Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በኢትዮጵያ ከተለያዩ ባንኮች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ መመዝበሩ ተገለጸ!!! EBC

Post by sarcasm » 30 May 2022, 09:27

በኢትዮጵያ ከተለያዩ ባንኮች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ መመዝበሩ ተገለጸ

የማጭበርበር ወንጀሎች መፈጸማቸው እየተረጋገጠ ቢሆንም የሕዝብ ገንዘብ በሚፈለገው ልክ ማስመለስ እንዳልተቻለም ገልጸዋል።



***********************
በኢትዮጵያ በተለያዩ ባንኮች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ምዝበራ መፈጸሙን ፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የፍትሕ ሚኒስቴር በባንኮች ላይ የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል መንሥኤ እና የአፈፃጸም ዘዴን በመለየት የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ የሠራውን ጥናት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
በውይይቱም የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ ሌሎች የባንክ እና የፀጥታ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት እንደተመለከተው ከ370 ቢሊዮን ብር በላይ በባንኮች ላይ የማጭበርበር ወንጀል ሙከራ ተደርጓል።
በዚሁ ሙከራ በተለያዩ ባንኮች ከ1.8 ቢሊዮን ብር በላይ ማጭበርበር የተፈፀመ ሲሆን ከ1.9 ቢሊዮን በላይ የመዛግብት ምዝበራ መደረጉ በጥናቱ ተረጋግጧል።
በጥናቱ መሠረት 50 በመቶ ማጭበርበር የተከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲሆን በአቢሲኒያ፣ በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል እና ወጋገን ባንኮች ከ1 እስከ 4 ያለውን ደረጃ በመያዝ የማጭበርበር ወንጀል ተፈፅሞባቸዋል።
የፍትሕ ሚኒስትር ዴኤታ ፈቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት፣ በባንኮች ላይ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል።
የማጭበርበር ወንጀሎች መፈጸማቸው እየተረጋገጠ ቢሆንም የሕዝብ ገንዘብ በሚፈለገው ልክ ማስመለስ እንዳልተቻለም ገልጸዋል።

https://www.facebook.com/EBCzena