Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Y3n3g3s3w » 24 Jun 2022, 13:22

Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do እነሱ እንዲጠመድባቸው ያዘጋጁለትን ወጥመድ ወደ ጎን ገሸሸ አርጎ በራሱ መንገድ እየገሰገሰ ነው

የውጮቹ የአብይ መንግስት ምነድነው እንዲያደርግ የሚፈልጉት?

እድገት የሚባ ነገር እርግፍ አርጎ ትቶ በወያኔና ሸኔ ተጠምዶ በዚህም የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ሀገሪቷ ከኢኮኖሚ ጥገኝነቷ እንዳታፈተልክ ነው:: ለዚህም ነው በግልፅ እነዚህን ሀይሎች ሳያሰልሱ እየረዱ ያሉተ simple as that! ከዛም ይሄንን መንግስት በአመፅ፣ በተለያዩ ፖለቲካ ጫናዎችና እክል በመፍጠር ገዝግዞ መጣል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ተመሳሳይ መንግስት ተመልሶ እንዳይከሰት ማረግ ነው

የአብይ መንግስት ምን እየሰራ ነው?

በከፍተኛው የህዝብ ጫና(የወጭና የውስጥ) ውስጥ ሆኖ ባልተለመደ የኢትዮጵያውያን ልማድ በተግስት ፣ በብልሃትና በውቀት እየተመራ የውጮቹን የሴራ አካሄድ ቀስበቀስ እያከሸፈ ከነጮቹ ፍላጎትና ምኞት በተቃራኒ ድል እያረጋቸው ነው:: በዚህ መሀል ግን በራሳችን ዜጎች የራሳችንን ዜጎች እየጨረሱብን /እያሰጨረሱብን መሆኑ በጣም ቢያሳዝንም በመንግስት በኩል እየተወሰደ ያለው የተጠና ስልት ግን ሊያስወቅሰው አይገባም:: ይልቁንም ህዝብ ከመንግስት ጋር ሆኖ ይህን ሴራ ማሽመድመድ አለበት!
የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጣባውና ከኖረበት ሺ ዐመታት ችግር ለመላቀቅ ከፈለገ አንድና አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለው ! ያብይን መንግስት ማገዝ! ያለበለዚያ ዝም ብሎ ከወያኔ/ሸኔና ከውጭዎቹ ጋር አብሮ የሚያጨበጭብ ከሆነ የራስን መቃብር ከጠላት ጋር ሆኖ እንደመቆፈር ይቆጠራል :: ይሄ መንግስ ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያዊነትን የሚዋጋ መንግስት አደለም ስለዚ የአማራ ህዝብም ሆነ የኦሮሞ ወይም ሌሎቹ ኢትዮጵያን የምንል ብሄር ብሄረሰቦች ይሄንን መንግስት ማገዝ እንጂ መታገል የለብንም የአብይ መንግስት ልክ እንደ አባገቶቸችን የኢትዮጵያንን የታመቀ አቅም፣ብልህነትና የነፃነት ፍቅር ቁልጭ አድርጎ በተላይ ደሞ ለውጭዎቹ ጠላቶቻችን አሳይቷቸዋል:: ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህ ማለት አሁን በተለይ የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆን በማያሻማ ሁኔታ ተረድተዋል እናም የቻሉትን በቻሉት ነገር ሁሉ ተጠቅመው ተረባርበው ማሰናከል ይፈልጋሉ እየጣሩም ነው ይሄንን በተለይ ባለፋት አራት አመታት መገንዘብ ያልቻለ ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ ላይ ነው ያለው ቢባል ማጋነን አይሆንም ይሄ ባይሆንማ ለምንድነው አማራው ላይ ሀገሬ ስላለ በተለየ መልኩ ኢላማ የተደረገው? ለምንድነው አብይና ኢትዮጵያን ያሉ የኦሮሞ ልጆች መንግስት ትደግፋላቹ እየተባሉ የሚዘለፉትና የሚገደሉት ? ጎበዝ ኢትዮጵያውያ ከመንግስት ጋር አብረን እነዚህን የውጭና የውስጥ ተላላኪዎች መታገል ብቻ ሳይሆን ተባብረን ካላሸነፍናቸው የውጭዎቹ እሰከዛሬ ያለተቀናቃኝ ሲያገኙት የነበረውን ዘርፈብዙ ጥቅም ላለማጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ምናልባትም እሰከዛሬ ድረስ አይተን የማናቀውን ክስተት ሊፈጥሩብን ይሞክራሉ ፣በዘህም ሌላ ብዙ ጥፋ ሊከተል ይችላል::

TheManWhoSawTomorrow

Abere
Senior Member
Posts: 10892
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Abere » 24 Jun 2022, 13:46

እትፍ! እትፍ! እትፍ! ስንት ሃፍረት ጌጡ ያደረገ ሰው በዚህ ምድር አለ?!

እነ ሀፍረት ሃብቱ- እነ ነውር ጌጡ፤
ፅንስ ይበላሉ -ከሆድ እያወጡ፤

ዐደባባይ ወጥተው ጮቤ እየረገጡ፤
ዐብያችን አሉን በሰው ሲያላግጡ።

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Sam Ebalalehu » 24 Jun 2022, 14:25

TheManWhoSawTommorow, I agree Abiy shouldn’t follow the path his detractors charted to him. He should focus on his main goal. But that doesn’t excuse his lack of imagination in anticipating what was to come. The other day several PP politicians, including Abiy himself, suggested those who did the killing took order from those who are hellbent to dismember Ethiopia. One shouldn’t be a rocket scientist to figure out who the order givers are. That begs the question if the government knew such a mortal enemy exists how come it had not been prepared for it.
At this time one expects the domestic enemy of Ethiopia to be in disarray, to be in their last gasp for survival, not in position to kill hundreds of innocent Ethiopians. This is inexcusable.
Last edited by Sam Ebalalehu on 24 Jun 2022, 14:31, edited 1 time in total.

Right
Member
Posts: 2725
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Right » 24 Jun 2022, 14:31

Crap.
The baby king has no a clue on what he is doing.
He is where the Weyannies want him to be. He is a dead man walking. Killing children, women and the elderly is a deadly trap he will never escape.

union
Member+
Posts: 6046
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by union » 24 Jun 2022, 14:34

Witaf neqay horus :lol:

[ quote=Y3n3g3s3w post_id=1304817 time=1656091375 user_id=47294]
Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do እነሱ እንዲጠመድባቸው ያዘጋጁለትን ወጥመድ ወደ ጎን ገሸሸ አርጎ በራሱ መንገድ እየገሰገሰ ነው

የውጮቹ የአብይ መንግስት ምነድነው እንዲያደርግ የሚፈልጉት?

እድገት የሚባ ነገር እርግፍ አርጎ ትቶ በወያኔና ሸኔ ተጠምዶ በዚህም የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ሀገሪቷ ከኢኮኖሚ ጥገኝነቷ እንዳታፈተልክ ነው:: ለዚህም ነው በግልፅ እነዚህን ሀይሎች ሳያሰልሱ እየረዱ ያሉተ simple as that! ከዛም ይሄንን መንግስት በአመፅ፣ በተለያዩ ፖለቲካ ጫናዎችና እክል በመፍጠር ገዝግዞ መጣል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ተመሳሳይ መንግስት ተመልሶ እንዳይከሰት ማረግ ነው

የአብይ መንግስት ምን እየሰራ ነው?

በከፍተኛው የህዝብ ጫና(የወጭና የውስጥ) ውስጥ ሆኖ ባልተለመደ የኢትዮጵያውያን ልማድ በተግስት ፣ በብልሃትና በውቀት እየተመራ የውጮቹን የሴራ አካሄድ ቀስበቀስ እያከሸፈ ከነጮቹ ፍላጎትና ምኞት በተቃራኒ ድል እያረጋቸው ነው:: በዚህ መሀል ግን በራሳችን ዜጎች የራሳችንን ዜጎች እየጨረሱብን /እያሰጨረሱብን መሆኑ በጣም ቢያሳዝንም በመንግስት በኩል እየተወሰደ ያለው የተጠና ስልት ግን ሊያስወቅሰው አይገባም:: ይልቁንም ህዝብ ከመንግስት ጋር ሆኖ ይህን ሴራ ማሽመድመድ አለበት!
የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጣባውና ከኖረበት ሺ ዐመታት ችግር ለመላቀቅ ከፈለገ አንድና አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለው ! ያብይን መንግስት ማገዝ! ያለበለዚያ ዝም ብሎ ከወያኔ/ሸኔና ከውጭዎቹ ጋር አብሮ የሚያጨበጭብ ከሆነ የራስን መቃብር ከጠላት ጋር ሆኖ እንደመቆፈር ይቆጠራል :: ይሄ መንግስ ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያዊነትን የሚዋጋ መንግስት አደለም ስለዚ የአማራ ህዝብም ሆነ የኦሮሞ ወይም ሌሎቹ ኢትዮጵያን የምንል ብሄር ብሄረሰቦች ይሄንን መንግስት ማገዝ እንጂ መታገል የለብንም የአብይ መንግስት ልክ እንደ አባገቶቸችን የኢትዮጵያንን የታመቀ አቅም፣ብልህነትና የነፃነት ፍቅር ቁልጭ አድርጎ በተላይ ደሞ ለውጭዎቹ ጠላቶቻችን አሳይቷቸዋል:: ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህ ማለት አሁን በተለይ የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆን በማያሻማ ሁኔታ ተረድተዋል እናም የቻሉትን በቻሉት ነገር ሁሉ ተጠቅመው ተረባርበው ማሰናከል ይፈልጋሉ እየጣሩም ነው ይሄንን በተለይ ባለፋት አራት አመታት መገንዘብ ያልቻለ ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ ላይ ነው ያለው ቢባል ማጋነን አይሆንም ይሄ ባይሆንማ ለምንድነው አማራው ላይ ሀገሬ ስላለ በተለየ መልኩ ኢላማ የተደረገው? ለምንድነው አብይና ኢትዮጵያን ያሉ የኦሮሞ ልጆች መንግስት ትደግፋላቹ እየተባሉ የሚዘለፉትና የሚገደሉት ? ጎበዝ ኢትዮጵያውያ ከመንግስት ጋር አብረን እነዚህን የውጭና የውስጥ ተላላኪዎች መታገል ብቻ ሳይሆን ተባብረን ካላሸነፍናቸው የውጭዎቹ እሰከዛሬ ያለተቀናቃኝ ሲያገኙት የነበረውን ዘርፈብዙ ጥቅም ላለማጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ምናልባትም እሰከዛሬ ድረስ አይተን የማናቀውን ክስተት ሊፈጥሩብን ይሞክራሉ ፣በዘህም ሌላ ብዙ ጥፋ ሊከተል ይችላል::

TheManWhoSawTomorrow
[/quote]

Horus
Senior Member+
Posts: 30655
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Horus » 24 Jun 2022, 15:04

የነገሰው፣
ተሳስተሃል። ወደ ኋላ ተመልሰው ሶሺያል ሂስትሪ ተመልከት ። አንተ በምትለው ልክ ሕዝቡን የማያዳምጥ መሪና መንግስት ይወድቃል ። አው አንድ መሪ እንደ ጭራ የህዝብ ስሜት መከተል የለበትም ። ግን ኮሌክቲቭ ዊዝደም የሚባል ግዜ የማይሽረው ሃቅ አለ። የብዙ ሕዝብ ግምታና ስሜት ከጥቂት ሰዎች እውቀትና ቲኦሪ የላቀ ብቻ አይደለም፣ ሁል ግዜ የሚሆነው ያ ኮሌክቲቭ ዊዝደም ነው ።

አንድ ነገር መነሻ አለው ። ያ ነገር መድረሻ አለው ። በመካከሉ ሂደት (ተግባር) እና መንገድ (ዘዴ) አሉ ። መነሻ የሌለው ሰው የትም አይሄድም። አቢይ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካ መነሻ ያለውን ረስቶ አሁን የኢትዮጵያ ጉዞ መነሻ የብሄር ጥያቄ አድርጎታል። ስህተት #1 ያ ነው ።

አንድ ሰው ጉዞ ሲጀምር መድረሻው፣ የሚሄድበት ቦታ የት እንደ ሆነ ካላወቀ መንገዱ የቱ እንደ ሆነ አያውቅም። ስለዚህ ያ ሰው መንገደኛ ነው ለማለት አይቻልም ። መንገድ የጠፋው ሰው ይባላል። የአቢይ ስህተት #2 ያ ነው ። መድረሻው ኢትዮጵያ ሳይሆን የሆነ የጎሳ ህልም ነው ።

አንድ ሰው መነሻ ኖሮት፣ በድረሻውን የሚያውቅ ሆኖ እንኳ መንገዱን (ዘዴውን) ማወቅ አለበት ። ምራብ ጎጃም አዊ ለመሄድ ያሰበ ሰው አፋር የሚሄደውን አቶቢስ አይሳፈርም ። ማለትም ጉዞ (ሂደት) እና መንገድ (ዘዴ) የአንድ ሳንቲም ዘውድና ጎፈር ናቸው ። መንገድህ ከተሳሳተ ያንተ ጉዞ (ያቢይ ብልጽግና ጉዞ) ወደ አፋር የሚነጉደው የአዊ ጎጃሜ ማለት ነው ።

የጎሳ መንገድ እየገሰገስክ የኢትዮጵያ መድረሻ አትደርስም ። ይህ የአቢይ አህመድ እጅግ ግዙፍ እና የውድቀቱ ሁሉ መሰረት ነው።

ሌላው ስህተተ የተለመደው የገዥ መደቦች ተረት ነው ። እሱም ስልጣናቸው አደጋ ላይ በወደቀ ቁጥር የውጭ ጠላት የሚሉት ነገር አለ። ይህ ውሸት ነው ። አሜሪካን አቢይን ለመጣል ሲሰሩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ባንድ ተንሰቶ ያ ለኢትዮጵያዊያን አይሰራም ! ኢትዮፕያዊያን መንግስታቸው ከማንኛውም የውጭ ጠላት ይጠብቃሉ ፣ ያ መንግስት ሕዝብ ሲያስከፋ ተነስተው ይጥሉታል። አቢይ ይህን የኢትዮጵያ ሳይኮሎጂ ገና ካልገባው መሪ መሆን አይገባውም።

አገር ጠባቂ ሕዝብ ነው ። መንግስት ጠባቂ ሕዝብ ነው ፣ ታሪክ ሰሪ ሕዝብ ነው ።

የውስጥ ጠላት ያልከውም ስህተት ነው። ሸኔ የሚባል ያገር ውስጥ ጠላት ካለ አቢይ አማራ ኦሮሞ ሳይል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወለጋ አይደለም እንጦሬጦስ ድረስ ዘምተው እንዲያጠፉት አዋጅ ያውጃል እንጂ የሸኔ ዘር አጥፊ ኦሮሞ ስለሆነ ቀሚሴን ማቄን የሚለው አቢይ የጎሳ መሪ እንጂ የኢትዮጵያ መሪ እንዳልሆነ ገሃድ አድርጎታል ።

ስለዚህ አቢይ አህመንድ በፎቆችና ግድቦች ሸፋፍኖ ለያሰፍን ያሰበው የዘር አምባገነነት ከወዲሁ ተጋልጦ መክሸፍ አለበት ። ለፎቅና ፋፍሪካ ከሆነ ቀድሞስ የትግሬ ሌባ ከበርቴ ገምብቶ ነበርኮ ። ዛሬ በኦሮሞ ሌባ ከበርቴ ቢተካ ለተራው ሰው ምን ፋይዳል አለው ?

እኔ አቢይን በግል የምሰድብ፣ እናቱን የምሰድብ ሰው አይደለሁም ። አቢይ የትግሬ ወያኔ ያጨማለቀውን ቂጣ ነው ወደ ኦሮሞ መር ቂጣ ለመለወጥ ላይ ታች የሚለው ።

ቴዲ አፍሮ ጨረሰው ነገሩን! አንድ ሰው አንድ ነው ! አንዴ የኦሮሞ ዘውጌ፣ አንዴ የኢትዮጵያ ዜጋ መሆን አይቻልም! ሁለት እግር ስላለን ባንድ ግዜ ሁለት ዛፍ አንወጣም!! ያቢይ ስህተት በዚህ ደረጃ ያለ መሰረታዊ ድክመት ነው። አቢይ አህመድ አሊ ወይ የጎሳ ፖለቲካኛ ነው! ወይ የዜጋ ፖለቲከኛ ነው ! በቃ !!!

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9761
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by DefendTheTruth » 24 Jun 2022, 16:23

Sam Ebalalehu wrote:
24 Jun 2022, 14:25
TheManWhoSawTommorow, I agree Abiy shouldn’t follow the path his detractors charted to him. He should focus on his main goal. But that doesn’t excuse his lack of imagination in anticipating what was to come. The other day several PP politicians, including Abiy himself, suggested those who did the killing took order from those who are hellbent to dismember Ethiopia. One shouldn’t be a rocket scientist to figure out who the order givers are. That begs the question if the government knew such a mortal enemy exists how come it had not been prepared for it.
At this time one expects the domestic enemy of Ethiopia to be in disarray, to be in their last gasp for survival, not in position to kill hundreds of innocent Ethiopians. This is inexcusable.
Well, if someone is still unconscious or act as unconscious of what yenegesew said here then that someone is either in a deep sleep or purposely cooperating with the arch enemy of the nation, at the cost of our future. The current situation is not business as usual, without any sort of exaggeration.

Ethiopia is at a cross-road right at this time, it is the time when Ethiopia will take off or crumble itself, never to rise again. The adversary is simply too big.

She is no more abiding herself with the "norm" prescribed for all the so called developing countries of the world, especially the African ones.

If the "norm" is broken, then you can imagine what is at stake, the fight is over the "norm", it has nothing or little to do with Ethiopia as such.

Having said that, Sam, with all due respect, how on earth should and could the government (this or any other) protect every inch of the country of over 100 million sq. km, when you say the government failed to prepare itself?

There are many people paying in their lives to protect Ethiopia's future, every passing day. Sometimes they face desparate enemy that wouldn't look back from taking a desparate and last attempt measure. The recent attack in Wollega is such a case.

These and many other innocent citizens of ours are paying in their precious lives for the future of Ethiopia, it is the prise that we should pay to safeguard Ethiopia's future, in my view. And we should be prepared for it!

Our enemies will never sleep, so should we too, if we mean we have something precious to care for: our future.

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Sam Ebalalehu » 24 Jun 2022, 17:22

DTT I understand to protect every inch of the country might be a problem. That is exactly the reason the government should have gone all the way to neutralize the enemy.
DTT, if we accept your premise we come to a conclusion it is ok for some Ethiopians to die because the government cannot control every inch of the country. In fact, just yesterday a TPLF cadre was spewing that theory here in ER in artful form.
When there is a domestic enemy which works tirelessly to create havoc in the country, the government should act with the same vigor against the enemy.
I understand the Abiy PP members are not sharing the same political doctrine. There are still some who are working against the government from within. I understand that. But no matter Innocent Ethiopians dying in mass constantly shouldn’t become a new culture.
Always keeping citizens safe is the responsibility of any government. The Abiy government would not be an exception.

Right
Member
Posts: 2725
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Right » 24 Jun 2022, 18:36

DTT just read and re-read the analysis of Horror above and you will get your answers. In summary, Ethnic politics will eat Abiye Ahmed alive. In a civilized nation like Ethiopia, with fully mechanized Defense force and a network of security aparatus, how come this group called SHENE massacre citizens like this? And they are doing whenever and wherever they want.

Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Y3n3g3s3w » 24 Jun 2022, 19:59

ሰሞን መቼም እንደ አበረ በይነ-መረቡን የተቆጣጠረው ና አስረሽ ምቺው የሆነለት አንድም ሰው አላየሁም :: ባማራ ደም አንተ የአዞ እንባ ታነባለህ ትጨፍራለህ ግን ምንም አታመጣ
ም በመጨረሻም ኢትዮጵያ ታሸንፋችኀለች!

Abere wrote:
24 Jun 2022, 13:46
እትፍ! እትፍ! እትፍ! ስንት ሃፍረት ጌጡ ያደረገ ሰው በዚህ ምድር አለ?!

እነ ሀፍረት ሃብቱ- እነ ነውር ጌጡ፤
ፅንስ ይበላሉ -ከሆድ እያወጡ፤

ዐደባባይ ወጥተው ጮቤ እየረገጡ፤
ዐብያችን አሉን በሰው ሲያላግጡ።

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by TGAA » 24 Jun 2022, 20:32

Y3n3g3s3w wrote:
24 Jun 2022, 13:22
Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do እነሱ እንዲጠመድባቸው ያዘጋጁለትን ወጥመድ ወደ ጎን ገሸሸ አርጎ በራሱ መንገድ እየገሰገሰ ነው

የውጮቹ የአብይ መንግስት ምነድነው እንዲያደርግ የሚፈልጉት?

እድገት የሚባ ነገር እርግፍ አርጎ ትቶ በወያኔና ሸኔ ተጠምዶ በዚህም የረጅም ጊዜ እቅዳቸው ሀገሪቷ ከኢኮኖሚ ጥገኝነቷ እንዳታፈተልክ ነው:: ለዚህም ነው በግልፅ እነዚህን ሀይሎች ሳያሰልሱ እየረዱ ያሉተ simple as that! ከዛም ይሄንን መንግስት በአመፅ፣ በተለያዩ ፖለቲካ ጫናዎችና እክል በመፍጠር ገዝግዞ መጣል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ተመሳሳይ መንግስት ተመልሶ እንዳይከሰት ማረግ ቅነው

የአብይ መንግስት ምን እየሰራ ነው?

በከፍተኛው የህዝብ ጫና(የወጭና የውስጥ) ውስጥ ሆኖ ባልተለመደ የኢትዮጵያውያን ልማድ በተግስት ፣ በብልሃትና በውቀት እየተመራ የውጮቹን የሴራ አካሄድ ቀስበቀስ እያከሸፈ ከነጮቹ ፍላጎትና ምኞት በተቃራኒ ድል እያረጋቸው ነው:: በዚህ መሀል ግን በራሳችን ዜጎች የራሳችንን ዜጎች እየጨረሱብን /እያሰጨረሱብን መሆኑ በጣም ቢያሳዝንም በመንግስት በኩል እየተወሰደ ያለው የተጠና ስልት ግን ሊያስወቅሰው አይገባም:: ይልቁንም ህዝብ ከመንግስት ጋር ሆኖ ይህን ሴራ ማሽመድመድ አለበት!
የኢትዮጵያ ህዝብ ከተጣባውና ከኖረበት ሺ ዐመታት ችግር ለመላቀቅ ከፈለገ አንድና አንድ ምርጫ ብቻ ነው ያለው ! ያብይን መንግስት ማገዝ! ያለበለዚያ ዝም ብሎ ከወያኔ/ሸኔና ከውጭዎቹ ጋር አብሮ የሚያጨበጭብ ከሆነ የራስን መቃብር ከጠላት ጋር ሆኖ እንደመቆፈር ይቆጠራል :: ይሄ መንግስ ኢትዮጵያውያንንና ኢትዮጵያዊነትን የሚዋጋ መንግስት አደለም ስለዚ የአማራ ህዝብም ሆነ የኦሮሞ ወይም ሌሎቹ ኢትዮጵያን የምንል ብሄር ብሄረሰቦች ይሄንን መንግስት ማገዝ እንጂ መታገል የለብንም የአብይ መንግስት ልክ እንደ አባገቶቸችን የኢትዮጵያንን የታመቀ አቅም፣ብልህነትና የነፃነት ፍቅር ቁልጭ አድርጎ በተላይ ደሞ ለውጭዎቹ ጠላቶቻችን አሳይቷቸዋል:: ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? ይህ ማለት አሁን በተለይ የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆን በማያሻማ ሁኔታ ተረድተዋል እናም የቻሉትን በቻሉት ነገር ሁሉ ተጠቅመው ተረባርበው ማሰናከል ይፈልጋሉ እየጣሩም ነው ይሄንን በተለይ ባለፋት አራት አመታት መገንዘብ ያልቻለ ኢትዮጵያዊ እንቅልፍ ላይ ነው ያለው ቢባል ማጋነን አይሆንም ይሄ ባይሆንማ ለምንድነው አማራው ላይ ሀገሬ ስላለ በተለየ መልኩ ኢላማ የተደረገው? ለምንድነው አብይና ኢትዮጵያን ያሉ የኦሮሞ ልጆች መንግስት ትደግፋላቹ እየተባሉ የሚዘለፉትና የሚገደሉት ? ጎበዝ ኢትዮጵያውያ ከመንግስት ጋር አብረን እነዚህን የውጭና የውስጥ ተላላኪዎች መታገል ብቻ ሳይሆን ተባብረን ካላሸነፍናቸው የውጭዎቹ እሰከዛሬ ያለተቀናቃኝ ሲያገኙት የነበረውን ዘርፈብዙ ጥቅም ላለማጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ምናልባትም እሰከዛሬ ድረስ አይተን የማናቀውን ክስተት ሊፈጥሩብን ይሞክራሉ ፣በዘህም ሌላ ብዙ ጥፋ ሊከተል ይችላል::

TheManWhoSawTomorrow
ይህንን የድኩም ፕሮፓጋንዳ እንደ ብልህ የፖለቲካ ስትራቴጂ አድርጎ ማቅረብ አንድም የኢትዮጵያን ህዝብ ዘመናት ያለፈ ብልህነት መናቅ ነው ፤ ወይንም የአብይ ላይ ያለህ እምነት ወደ አምልኮ ተቀይሯል ማለት ነው፡፡ መጀመርያ የውጭ ጠላቶችህን መዋጋት የምትችለው ህዝብህን ለጠላት ጥቃት አጋልጠህ ስይሆን ህዝብህን ይዘህ የውጭ ጫናን መቋቋም ስትችል ነው ፤ ህዝብ በየቀኑ እየታረደ ግድ የለም ታረዱ ነገ የገብስ ዘላላ መስካችሁን ይሞላል ማለት ምን ማለት ነው፤ ሰብሉ ለሰው ነው እንጂ የሰው ህይወት ለሰብል ሲባል አይጠፋም ወይም መጥፋት የለበትም ፤ የሰው ሀይወት ክቡር ነው !ሁለተኛ ለአብይ የኢትዮጵያ ሀዝብ በተደጋገመ ሁኔታ አብሮት ቆሞ መሰዋአትነት ከፍላል ፤ ነገር ግን አሁን ግልጽ የሆነ ነገር ቢሆን አብይ የኢትዮጵያን ብሄረሰቦች አንድ ላይ ሲያነሱ ከአጀንዳው ጋር ስለተጋጨበት ፍርሀቻ ውስጡ ጭሮበታል ፤ ስለዚህም ነው ህዝቡ ድሉን ሳያጣጥም ኢትዮጵያ መቀመቅ እንድትሄደ የቀይሱትን እነ ስብሀት ነጋን እግዚያብሄር ነግሮኝ ነው ብሎ የለቀቀቻው፤ በቅርብ በፓርላማ ባደረገው ንግግር አስመሳይ የኢትዮጵያ ካባውን አውልቆ ፊት ለፊት ጸረ ኢትዮጵያዊ አቋሙን ግልጽ አድርጎ እርቃኑን ቆሟል _ አሁን እንኳን በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሲታረዱ ፤ ፓርላማው አሸባሪ ብሎ የወሰናባቸውን ኦነግ ( ሸኔ ?) ኢመደበኛ ብሎ ፖለቲካ ሲቀምር እያየህው ነው ፤ እዚህ መጥተህ አብረነው ገድል እንግባ ትላለህ ፤ አብይ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ የዘፈነው ፤ የራሱን ሰዎች ቦታ እስከሚያስይዝ ነው ፤ አሁን ህዝብ ላይ ያለው ትእቢት የናረው ያንን አድርጌ ጨርሻለሁ ብሎ ነው፤ ይመስለው ይሆናል እንጂ የኢትዮጵያ ህዝብ የዚህን መሰሪ ተፈጥሮ አውቆ ተረድቶ ትፍቶታል ፤ ጊዜዊን ብቻ ነው የሚጠብቀው ፤ አንተ በደም ላይ ችግኝ ተከላውን የብልህ መንገድ አድርገህዋል ምክንያቱን አንተ አይደለሁም ወይም ቤተሰብህ በጨላማ የሚታረዱብህ ፤ ሆዳምነት እንደ እውቀት ከመናገር በስተቀር የአብይን ቁልቁለት ጉዞ አታተርፈውም ፤ አሳማን ሊፕሲቲክ ብትቀባ አሳማነቱን መቀየር አትችልም ፟ የፖለቲካ አጀንዳህ ምን እንደሆነ ግልጽ ነው እየስመጠ ያለ መርክብ ማትረፍ ፤ አምስትም አንድም አመት ይውሰድ መርከቡ መስመጡ አይቀርም ፤ ዋናው የኢትዮጵያዊያን ግብ መሆን ያለበት አብይ እራሱ ይዞ እንዲሰምጥ ማድረግ ነው ፤

Horus
Senior Member+
Posts: 30655
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Horus » 24 Jun 2022, 21:47

የኢትዮጵያ ችግርና መፍትሄ ለምን እንዲህ እንደ ሚከብዳችሁ እናንተ እንደ ማያውቅ ሁኑ እንጂ መልሱ እጅግ ቀላል ነው ። ከሞት ከተረፉት አንዲት ወጣት ሴት የተናገረችው ሙሉ መልሱን ይዞታል። እሷ የሚገድሉን እዚሁ ከኛ ጋር ያሉት ናቸው ። እኛን ገድለው መሬታችን ለመውሰድ ነው ያለችው።

እኔ እዚህ ፎረም ላይ በኢትዮጵያ የብሄር ጥያቄ የሚባል ነገር የለም። ሁሉም የመሬት ጥያቄ ነው ። መሬት የኢትዮጵያ ጎሳዎች መተላለቂያ የሆነው በአንድና አንድ ምክኛት ብቻ ነው ። እሱም እግዚአብሄር የፈጠረውን መሬት የሆነ ጎሳ በጉልበቱ የሰራው ይመስል የኢትዮጵያን መሬት በካርታና ድምበር ከፋፍሎ ይህ የትግሬ መሬት ነው፣ ይህ የኦሮሞ መሬት ነው። ይህ የጉሙዝ መሬት ነው ተብሎ የተከለለ ቀን ነው ባኢትዮጵያ የጎሳዎች እርስ በርስ አልቂት ታቅዶ የተበየነው ።

ስለዚህ ይህ አንዳችሁን እንዲፈርስ በማትጠይቁት የጎሳዎች የግል መሬት ክልል ሳቢያ ነው ኦሮሞው አማራውና ሌላው ጎሳን ከመሬቱ ለማጽዳት፣ የዘር ማጽዳት የሚያደርገው። ትግሬዎች መጀምሪያ መሬቱን ቀምተው ቀጥለው ያደረጉት ከትግሬ መሬት ለላውን የማጽዳት ነው። ኣዲስ አበባ አንድ ኢትዮጵያዊ ሰበታም ቡራዩ ገፈርሳ መኖር አይችልም ኦሮሞ ካልሆነ። ነገ ሌሎችም ጎሳዎች ተመሳሳይ ነው የሚያደርጉት ። ገና ይህ ሌላውን ከጎሳ የግል መሬት የማጽዳት ዘመቻ በያንዳንዱ ከተሞች ይካሄዳል ።

የጎሳ ከበርቴው መሬቱን ይፈልገዋል፣ ይሸጠዋል፣ ያከራየዋል፣ ይከብርበታል፣ አሁን ዘመናዊ እርሻ ገብቶለታል ያርሰዋል።

ስለዚህ እኔ አዝናለሁ እዚህ ፎረም ላይ ሙሉ ቀን ስትሳደቡና ስትንጫረሩ የምትውሉ ከኢትዮ360 ጀምሮ እስከ ተራ የፖለቲካ መሃይም እጅግ ታሳዝኑኛላችሁ! ምንም የምትፈይዱት ነገር የለም ። በኢትዮጵያ ለውጥ እንዲመጣ በእውነት የምትፈልጉ ካላቻችሁ ማድረግ ያለባችሁ አንድና አንድ ነገር ብቻ ነው።

በኢትዮጵያ የክልል መሬት ባለቤትነት ከጎሳ ወጥቶ፣ የጎሳ ድንበሮች ፈርሰው አዲስ የመሬት ስሪት እንዲበየን መታገል ነው ። የወለጋ አማራ ሲጨፈጨፍ የጎጃም አማራ ዘምቶ መከላከል ያቃተው በቆሻሻው ክልል ምክኛት ነው። ኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠብቅ ሃይል አላት ። ችግሩ የኢትዮጵያ መንግስት በትግሬና ኦነግ የተዋቀረው የኢትዮጵያ ሃይል ህዝብ እንዲጠብቅ ሳይሆን የጎሳ ድንበር እንዲያስከበር ነው።

እንዴት ይህን እጅግ ቀላልና ግልጽ ችግር ሊገባችሁ ተሳናችሁ ። በኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ መንግስት ቢኖር ድሮ ድሮ በየወለጋውና ሰቆጣው አማራ ሱማሌ ሳይባል ሁሉንም ህዝብ የሚጠብቅ ሰራዊት ይኖረን ነበር ። በኢትዮጵያ የኢትዮጵያ መንግስት የለም። ያለው የሱማሌ መንስት፣ የትግሬ መንግስት፣ የኦሮሞ መንግስት፣ ያማራ መንስት ነው ።

ይህን እጅግ ቀላልና ግልጽ ችግር መገንዘብ እንዴት ተሳናችሁ? ነገም ቢሆን ሺ ግዜ ብትንጫረር ግዜ ዉታፍ ከዳኝ ውታፍ ነቃይ እያልክ ብታላዝን የክልል ድምበር እስካለ ድረስ አንድም የምታድነው ዘር አይኖርም ።

ዘሬ እያለቀ ነው ብለህ ወለጋ ብትዘምት የሚሆነው የአማራና ኦሮሞ ጎሳዎች ረጅም የጎሳ ጦረነት ነው ። የሚሆነው ያማራና የኦሮሞ መንግስቶች ጦርነት ነው! በቃ!

በኢትዮጵያ የዘር እልቂት እንዲቆም ትፈልጋለህ? ክልል የተባለው የትግሬ ቂጣ ለማፍረስ ተደራጅ! ያኔ አይደለም ኢትዮጵያዊ ያለም ሕዝብ ከጎንህ ይቆማል! እንሳ ማነው ዉታፍ ነቃይ አላዋቂ ፖለቲከኛ መሳይ ስሜታም ሁሉ!

ጎሳዎች ሁሉ የሚተላለቁት አንዱ ያንዱን መሬት ለመቀማት ነው ። ላለፉት 1 ሺ አመታት የሆነው ይህ ነው ። ብዙ ጎሳዎች ከታሪክ ገጽ የጠፉት መሬታቸውን ለመቀማት ነው ። ይህን የኢትዮጵያ ታሪክ ሃ ሳይሉ ስለ ፖለቲካ የሚንጫረሩ ያሳዝኑኛል!

ያለው አንድ እና አንድ ችግር ነው! አንድ ጎሳ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሃብት የሆነው መሬትን የኔ የግል ንብረት ነው የሚለው ወያኔና ኦነግ ቂጣ ነው

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Selam/ » 24 Jun 2022, 22:34

ወቸው ጉድ!

- የፈላስፉው፣ የከሳሹና የዳኛው ብዛት። ያለምንም መረጃ አብይ ገዳይ ነው ስትሉ ትንሽ ሀፍረት ስርቅ አይላችሁም? በልቤ የወያኔ እንጅ እንዳለበት ባውቅ እንኳን፣ ጣት ለመቀሰሩ ጊዜ እየገዛሁ ፀጥ ለጥ ብያለሁ።

- እዚህ እስለጠነ ሀገር እንኳ፣ የህፃናትንና አዛውንትን የግፍ ጭፍጨፉ መከታተል መቆጣጠር መንግሥት ተስኖታል፣ ኋላ ቀሩ የኢትዮዽያ ደኅንትና ጦር ሰራዊት እንዴት አባክ አድርጎ ነው በየጢሻ የሚሽሎከሎክን አረመኔ የሚቆጣጠረው?

- አብይ ህገ መንግሥትና ክልል አፍርሶ፣ አንድ ያድርገን የምትል ጎበዝ፣ እስኪ መጀመሪያ አንተ አይንህ ላይ ያጠለቅከውን የጎጥ ጭምብል አውልቀህ፣ እዚህ ፎረም ያለውን የሌላ ጎሣ ኢትዮዽያዊ ወንድምህን በጨዋ ደንብ አስተናግደው፣ ራስህን አጥብበህ ከምትሄድባት ቤተእምነት በአመት አንዴ እንኳን ቀርተህ የድሮ ጓደኛህ ወደሚሄድበት ቤተእምነት ብቅ በል።

- ግብዝ ቀላባጭ ሁላ!

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by TGAA » 24 Jun 2022, 22:37

ሆሩስ ፤ የምትለው ግልጽ ነው ፤ ብዙ ስው አንተ የምትለው ስይገባው ቀርቶ አይደለም አትኩሮቱን አሁን የሚደረጉት ነገሮች ላይ የሚያደርገው ፤ ምክንያቱ አንድ ነው ይሄውም በአሁኑ ሰአት ያለው መንግስት ያለውን የህዝብ ሀበት ተጥቅሞ ፤ ካድሬዎቹን አሰልፎ ፤ የዘረኛ ፖሮፓጋንዳውን እየነዛ ተግባራዊ እያደረገ ያለው ይህንን የጎሰኛ የብሄር የመሬት ፖሊሲ ነው ፤ በቅርቡ አብይ ስለቤት ክራይ መጨመር ሲናገር የተናገርው ነገር መሬት የመንግስት መሆኑን አትርሱ እናንተ ቤት ስለገነባችሁ ዋጋ መተመን አትችሉም ነው ያለው ፤ ስለዚህ ይህንን የተጣመመ የጓሳ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ለመፍታት ፖሊሲ ከመቀየሩ በፊት ፤እዚያ የሚያድርስን መንገዱ ማዘጋጀት አለብን ፤ ለምሳሌ ህብርተሰቡ በማንነቱ እንዳይጎዳ አሁን ያለውን ህግ እንዲከበር ማድረግ ፤ ሁለተኛ የህግ የበላይነት በየቦታው እንዲሰፍር መታገል ፤ ከዚህ በኋላ ነው አንተ ያለከውን የጎሳ የመሬት ባለቤትነት ችግርን ማረም የሚቻልበት መንግድ ፤ አንት የምትለት ከፈረሱ በፊት ኮርቻውን ላይ ነው እያቶኮርክ ያለህው ፤ ስለዚህ አሁን መደረግ ያለበት ነገር ቢኖር መንግስት ሁለት ካርድ መጫወቱን አቁሞ ህግ በሁሉም አስተዳደር እንዲከበር ማድረግ ፤ ( አብይ ሰለፍርድ ቤት ያለው አመለካከት ሁሉም ሌቦች ናቸው የሚለው የራሱን ካድሬዎች ለመሙላት ነው) የመንግስት ደጋፊዎች ችግር ህዝቡ አውቆ የተፋውን ነገር ቀለም በመቀባት እውነታውን የሚቀይሩ የመስላቸዋል / ወይንም እውነታው ሲቀየር ከህልማቸው ጋር ስለሚቃረን ማመን አይፈልጉም ፤ ይህ ደግሞ ህዝቡን ግራ ከማጋባት በስተቀር የሚጠቅም ነገር አይኖረውም ፤

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by kibramlak » 24 Jun 2022, 23:25

የሞተ ሰው፣
ለአንድ ጤነኛ መሪ ሀገር ማለት ህዝብ ነው፣ ለወራሪዎች እና ለሌቤች ሀገር ማለት መሬት እና ንብረት ነው፣፣ ለእነዚህ የከረፉ ዘረኞች (ልክ እንደ ውጭ ወራሪዎች) ህዝቡን ሳይሆን መሬቱን እና ንብረቱን ብቻ ነው የሚያዪት፣፣ አብይ የከረፉ ዘረኞች ቀንደኛ ተዋናይ ነው፣፣ ባይሆን ኖሮ ትንሽየ የሰው አምሳል ርህራሄ ይኖረው ወይም ያሳይ (ለማስመሰል) ነበር፣፣ የውጭ ጠላትን መመከት የሚቻለው እኮ ህዝብን በመያዝ ነው. ሌላ አላማ ባይኖረው ከ70% በላይ ካለው ህዝብ ጋር አይጣላም ነበር፣፣ ግን ጭምብሉ ወለቀ፣ ፅንፍ የረገጠ የዘረኝነት ምትሀቱ በአደባባይ ቁልጭ ብሎ ወጣ፣፣ እንዳንተ አይነቱ ግን ወይ የዚህ ሰይጣናዊ ስርአት ተጠቃሚ/ተዋናኝ/ ነው ወይም ማስተዋል የተሳነው በቁሙ የሞተ ሰው ነው፣፣
Y3n3g3s3w wrote:
24 Jun 2022, 13:22
Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do እነሱ እንዲጠመድባቸው ያዘጋጁለትን ወጥመድ ወደ ጎን ገሸሸ አርጎ በራሱ መንገድ እየገሰገሰ ነው

የውጮቹ የአብይ መንግስት ምነድነው እንዲያደርግ የሚፈልጉት?
::

TheManWhoSawTomorrow
Last edited by kibramlak on 24 Jun 2022, 23:32, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30655
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Horus » 24 Jun 2022, 23:30

TGAA
ክልሎችን የማፍረስ ሪፎርም የዛሬ 4 አራት አመት ተጀምሮ ቢሆን ዛሬ ሕግ ሆኖ ነበር። ነገር ግን ያ ያልሆነው አቢይ በግልጽ ተናግሮታል የሱ ለውጥ አላምንም ጥርጥር ኢ ህ አ ደኢጋዊ ነው ብሎዏል። ስለዚህ እርምህ ን አውጣ አቢይ ስልጣን ላይ ሆኖ ክልሎች አይፈርሱም ። ይህ ቁም ነገር ቁጥር #1 ነው ።

ሌላው አሁን ከፖለቲካ ታክቲክነት ወደ ጥንቆላና ማጂክ የተሸጋገረው ህሳቤ 'ሕግ ማስከበር' የሚባለው እንቆቅልሽ ነው። የአመጻ ሞኖፖሊ የጨበጠው የጎሳው ከበርቴ ለራሱ ሕልውና ዝና ሃብትና ክብርና ስልጣን የሚፈልገውን የጎሳ ህግ አስጠብቅ ወይም ለውጥ የሚለው በሎጂክ ላይ መቀለድ ነው። ለ4 አመታት ህግ የማይከበረው ሕግ የሚጥሰው እራሱ በመንግስት የተደራጀው የጎሳ ከብርቴው ነው ። የጎሳ ከበርቴ ህልውና የቆመው በዘር ክልልና ሌላውን ዘር ከክልሉ በማስወገድ ነው ። ይህ ቁም ነገር 2 ነው ።

ማለትም የመንግስት ጥያቄ the question of state power የሚባለው ያ ነው ።

ሕግ ያለ ማስከበር ችግር የመጣው ህግ ማስከበር የጎሳ ከበርቴውን ስልጣን ስለሚነካ ነው ።

ስለሆነም በኢትዮጵያ መንግስት አለመኖሩን የሚመሰክረው ይህ ነው። አቢይ ገዢው ፓርቲ ቁንጮ ነው ። የመንግስቱም ቁንጮ ነው ። ሌላው ቀርቶ ፓርላማውም። ፍርድ ቤቱም ፣ ጦር ሰራዊቱን እሱ ካለው ውጭ ውልፍ አይሉም። ይህ ሆኖ ሳለ አቢይ 10 ሚሊዮን የፓርቲ አባላቱን ሌቦች ይላቸዋል። ያ ሕዝቡን ደስ ለማሰኘት እንጂ ስልጣን ከሌቦቹ ወደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እንዲዞር አይፈልግም። እነዚህ የፓርቲ ሌቦች ቦታቻው ላይ ሆነው በመስረቅ እስከ ኖሩ ድረስ ለይምሰል ሌቦች ቢባሉ ጉዳያቸው አይደለም።

ዳኞቹን ሌቦች ይላቸዋል፣ ማለትም ሕዝብ ሲቆጣ የህዝብ ድምጽ ሃይጃክ በማድረግ ተቆርቋሪ ይመስላል። ግን በተግባር ያለው ሌላ ነው ። አዲስ አበባ የምትገዛው በማጅራት መቺዎች ስለሆነ አሁን 200 000 ህዝባዊ ሰራዊት የሚባል ተፈጥሯል ያ ስንት ሺ ፖሊስ ሳይበቃ ማለት ነው።

ባንድ ቃል ኢትዮጵያን እያፈረሰ ያለው የጎሳ ሕግ እየተከበረ ኢትዮጵያ ከጎሳ መከራ ተወጣለች የሚለው ጥንቆላ በሎጂክ መቀለድ ነው ።

ዛሬ ይህን በምንልበት ቅጽበት ይህ ቆሻሻ የዘር ስርዓት መፍረስ አለበት የሚል አንድ ድምጽ አይሰማም። ማለትም ይህ ሁሉ ጫጫታ ምን ለመፈየድ እንደሆነ የሚያውቅ ሰው የለም ። አቢይን ስለሰደብከው ከስልጣን አይወርድም፣ ወደ ዜጋ ፖለቲከኛት አይለወጥም ።

አቢይ ስልጣን ላይ መክረም የሚችለው ይህን ቁ 1 የኢትዮጵያ ጥያቄ ከመለሰ ብቻ መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ በግልጽ እንዲነግረው ያስፈልጋል ።
Last edited by Horus on 25 Jun 2022, 00:20, edited 2 times in total.

Right
Member
Posts: 2725
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Right » 24 Jun 2022, 23:50

ስለዚህ ይህ አንዳችሁን እንዲፈርስ በማትጠይቁት የጎሳዎች የግል መሬት ክልል ሳቢያ ነው ኦሮሞው አማራውና ሌላው ጎሳን ከመሬቱ ለማጽዳት፣ የዘር ማጽዳት የሚያደርገው። ትግሬዎች መጀምሪያ መሬቱን ቀምተው ቀጥለው ያደረጉት ከትግሬ መሬት ለላውን የማጽዳት ነው። ኣዲስ አበባ አንድ ኢትዮጵያዊ ሰበታም ቡራዩ ገፈርሳ መኖር አይችልም ኦሮሞ ካልሆነ። ነገ ሌሎችም ጎሳዎች ተመሳሳይ ነው የሚያደርጉት ። ገና ይህ ሌላውን ከጎሳ የግል መሬት የማጽዳት ዘመቻ በያንዳንዱ ከተሞች ይካሄዳል ።

Not true.
One of the main reasons that the Ethiopian people hated and removed the TPLF is because of its ethnic policy and ethnic based constitution. Ethiopians welcomed and gave Abiye Ahmed the support he needs at the start was because of his promise to unite Ethiopians and because of the hope that he might get rid off ethnic politics. It turned out he is as narrow minded as the Weyannies.

He has been told, advised and begged by the majority of Ethiopians to get rid off this primitive, destructive and hurtful politics. He has been begged to Scrap the current constitution and adopt a new one based the universally accepted charter of rights. He adamantly refused.

Everybody knows the current constitution, Killil policy, land policy(totally owned by state as it was copied from Soviets) is a recipe to disaster.

Those are the facts. Trying to distort the facts to protect the Abiye regime is wrong.

5 years is a long time. PM Abiye is not a honest man. Just look at his record.

The solution is for enlightened people across the country to reach out to each other and reach to a conclusion that the current situation is not good to anyone but to a selected tribal leaders and their cadres. The first priority is to get rid off the TPLF & OLF. I hope our enlightened Oromo brothers (by the way as frustrated as we are their numbers are growing by the day) would take the lead.

TGAA
Member+
Posts: 5598
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by TGAA » 25 Jun 2022, 00:07

Selam/ wrote:
24 Jun 2022, 22:34
ወቸው ጉድ!

- የፈላስፉው፣ የከሳሹና የዳኛው ብዛት። ያለምንም መረጃ አብይ ገዳይ ነው ስትሉ ትንሽ ሀፍረት ስርቅ አይላችሁም? በልቤ የወያኔ እንጅ እንዳለበት ባውቅ እንኳን፣ ጣት ለመቀሰሩ ጊዜ እየገዛሁ ፀጥ ለጥ ብያለሁ።

- እዚህ እስለጠነ ሀገር እንኳ፣ የህፃናትንና አዛውንትን የግፍ ጭፍጨፉ መከታተል መቆጣጠር መንግሥት ተስኖታል፣ ኋላ ቀሩ የኢትዮዽያ ደኅንትና ጦር ሰራዊት እንዴት አባክ አድርጎ ነው በየጢሻ የሚሽሎከሎክን አረመኔ የሚቆጣጠረው?

- አብይ ህገ መንግሥትና ክልል አፍርሶ፣ አንድ ያድርገን የምትል ጎበዝ፣ እስኪ መጀመሪያ አንተ አይንህ ላይ ያጠለቅከውን የጎጥ ጭምብል አውልቀህ፣ እዚህ ፎረም ያለውን የሌላ ጎሣ ኢትዮዽያዊ ወንድምህን በጨዋ ደንብ አስተናግደው፣ ራስህን አጥብበህ ከምትሄድባት ቤተእምነት በአመት አንዴ እንኳን ቀርተህ የድሮ ጓደኛህ ወደሚሄድበት ቤተእምነት ብቅ በል።

- ግብዝ ቀላባጭ ሁላ!
እዚህ እስለጠነ ሀገር እንኳ፣ የህፃናትንና አዛውንትን የግፍ ጭፍጨፉ መከታተል መቆጣጠር መንግሥት ተስኖታል፣ ኋላ ቀሩ የኢትዮዽያ ደኅንትና ጦር ሰራዊት እንዴት አባክ አድርጎ ነው በየጢሻ የሚሽሎከሎክን አረመኔ የሚቆጣጠረው?[/size

Why do you think then when OLF was supposedly was fighting against TPLF supported by Eritrea -- OPDO didn't let this kind of massacre take place, but now when OPDO is in charge of Oromia with more than 300000 Militia to boot, in the same place to the same particular people this kind of tragedy has kept happening?

ኦነግ ሸኔን የሚያካሂደው ኦፕሬሽን ስላለ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡ – የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ

https://mereja.com/amharic/v2/727155
is it a made-up story ? who knows ? The same thing when the Mayer of Shasemene called Shemels to send more force to shashemenee -- shemeles told him to go back to his sleep. That is what he said in court. is that also a concocted story . No evidence is enough for true believers, I guess.

Selam/
Senior Member
Posts: 11549
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Selam/ » 25 Jun 2022, 00:21

I don’t buy everything that’s written out there.
TGAA wrote:
25 Jun 2022, 00:07
Selam/ wrote:
24 Jun 2022, 22:34
ወቸው ጉድ!

- የፈላስፉው፣ የከሳሹና የዳኛው ብዛት። ያለምንም መረጃ አብይ ገዳይ ነው ስትሉ ትንሽ ሀፍረት ስርቅ አይላችሁም? በልቤ የወያኔ እንጅ እንዳለበት ባውቅ እንኳን፣ ጣት ለመቀሰሩ ጊዜ እየገዛሁ ፀጥ ለጥ ብያለሁ።

- እዚህ እስለጠነ ሀገር እንኳ፣ የህፃናትንና አዛውንትን የግፍ ጭፍጨፉ መከታተል መቆጣጠር መንግሥት ተስኖታል፣ ኋላ ቀሩ የኢትዮዽያ ደኅንትና ጦር ሰራዊት እንዴት አባክ አድርጎ ነው በየጢሻ የሚሽሎከሎክን አረመኔ የሚቆጣጠረው?

- አብይ ህገ መንግሥትና ክልል አፍርሶ፣ አንድ ያድርገን የምትል ጎበዝ፣ እስኪ መጀመሪያ አንተ አይንህ ላይ ያጠለቅከውን የጎጥ ጭምብል አውልቀህ፣ እዚህ ፎረም ያለውን የሌላ ጎሣ ኢትዮዽያዊ ወንድምህን በጨዋ ደንብ አስተናግደው፣ ራስህን አጥብበህ ከምትሄድባት ቤተእምነት በአመት አንዴ እንኳን ቀርተህ የድሮ ጓደኛህ ወደሚሄድበት ቤተእምነት ብቅ በል።

- ግብዝ ቀላባጭ ሁላ!
እዚህ እስለጠነ ሀገር እንኳ፣ የህፃናትንና አዛውንትን የግፍ ጭፍጨፉ መከታተል መቆጣጠር መንግሥት ተስኖታል፣ ኋላ ቀሩ የኢትዮዽያ ደኅንትና ጦር ሰራዊት እንዴት አባክ አድርጎ ነው በየጢሻ የሚሽሎከሎክን አረመኔ የሚቆጣጠረው?[/size

Why do you think then when OLF was supposedly was fighting against TPLF supported by Eritrea -- OPDO didn't let this kind of massacre take place, but now when OPDO is in charge of Oromia with more than 300000 Militia to boot, in the same place to the same particular people this kind of tragedy has kept happening?

ኦነግ ሸኔን የሚያካሂደው ኦፕሬሽን ስላለ የጊምቢ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከላይ የተላለፈ ትዕዛዝ አለ አስፈጽም አሉኝ፡፡ – የቶሌ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ንጋቱ ኡመታ

https://mereja.com/amharic/v2/727155
is it a made-up story ? who knows ? The same thing when the Mayer of Shasemene called Shemels to send more force to shashemenee -- shemeles told him to go back to his sleep. That is what he said in court. is that also a concocted story . No evidence is enough for true believers, I guess.

Horus
Senior Member+
Posts: 30655
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Dr Abiy is doing the exact opposite of what "they" wanted/wished him do

Post by Horus » 25 Jun 2022, 00:26

Right wrote:
24 Jun 2022, 23:50
ስለዚህ ይህ አንዳችሁን እንዲፈርስ በማትጠይቁት የጎሳዎች የግል መሬት ክልል ሳቢያ ነው ኦሮሞው አማራውና ሌላው ጎሳን ከመሬቱ ለማጽዳት፣ የዘር ማጽዳት የሚያደርገው። ትግሬዎች መጀምሪያ መሬቱን ቀምተው ቀጥለው ያደረጉት ከትግሬ መሬት ለላውን የማጽዳት ነው። ኣዲስ አበባ አንድ ኢትዮጵያዊ ሰበታም ቡራዩ ገፈርሳ መኖር አይችልም ኦሮሞ ካልሆነ። ነገ ሌሎችም ጎሳዎች ተመሳሳይ ነው የሚያደርጉት ። ገና ይህ ሌላውን ከጎሳ የግል መሬት የማጽዳት ዘመቻ በያንዳንዱ ከተሞች ይካሄዳል ።

Not true.
One of the main reasons that the Ethiopian people hated and removed the TPLF is because of its ethnic policy and ethnic based constitution. Ethiopians welcomed and gave Abiye Ahmed the support he needs at the start was because of his promise to unite Ethiopians and because of the hope that he might get rid off ethnic politics. It turned out he is as narrow minded as the Weyannies.

He has been told, advised and begged by the majority of Ethiopians to get rid off this primitive, destructive and hurtful politics. He has been begged to Scrap the current constitution and adopt a new one based the universally accepted charter of rights. He adamantly refused.

Everybody knows the current constitution, Killil policy, land policy(totally owned by state as it was copied from Soviets) is a recipe to disaster.

Those are the facts. Trying to distort the facts to protect the Abiye regime is wrong.

5 years is a long time. PM Abiye is not a honest man. Just look at his record.

The solution is for enlightened people across the country to reach out to each other and reach to a conclusion that the current situation is not good to anyone but to a selected tribal leaders and their cadres. The first priority is to get rid off the TPLF & OLF. I hope our enlightened Oromo brothers (by the way as frustrated as we are their numbers are growing by the day) would take the lead.
ያልፈወን ትግል ተወው። ዛሬ የቱ ሃይል ነው በግልጽ ፕሮግራም አድርጎ ክልል ይፍረስ የሚል መፈክር ይዞ የቆመ? አንድም የለም! አማራ መግደል ይቁም ማለት ክልል ይፍረስ ማለት አይደለም ። በቃ!

Post Reply