Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: Shocking: መንግሥት ያለመኖሩን የሰማው ጎርፍም ከበባ ጀምሯል

Post by Ethoash » 24 Jun 2022, 15:18

ዶክተር ቶማስ ኩክ

አዎ አንተ ለቀልድ ነው ያልከው ግን ይህ ጎርፍ ምክን ያት አለው ። ዶክተር አብይ እንጦጦ ተራራውን በአስፋልት ሞልቶት ጎርፉ ወድ መሬት መስረግ ሲገባው ጎርፍ ሆኖ ብዙ የአዲሰአበባን ከተማዎችን እያጠለቀለቀ ነው ። አንዴ ጎርፍ ቤት ውስጥ ከገባ ያንን ቤት መጣል አለብህ ። ያለበለዚያ ሞልዱ አድጎ በስውነት ህ ላይ ታላቅ በሽታ ያስከትላል። ኢትዬዽያኖች ይህንን ጎርፍ ችግር በደንብ ቤታችንን ማድረቅ ስለማንችል ቤቶቹ መጣል አለባቸው እንደቆሻሻ። ግን ድህነታችን እዛው ጎርፍ የገባበት ቤት ውስጥ ስኖር በበሽታ ታመን ስንሞት ግዜው ስለሚዘገይ ሁለቱን አናገናኘውምና እልቂቱ ይቀጥላል።

ሁለተኛ እንጨት ለማገዶ እስከተቆረጠ ድረስ ጎርፍ መቀጠሉ አይቀሬ ነው። ታድያ ጎርፍን ለማቆም እንጨት አትቁረጡ ሳይሆን ። እንጨቱን የሚተካ ዜዴ መፍጠር ነው። አንደኛው ባዬ ጋዝ ነው። ባዬ ጋዝ ካመረትን ምግብ በባዬ ጋዝ ካበስልን እንጀራም ሁሉ ። የእንጨት ፍላጎት ይቀንሳል። ቤት በእንጨት እንዳይስራ ሽክላን ርካሽ ማረግ እና የእንጨት ቤትን መከልከል ወይም ዋጋውን ከፍ ማረግ።

ሶስተኛ ሕዝቡን ቆሻሻ ውሃ ዳር እና ትቦ ላይ እንዳይደፈ ማስተማር ትቦው ከተደፈነ ጎርፍ ሲመጣ ቤታችን ውስጥ ነው የሚገባው።

አንዴ አውሎ ንፋስ በድሬደዋ ይከስታል ። ታድያ ሕብረተስቡና ጋዜጠኛው አውሎ ንፋሱ ውስጥ ሴጣን ነው ያለው ይሉሀል። ግን የእንጨት ጭፍጨፋና የመሬቱ መራቆት አውሌ ንፋሱ አዋራ ማስነሳቱ ነው ። ይህ ድርጊት የመጣው ከብቶችን ሳሩን ከመጠን በላይ ሲግጡትና መና ሲያስቀሩት ነው። ከዚያ በኋላ አፈሩ ይጋለጥና ንፋስ ሲመጣ በንፍስ ይነሳና ከተማዋን ጨለማ ያለብሳታል።

ይህም ሲገርመኝ ድግሞ ያለመጥን መስኖ ውሃ ከሀይቅ በመጠቀም ሐይቁንም አድረቀውታል ይህ እንግዲህ በደንብ ሊስራበት የሚይስፈልግ የአየር ንብረት ጥበቃ ነው።

Post Reply