው! ቀይ ማለት ነው ። አበሻ የሚለው የኢትዮጵያ አረብኛ ስም የመጣበት ቃል ነው! በግሪክ አይቴ ኦፖስ ማለት ቀይ ፊት ያላቸው ሕዝቦች ማለት ነው ። ኢትዮጵያ ማለት የአረብኛው ስማችን የግሪክ ትርጉሙ ነው! ብሻ ግሪዳደ ማለት ቀያዮቹ ልጃገረዶች ማለት ቢሆንም ቅኔው ግን አበሾቹ ኢትዮጵያዊያቱ ኮረዶች ማለት ነው !!!! ኬር!!!

Re: ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ!

Posted: 01 Jul 2022, 02:31
by Horus
እግረ መንገዴን ይህቺን ፋክት ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ልንገራችሁ! ካልተስማማችሁ የቋንቋ ሊቃውንት አምጡና ርቱኝ! አበሻ ማለት ፈረንጆች አቢሲኒያ የሚሉት ሕዝብ ነው። ቃሉ አረብኛ ነው ። ትርጉሙ ቀይ ሕዝብ ማለት ነው ። የግሪክኛ ብሻ ፊት ያላቸው ለሚለው ትርጉም ሲሰጡ ደም የሚመስለው ሳይሆን እሳት ለሚመስለው ቀይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው ብለው ተረጎሙት ። ትክክለኛ ቃሉ ያለው 'ብሻይ' 'Bishai' = red የሚለው ጥንታዊ ቃል ነው ። ያ ደሞ ቱባ ሆኖ ሳይሸራረፍ ያለው ጉራጌኛ ቋንቋ ውስጥ ነው ። ብሻ ማለት ዛሬ ቀይ ማለት ነው። ስለሆነም በአበሻና ኢትዮጵያ መሃል ልዩነት ለማግኘት የምትለፉ እርሱት! ቃሉ አንድ ነው፤ አበሻ አረብኛ፣ ኢትዮጵያ ግሪክኛ ነው! በቃ !!

Re: ያማተ የቦሊተ ብሺ ግሪዳደ ቅብ ያውንበማ ባናተ! አበሻ = አቢሲኒያ = ኢትዮጵያዊ = ቀይ ሕዝብ !

Posted: 01 Jul 2022, 06:53
by Right
The number of People killed by the Amharas massacre in Welega passed 3000.