Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ይህ እጅግ አስደናቂ ፕሮግራም ነው! የጉራጌኛ ቋንቋ ዲያሌክቶች ሁሉ አንድ እየሆኑ ነው!

Post by Horus » 27 Jun 2022, 00:16

አምደ ገብራኤል በሰባት ቤት ሲናገር ክስታኔው ያሬድ ስለሚገባው መልሱን በስታኔኛ ይመልሳል! ያ ደሞ ክስታኔኛው ስለሚገባው መልሱን በሰባት ቤት ይመልሳል! እጹብ ድንቅ ! ግን ክስታኔኛ ተናጋሪው የከተማ ሰው ስለሆነ በጣም ተራ የሆኑ የክስታኔኛ ስህተቶችን ይሰራል ። ለምሳሌ 'አንደኛ' ይላል 'ቃሉ ግን 'አትለኛ' ነው ። 'ተነጋግረን' ያላል ቃሉ ግን አንዱ 'አወረርነም ' ወይም ተመካክረን ለማለት 'ተቱጋገትነም ' ነው። ጥሩ ሙከራ ነው ። ቀስ በቀስ ይጠራል !!

ለምሳሌ እኔ አፈ የፈታሁት በክስታኔኛ ነው ። ነገር ግን ሙሉ በሙል በሚባል ድረጃ መስቃንኛ እሰማለሁ፣ ይገባኛል ። ቢያንስ 6 ወር እንኳ ቡታጀራ ብኖር በመስቃንኛ መመለስ እችላለሁ ማለት ነው ። ማለትም በአጭር ግዜ ውስጥ አንድ ግዙፍ ጉራጌኛ ቋንቋ ማደጉ አያጠራጥም ።

Last edited by Horus on 27 Jun 2022, 00:54, edited 1 time in total.



Horus
Senior Member+
Posts: 30653
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይህ እጅግ አስደናቂ ፕሮግራም ነው! የጉራጌኛ ቋንቋ ዲያሌክቶች ሁሉ አንድ እየሆኑ ነው!

Post by Horus » 27 Jun 2022, 02:10

TesfaNews,
Thank you. It has been a long time since I listened him. He is very creative and multilingual. He also paints and avid horse rider.
Yeditna ዬዲታና ማለት የኔ ነች ማለት ነው። እጮኛውን አገር ቤት ወስዶ ሲያስተዋውቅ ነው ።




Post Reply