Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

አማራ ክልልን ወደ 4 ክልሎች ለማሳደግ የቀረበ ምክረ ሃሳብ! (በድጋሚ የቀረበ)

Post by sarcasm » 03 Jun 2022, 15:59

አማራ ክልልን ወደ 4 ክልሎች ለማሳደግ የቀረበ ምክረ ሃሳብ! (በድጋሚ የቀረበ)

By Haileyesus Adamu

ፖለቲካ ሳይንስ ነው። የ ፖለቲካ ችግሮችም ሳይንሳዊ በሆነ ምርምር፣ አመንክዮ እና ምክንያታዊነት ይፈታሉ። የመፍትሄ ሃሳቡ መነሻ አሁን ያለው የቋንቋና ነገድ ፌዴራሊዝም አሁን በሀገሪቱ ለሚታዩ ችግሮች ዋናው ምክንያት ነው የሚል ነው። አሁን ያለው የፌደራል አወቃቀር ሳይሆን አተገባበሩ ነው ችግር ያለበት የሚሉ ወገኖች አሉ። በኔ እምነት ግን ማንኛውም በማንነት እና ሃይማኖት ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ አክሳሪ እንጅ አትራፊ አይደለም። 30 ዓመት ተሞክሮ ታይቷል። ውጤቱም የእርስበርስ ጥላቻና እልቂት ነው።

ብዙ አሰልች ሐተታ ሳላቀርብ ቀጥታ ወደ መፍትሄ ሃሳቡ ልሂድ። አሁን ያለውን የብሔር ፌዴራሊዝም ለማፍረስ ቁልፉ በ እጃችን ነው። መፍትሄውም አማራ ክልልን ወደ 4 ክልሎች ማሳደግ ነው። ይህን ስል ብዙ ሰዎች ልትደነግጡ ትችላላችሁ ግን በትግስት ምክንያቴን አንብቡ። የ አማራ ሕዝብ አሁን ያለውን የ ብሔር ፌዴራሊዝም ይቃወማል ። እንዲፈርስም ይፈልጋል። ስለዚህ አማራ ክልልን ወደ አራት ክልሎች ማለተም ወደ ጎጃም፣ ወሎ፣ ጎንደር እና ሸዋ ክልሎች ብለን ወደ 4 የአስተዳደር ክፍለሀገሮች ወይም ክልሎች ብናሳድጋቸው ሀገሪቱ ውስጥ ምን ይከሰታል ? አማራ ይዳከማል ? ወይስ የ ብሔር ፈደራሊዝሙ ይፈርሳል? መልሱ የ ብሔር ፈደራልዝሙ ይፈርሳል ነው።

ይህ እንዴት እንደሚሆን በምሳሌ ላስረዳ። domino show የሚባል ጨዋታ አለ። በዚህ ጨዋታ ላይ ብዛት ያላቸው የረክታንግል ቅርፅ ያላቸው ዶሚኖዎች ቨርትካልይ ተራ በተራ ተጠጋግተው ይደረደራሉ። ከዛ የመጀመሪያው ዶሚኖ ተገፍትሮ ሲወድቅ ከ አጠገቡ ያለው ያለው ሌላኛው ዶሚኖም ይወድቃል እንዲህ እያለ ሁሉም ዶሚኖ ተራ በተራ ይወድቃል። ይህ በአንዱ ዶሚኖ መውደቅ ምክንያት የተቀሰቀሰው ሁሉንም ዶሚኖዎች ይጥላቸዋል። chain reaction ይፈጠራል ማለት ነው።

ይህንን ወደ እኛ ሀገር ፖለቲካ እናምጣው። ሀገራችን አሁን ያለውን የባንቱስታን የብሔር አወቃቀር ለማስውገድ የፌደራል መዋቅሩ ይፍረስ ብንል የነገድ ብሄርተኞች ከፍተኛ ተቃውሞ ያስነሳሉ። በተለይ ኦሮሚያ ላይ የማይሞከር ነው የሚሆነው። ነገር ግን አማራ ክልልን አፍርሰን ወደ አራት ክልሎች ማለትም ጎጃም ወሎ ጎንደር እና ሸዋ ክልሎች ስናሳድገው በ ኦሮሚያ ያሉት ወለጋ አርሲ ባሌ ሸዋ ኢሊባቡርም የክልልነት ጥያቄ ያነሳሉ። ለምን ? ምክንያቱም ክልል መሆን በመልካም አስተዳደር ፣ በኢኮኖሚ፣ በበጀት ድልድልና ድጎማ እንዲሁም በፖለቲካ ውክልና የተሻለ ጥቅም ስለሚስገኝ። ይህን የአማራ ክልልን አፍርሶ ወደ አራት የመልክአምድር ክልሎች ማሳደግና ሁኔታው በሌሎች የቋንቋ ክልሎች ላይ የሚፈጥረውን ሁኔታ geographic Domino ብዬ ሰይሜዋለሁ። የቲዋሪዬ ጭብጥ የአማራ ክልልን ማፍረስና ወደ ጎጃም ጎንደር ወሎና ሸዋ መልክአምድራዊ አከላለል መመለስ በአማራ ክልል ሳይወሰን በዶሚኖ ኢፌክት በሀገሪቱ ያለውን የብሄር አከላለል አፍርሶ ወደ geographic federalism ይወስደናል የሚል ነው። ይህንን ፅንሰ ሀሳቤን አማራ ክልል ላይ በመጀመሪያ እንዲሞከር የፈለኩበት ምክንያት ክልሉን ላቦራቶሪ ለማድረግ ሳይሆን የቋንቋና የነገድ ፌዴራሊዝሙ በአማራ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ራሱ አፍርሶ የተሻለ ስርዓት በማሳየት ሌሎችም እንዲተገብሩት ማሳየት ይችላል ከሚል መነሻ ነው።

ባጭሩ አማራ ክልልን ወደ አራት ክልሎች ማሳደግ (ክልል ቃሉ መከለል መወሰን የሚል አሉታዊ ስለሚመስል ሌላ የተሻለ ስያሜ ልንሰጠው እንችላለን) የኢኮኖሚ አቅምን ያጠነክራል። ስልጣንን decentralized ያደርጋል። የተሻለ የ ፖለቲካ ውክልና ያስገኛል። አሁን ክልሉ ላይ የሚታየውን ክፍፍልና የስልጣን ሽኩቻም ያስወግዳል። ስለዚህ አማራ ክልል ወደ አራት ክልሎች ተከፋፍሎ ሲያድግ ኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ዞኖችም የክልልነት ጥያቄ እንዲያነሱ ያደርጋቸዋል። ይህ ዶሚኖ effect ነው። ደቡብ ላይ የ ሲዳማ ክልልነት ጥያቄ በክልሉ ያሉ ዞኖች ሁሉ የክልልነት ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጉዋል። የሲዳማ ክልልነት ጥያቄ start point ሁኖ chain reaction ፈጥሮ በመላው ደቡብ ፈጥሩዋል ። ይህን ደቡብ ላይ እየተጠየቀ ያለ ጥያቄ ወደ geographic አከላለል shape ማድረግ ይቻላል።
የደቡብን መፍረስ እንደ መነሻ ወስደን አንስተን (ደቡብ ላይ የክልልነት ጥያቄው በ ነገድ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም የመፍትሄ አሰጣጡ ላይ ወደ geographic federalism መውሰድ ይችላል) የ አማራ ክልልንም ወደ 4/5 ክልሎች ብናሳድገው ኦሮሚያም የክልልነት ጥያቄው ይነሳል። ምክንያቱም ክልል መሆን ከላይ እንደጠቀስኩት የ በጀት እና የኢኮኖሚ ጥቅም ያስገኛል። ሕዝቡም በተሻለ ሁኔታ ራሱን በራሱ ያስተዳድራል። እንዚህን የሚፈጠሩ ክልሎች ክልል ብንላቸውም፣ state ወይም አውራጃ አልያም ክፍለ ሀገር doesn't matter። ዋናው ስያሜው ሳይሆን አደረጃጀቱ ከብሄር መስፈር መውጣቱ ነው።

ጎጃም ክልል ሲሆን የጎጃም አማርኛን፣ የአዊ አገውኛን እና ሽናሽኛን የስራ ቋንቋ ማድረግ። ወሎን ክልል አድርጎ የወሎ አማርኛን፣ የዋግ አገውኛን፣ ራይኛን(የራያ ትግርኛ) እና የወሎ ኦሮምኛን የክልሉ የስራ ቋንቋ ማድረግ (ራያ አንድ ይሆናል በሚል ታሳቢነት ነው)።

ጎንደርን ክልል አድርጎ የጎንደር አማርኛን፣ ቅማንትኛን እንዲሁም የወልቃይት ትግርኛን የስራ ቋንቋ ማድረግ (ወልቃይት ጠገዴ ጠለምት አንድ ይሆናል በሚል ታሳቢነት ነው)። ሸዋንም እንዲሁ ክልል አድርጎ የሸዋ አማርኛን እና ኦሮምኛን እንዲሁም ጉራጊኛን የስራ ቋንቋ ማድረግ (ሸዋ በሂደት አንድ ይሆናል በሚል ታሳቢነት ነው) ።

አወቃቀሩ ብሄርን መሰረት ያደረገ ሳይሆን የመልካምድር አቀማመጥን የተከተለ ይሆናል።

አማራ ክልል ላይ የሚፈጥረው ሁኔታ በ ኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች የክልልነት ጥያቄ እንዲነሳ trigger ያደርጋል። በኦሮሚያ በ ደቡብ በ ትግራይ እና በ አማራ ክልልም የ ወረዳነት እና የ ዞንነት ጥያቄ ሲነሳ አይተናል። በአንድ ክልል ውስጥ እየኖሩ ተመሳሳይ ቋንቋ ኑሯቸው ነገር ግን ተነጥለው ዞን እና ወረዳ የመሆን ጥያቄ በተለያዩ ቦታዎች የሚያነሱት ዞንነት እና ወረዳነት የመልካም አስተዳደር ፣ የበጀት ድልድል እና የ ልማት ተጠቃሚነት ላይ አስተዋፅኦ ስላላቸው ነው። ክልል መሆን የሚያስገኝውን ጥቅም ሁሉም ስለሚረዳ በርግጠኝነት በየ አቅጣጫው የ ክልልነት ጥያቄው ይነሳል። የደቡብ (ከብሔር ይልቅ ወደ ጂኦግራፊያዊ shape ተደርጎ) እና የአማራ ክልል መፍረስ በ ብሔር ላይ የ ተመሰረተው ስርዓት ላይ cascading effect ይኖረዋል።

cascading effect የምንለው እርስበርሳቸው በተያያዙ ስርዓቶች ውስጥ የ አንዱ መፍረስ አጠቃላይ የሥርዓት መፍረስ system failure ያስከትላል። አማራው ይህን የብሔር አወቃቀር ከመላ ሀገሪቱ ላይ ነቅሎ ለመጣል መፍትሄው በእጁ ነው። ሰውነታችን cancerን የሚከላከለው በ Apoptosis ወይም programmed cell death በምንለው መንገድ ነው። dysfunctional የሆነን ሴል በራሱ መግደል ማለት ነው። አሁን ሀገራችን ላይ ያለውን የብሔር ስርዓት ለማስወገድ ቀላሉ መፍትሄ የራሳችንን በቋንቋ ላይ የተመሰረተ አማራ ክልል ማፍረስ እና ወደ ተለያዩ ክልሎች መቀየር ነው። ይህ አማራን ያዳክማል ከተባለ ስህተት ነው ። አንድነት በአላማና በጋራ ራእይ ላይ ሲመሰረት እንጅ በአንድ ክልል ውስጥ በመታጎር አይመጣም። አማራ ክልል ወደ አራት ክልሎች አድጎ ሁሉም ክልሎች የየራሳቸው የ ፖሊስ እና ልዩ ኃይል ሲኖራቸው የበለጠ ኃይል ይኖረዋል እንጅ አይዳከመም። በመጀመሪያ ደረጃ በጎንደር በወሎ በሸዋ(የቅማንት የኦሮሞ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ) ያየናቸውን የእርስበርስ ግጭቶችን ያስወግዳል። ሲቀጥል ሙስናን ይቀንሳል፣ የተሻለ መልካም አስተዳደር ይፈጥራል፣ ስልጣንን decentralized ያደርጋል፣ የተሻለ የበጀት ድልድል ይኖራል፣ በኢኮኖሚው ጠንካራ ይሆናል፣ ፍትሃዊ ልማት ይፋጠናል። ሲሰልስ በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የብሔር አወቃቀር እንዲፈርስ ምክንያት ይሆናል። በመጨረሻም የእርስበርስ ጥላቻን ያስወግዳል። በዚህም ሁሉም አትራፊ የሚሆንበት ስራአተ ማህበር እንዲመሰረት ጥርጊያውን ይከፍታል።

https://www.facebook.com/haileeyesusadamu

Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

Re: አማራ ክልልን ወደ 4 ክልሎች ለማሳደግ የቀረበ ምክረ ሃሳብ! (በድጋሚ የቀረበ)

Post by Abaymado » 04 Jun 2022, 08:37

Oh my this lunatic is still living?
Is he really amara?
he is certified nut.

sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: አማራ ክልልን ወደ 4 ክልሎች ለማሳደግ የቀረበ ምክረ ሃሳብ! (በድጋሚ የቀረበ)

Post by sarcasm » 13 Aug 2022, 19:46

sarcasm wrote:
03 Jun 2022, 15:59

Post Reply