Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አንድ የሆያ ሆዬ ቤት ስንኝ ለቴዲ አፍሮ!

Post by Horus » 24 Jun 2022, 03:14

በግጥም ቅኝት ዝርያ የሆያ ሆዬ ቤት የሚባለው የግጥም አይነት ቤት አይመታል። ለምሳሌ
አፋፍ ላፋፍ ስሄድ አገኘሁ ሚዳቋ
ጅራቷን ቢይዛት አይኗ ፍጥጥ አለ

የሚለው ሆያ ሆዬ ቤት ይባላል።

አንድ የሆያ ሆዬ ቤት ስንኝ ለቴዲ አፍሮ!

አከን አተን በፒራሚድ ያቆመው
ካህነ ካህናት ወሊቃውንት አሲረው
እንደ ረቀቀ አረቄ ዳግም ዘጎጃም
የጠለለ አሮጌ ጠጅ ፍልቴር እንደሸዋ
የመስቀል ክትፎ የብርንዶ እርጎ ጎርፍ
ቅኔ በዮፍታሄ እግር በመንግስቱ ለማ ፋና
ቅኝት በጸጋዬ ሜታፎር
በቴዲ አፍሮ ምስጢር
የሰምና ወርቅ ጥልቅ ባህር
Last edited by Horus on 24 Jun 2022, 22:14, edited 1 time in total.

Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ የሆያ ሆዬ ቤት ስንኝ ለቴዲ አፍሮ!

Post by Horus » 24 Jun 2022, 22:11


Horus
Senior Member+
Posts: 30657
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: አንድ የሆያ ሆዬ ቤት ስንኝ ለቴዲ አፍሮ!

Post by Horus » 25 Jun 2022, 03:14

ቅኔን ቅኔ ይፈታዋል ይባላል። ተቀኘ፣ ካሀነ፣ ቅነየ፣ ቂና ፣ ፈጠረ፣ አደረገ፣ ከወነ ማለት ነው ! ቅኔ ማለት አርት ማለት ነው። ከላይ "ቅኝት በጸጋዬ ሜታፎር
በቴዲ አፍሮ ምስጢር " ብዬ ነበር። ለምን?

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህን በአንድ ስለ ዳንኪራና እውነት በሚቋጥር ግጥሙ (የግጥሙ ስም ረስቼዋለሁ፣ እሳት ወይ አበባ በተባለው መድብሉ ውስጥ ያለ ነው) " እርገጥበት ጨፍርበት ዝምማ ያልከው እንደሆን ይነግርሃል አንዳች እውነት" ማለትም አይምሮህ አንዳች እውነት ቁም ነገር እንዳያስብ በጫጫታና ሆያሆዬ ጥመደው፤ አለበለዚያ አንጎልህ ጸጥ ያለ ግዜ ካገኘ እውነትህን እንድታይ ያደርግሃል ይላል!!!

ያን ወብ የጸጋዬ ማክሲምን ነው ቴዲ አፍሮ ልክ እንደ ባለቅኔው አባቱ ቅኝቱን የቂናው!!

ቴዲ አይነግረንም እንጂ ከግዕዝ አዋቂው አባቱ ብዙ የተማረው ነገር ያለ ይመስለኛል ። አባቱ ካሳሁን አፍ በፈታበት ክስታኔኛ የቅኔ ትርጉም በመጀምሪያ ጥሬ ትርጉሙ አሁንም አለ ። ቅኝት አርት ጥበብ ማለት ሲሆን ቂና ማለት አደረገ፣ ፈጠረ ማለት ማለት ነው። ወቂና መቀኘት መፍጠር ማድረግ ማለት ነው። ቅኔ ማለት ስራ ወይም ወዘላ አይደለ። ቅኔ ማለት ማክላለት ወይም የማደራጀት ክህሎት አይደለም ። ቅኔ ማለት መሸከት ወይም ማሳመር አይደለም። ቅኔ ማለት ማባለት፣ ዋባልት ወይም በባልትና ማስዋብ አይደለም።

ቅኔ ፈጠራ፣ አርት ማለት ነው! ቴዎድሮ ካሳሁን ቅኔ ቂናም እንላለን ! ቴዲ አፍሮ ቅኔ ተቀኘ ማለት ነው!!

ቅኝት በጸጋዬ ሜታፎር
በቴዲ አፍሮ ምስጢር

Post Reply