Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10894
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግብዝነት:- የጎሳ ክልል እና ጎሳ ፓርቲ እንድ ሰረዝ አንድም ቀን አልጠየቀም። በዓለም አቀፍ ህግ የተከለከለ ወንጀል እያየ ዝም ይላል።

Post by Abere » 30 Jun 2022, 11:15

የኢትዮጵያ ሰብ አዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ግብዝነት - የጎሳ ክልል እና ጎሳ ፓርቲ እንድ ሰረዝ አንድም ቀን አልጠየቀም - ለዓለም አቤቱታ አላቀረበም። በዓለም አቀፍ ህግ የተከለከለ ምሶሶ የሚያህል ወንጀል ዐይኑ እያየ ዝም ይላል። ኢሰመኮ ተአማኒነት ያሳጣ ግብር።
ኢሰመኮ የስታትስቲክስ ማካመቻ ኮሮጆ እንጅ መሰረታዊ የሰብዐዊ መብት ኮሚሽን አይደለም። የጎሳ ፌደረሼን እና ፓርቲ የወንጀል መፈልፈያ ማሽን በመሆናቸው የሞት፤የስደት፤ የእስራት እና ስቃይ ሶቆቃ ቁጥር በየቀኑ ይፈላል። ኢሰመኮ ይህን ቁጥር ይሰበስባል ግን የሚፈለፍለውን ማሽን ተሰብሮ ከአገልግሎት ውጭ እንድ ሆን የሰቆቃ ስታትሲትክስ መሰብሰብ ስራው እንድያቆም ሰርቶ አያውቅም። እምባ በባልዲ የሚያልብ ድርጅት ነው። ይህ ምን ይሰራል። ኢሰመኮ ለእራሱ እንጅ ለኢትዮጵያዊያን የቆመ ድርጅት እንዳልሆነ አድርጎ ይገልጻል። የዚህ ድርጅት ህልውና ለUN እንድቀጥል - ኢትዮጵያዊያን በጎሳ ክልል ግፊት በየዕለቱ ማልቀስ እና መሞት አለባቸው። ያሳዝናል ድርጅት ግብዝ ሲሆን።