Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቦዠ የጉራጌ ጥንታዊ የብርሃን አምላክ ነው! ዛሬ የሚከበረው በመስቀል እሳት ሲሆን ባስፈሪነቱ የሚገለጸው በብራቅ (መብረቅ) ነው

Post by Horus » 29 Jun 2022, 22:35

ይህ ትረካ ስለ ቦዠ ነው ! ቦዠ ብርሃን ማለት ሲሆን ወዥ ማለት ማየት፣ በብርሃን ወስጥ መሆን ማለት ነው። የትረካው ረዕስ 'ቦዠ ሸከተም (ሺከተም) ማለት የቦዠ ስራ፣ የቦዠ ፍጥረት ማለት ነው ። ሽካ ጥበብ፣ ክህሎት ማለት ሲሆን ወሸክት መሸከት ማለት መፍጠር፣ አንድን ነገር መገንባት፣ ህልው ማድረግ ማለት ነው። ለምሳሌ የእጅ ሰራ ውጤቶች ሁሉ ሸከት ይባላሉ ። በአማራኛ ሸቀጥ የተባለው ማለት ነው! ያ ዛሬ የተዋበ ነገር ሁሉ ሸጋ ይባላል። የሴ ልጅ ውበትም የምናቆላፕሰው ሸጋ ሸጉሌ ብለን ነው! በጉራጌኛ የሸማኔ ጥበብ መሳሪያዎች በጥቅል ሸጋ ተብለው ይጠራሉ !