Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30849
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

እያመመው መጣ! 1ኛ ሆነ! 1.8 ሚሊዮን ተመልካች በ20 ሰዓታት በአንድ ዩቲዩብ ብቻ

Post by Horus » 22 Jun 2022, 22:14

"ሁለት የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች በዓለም ጆሮ ውስጥ ገቡ..

የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ....

ክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በህጋዊ የዩትዩብ ቻናሉ ላይ የለቀቀው "ናዕት" የተሰኘው ሙዚቃ በተለቀቀ በ2ዐ ሰዓታት ውስጥ በዓለም ላይ በፍጥነት እየተደመጡ ካሉ ሙዚቃዎች ውስጥ የአንደኛ ደረጃነትን ይዟል። ለዚህም የኢትዮጵያ ሙዚቃ አፍቃሪያንን እና የቴዲ አፍሮ አድናቂዎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን።

እንዲሁም የእሱባለው ይታየው በድርጅታችን ሆፕ ኢንተርቴይመንት የተለቀቀው "ቻው ትልና" የተሰኘው ሙዚቃ ለተከታታይ ለሁለት ቀናቶች በአንደኛ ደረጃነት ሲደመጥ ቆይቶ አሁን በሁለተኛ ደረጃነት እየተደመጠ የሚገኝ ሙዚቃ ሆኗል። "የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ..." እንዲል ከያኒው።

እንዲህ ያሉ ስኬቶች ለኢትዮጵያ ሙዚቃ ትልቅ መነቃቂያ እንደሚሆን ሆፕ ያምናል። ሙዚቃዎቻችን ከዓለም ሙዚቃዎች ጋ ተወዳዳሪ ሆነው ሲደመጡ ማየት ትልቅ ኩራትን

ያጭራል።@Wax - music"