Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Obviously, አብይ አህመድ አገር በስርአት መምራት አልቻለም። መክሸፍ እንደ አብይ is loading.:- Teklemichael Abbebe Sahlemariam

Post by Wedi » 26 Jun 2022, 09:31

Obviously, አብይ አህመድ አገር በስርአት መምራት አልቻለም። መክሸፍ እንደ አብይ is loading.

Teklemichael Abbebe Sahlemariam
·
Obviously, አብይ አገር በስርአት መምራት አልቻለም። ከሰኔ 2013 በፊት በነበሩት 3 አመታት: ሽግግር ላይ ነበር: ሙሉ ስልጣን ወይም legitimacy አልነበረውም እንበል። ከሰኔው ምርጫ በኋላ ግን ምን ሰበብ አለው? ከጥቅምት 2014 ጀምሮ: ብልጽግና 95 ከመቶ የሚሆነውን የክልልም የፌደራልም ምክርቤቶች ወንበር ያዘ። ኢሕአዴግ እንኳን በዘመኑ: ከአጋር ድርጅቶች ጋር ሆኖ እንጂ: በራሱ ለብቻው: ይሄን ያሕል ወንበር ይዞ አያውቅም። ይሄንን ያሕል ስልጣን ተቆጣጥሮ: እንኳንስ ሕግ ማስከበር: አስፈላጊ ሆኖ ከቸገኘ: ሕገ መንግስት ማሻሻል እየተቻለ: የአብይ አሕመድ: ስራውን በአግባቡ አለመስራት: አንድም ስራውን አለማወቅ: አለያም ንቀት ነው: ሌላም የችሎታ ማነስ: ወይም እብሪት: ወይም በራስ ወዳድነት መጠመድና የሌሎችን ሕመም አለመረዳት: ወይም ምን እንበለው? አብይ ከ95 ከመቶ በላይ ወንበር ይዞ: ይሄ ሁሉ ወንጀል ሲፈፀም: በችግኝ ማፍላት መጠመዱ: ደም ያፈላል። የሰውዬውን ደሕንነትም እንድንጠራጠር ያደርጋል። ወዳጄ Esayas Teshome እንዳለው: Crisis management ላይ: የፌደራሉም የክልሉም መንግስታት: ዜሮ ናቸው። የኦሮሚያ መንግስት ከከሸፈ ቆየ። መክሸፍ እንደ አብይ is loading.


https://www.shorturl.at/giuAC