Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
tarik
Senior Member+
Posts: 33102
Joined: 26 Feb 2016, 13:04

ኣሸባሪ-ህወሓት የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብ የትግራይ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ጠየቁ!!! WEEY GUUD !!!

Post by tarik » 26 Jun 2022, 11:22

ህወሓት የትግራይ ህዝብ ብቸኛው ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብ የትግራይ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ጠየቁ

ህወሓት የትግራይን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል ብለው እንደማያምኑም ነው ፓርቲዎቹ የገለጹት
አል-ዐይን2022/6/26 11:59 GMT

ሳልሳዊ ወያነ፣ ነፃነት ትግራይ እና ባይቶና በድርድሩ ህወሓት ብቸኛው የትግራይ ተወካይ ሆኖ እንዳይርብ ጠይቀዋል

ከፌዴራል መንግስቱ ጋር እንደሚደረግ በሚታሰበው ድርድር ህወሓት የትግራይ ህዝብ ወካይ ሆኖ በድርድሩ እንዳይቀርብ የትግራይ ተቃዋሚ ፖርቲዎች ጠየቁ፡፡

ፓርቲዎቹ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሓት የትግራይን ሕዝብ እንደማይወክል አሳስበዋል።

ሳልሳዊ ወያነ፣ ነፃነት ትግራይ እና ባይቶና የተባሉት ፓርቲዎች ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ በፃፉት ደብዳቤ ህወሓት በድርድሩ የትግራይን ሕዝብ ሊወክል እንደማይችል ገልጸዋል።

ግጭቱ በሰላም እንዲፈታ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅ ነው ያሉት ፓርቲዎቹ ቢሆንም ህወሓት የትግራይ ህዝብ ብቸኛ ተወካይ እንዳልሆነና እንዳይሆን ሊታወቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

ሶስቱም ፓርቲዎች በፃፉት ደብዳቤ ድርጅቱ በትግራይ ሕዝብ ዘንድ ሕጋዊ ውክልና እንደሌለው ገልፀዋል።

ድርድሩን በመልካም ጎን እንቀበላለን ቢሉም ህወሓት የትግራይ ሕዝብ ወካይ ሆኖ የቀረበበትን መንገድ ግን እንደማይቀበሉት ነው ፓርቲዎቹ ያስታወቁት።

ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ህወሓት የትግራይን ህዝብ ጥቅም ያስከብራል ብለው እንደማያምኑም አስታውቀዋል ፓርቲዎቹ፡፡

ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገዶች እልባት ለመስጠት ባለመቻሉ ምክንያት በሽብርተኝነት የተፈረጀው ህወሓት ከፌዴራል መንግስቱ ጋር ጦርነት መግጠሙ የሚታወቅ ነው፡፡

ህወሓ የትግራይን ህዝብ "የሃሰት ፕሮፖጋንዳው መሳሪያ ከማድረግ ውጪ ሌላ ዓላማ የለውም" ሲል የወቀሰው የፌዴራል መንግስት ሰብዓዊ እርዳታዎች እንዳይደርሱ በረራዎችን ከልክሏል ሲል ከሰሞኑ መክሰሱ የሚታወስ ነው፡፡

የመቀሌ አውሮፕላን ማረፊያ በነዳጅ እጥረት ምክንያት አገልግሎት እንዳቆመ ያስታወቀው ህወሓት "መንግስት በኦሮሚያ፣ በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በሌሎችም ቦታዎች የተደረጉ ግድያዎችን አጀንዳ ለማስቀየር" ያደረገው ነው በሚል ክሱን ማስተባበሉም አይዘነጋም፡፡