Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የዋኀን የጁሃር ሙሃመዲ ሰሞነኛ ወሬ አዳምጠው ጁሃር ተሻሻለ ሲሉ ሰማሁ እና ወሬውን ሳታኝኩ ነው እንደ የወጣችሁት ብያለሁ። እንደ ዓሣ እሾህ መልሶ ይወጋችኋል። እነደት?

Post by Abere » 28 May 2022, 11:43

የዋኀን የጁሃር ሙሃመዲ ሰሞነኛ ወሬ አዳምጠው ጁሃር ተሻሻለ ሲሉ ሰማሁ እና ወሬውን ሳታኝኩ ነው እንደ የወጣችሁት ብያለሁ። እንደ ዓሣ እሾህ መልሶ ይወጋችኋል። እነደት?

1) የጁሃር ሙሃመድ ጭብጥ አንኳር መሰረቱ በንግግሩ ውስጥ ሁሉ ኦሮሙማ ነው። ኦሮሙማ በምን ዓይነት መንገድ ከገጠመው የነውጥ ማዕበል ማለፍ ይችላል የሚል ሃሳባዊ ማብሰልሰል ያንጸባረቀ ነው።

2) ጁሃር ሙሃመዲ በንግግሩ ሁሉ ዐብይ አህመድ የሚመራው ብልጽግና ፓርቲ አሁን ላለው ውድቀት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ ያደርጋል - ከመነሻው ለውጡ መስመር ተሳስቶ እንድሂድ ዐብይ አህመድ በስህተት ሾፍሯል ነው። ነገሩ ግን አብይ አህመድን ማን አሾፈረው ነው? የአዲስ አበባ ታክሲዎች ይችን ይለጥፋሉ -አብዝተው << ሾፌሩን ማነጋገር ክልክል ነው>> የሚል። አብይ አህመድን ከገፋፉት ሰዎች መካከል ጁሃር 1 ቁጥር ነው። እንደት ይረሳል ኮዬ ጨፌ ደሜ ትፈሳለች፤ የሻሸመኔ እና ሀረር ዕልቂት እና ቤ- እምነት ቃጠሎ፤ በአዋሳ የወላይታ እና ሌሎች ወግኖች ዋይታ እና ዕልቂት፤ የጌድዮ እልቂት እና መፈናቀል፤ ወዘተ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ የጅሃር ውጤቶች ናቸው። ለወጥ ተብየው የጀመረው በለውጥ ሳይሆን በነውጥ ነው። ዋናው የዐብይ አህመድ ተፏካች ጁሃር ነበር። ለወያኔ ጥብቅና ሽንጡን ገትሮ አንድ ጊዜ ፌደራሊስት ሌላ ጊዜ የኮንፌደራሊስት አቀንቃኝ በመሆን ለትርምሱ ጽንስ ያበረከተው ቀላል አይደለም። የማስታወስ ችሎታ ያነሰው ዜጋ ካለ አሁን ጅሃር ከደሙ ንጹህ ነኝ የሚለውን ቢቀበል ያሳዝናል። እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዳውም ጤዛነሽ አብይ አህመድ እራሱ ዋና የኦነግ መረጃ ክፍል እና አስተባባሪ በመሆን በወያኔ ስርዐት ውስጥ እያለ ቀላል የማይባላ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሰው የጅሃርን እኔ እበልጥ ኦሮሙማ ነኝ ውድድር እንድጦፍ እና የጥፋት ዶፍ እንድ ወርድ ረድቷል። አሁን ላለው ጠቅላላ ብሄራዊ ነውጥ ኦሮሙማ አቀንቃኞች እጅግ ተጠያቂዎች ናቸው። ታሪክ በጊዜው ይፈርዳል።

3) ጁሃር መሃመድ በንግግሮቹ የፓለቲካ እርምት/ political correctness/ የሞላቸው አነጋገሮች በማድረግ እውነተኛውን ነገር ደብቋል። ከእስር በፊት ዘግናኝ ወንጀሎች እንደፈጸመ በሙሉ ልቡ ያመነ ግን መደብቅ ያለበት ጉዳይ ከመሆኑ አንጻር አሁን ከእስራት ከተፈታ በኋላ እንደ ነጻ ሰው ወይም ዜጋ ለመኖር ከባድ የጸጸት እና የማስተባበያ አባባሎች መናገር የግድ ይልበት ነበር። ስለዚህ ሰላማዊ ለመምሰል የተናገራቸው ሁሉ ለእራሱ የወደፊት ህልውና ይቅርታ የመጠየቅ ይዘት ያላቸው እንጅ ከተቆርቋሪነት የመነጩ አይደሉም።

ወገኔ ሆይ ሰውን ስታምን እየመረመርክ እና በዝግታ ነው። ይቅርታ ሳትጠየቅ አንተ ይቅርታ ልትሰጥ ወይም ይቅር ልትል አትችልም። የሞራል እና የተፈጥሮ ህግ ይከለክልሃል። ሁል ጊዜ በሬ ካራጁ አትሁን።

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የዋኀን የጁሃር ሙሃመዲ ሰሞነኛ ወሬ አዳምጠው ጁሃር ተሻሻለ ሲሉ ሰማሁ እና ወሬውን ሳታኝኩ ነው እንደ የወጣችሁት ብያለሁ። እንደ ዓሣ እሾህ መልሶ ይወጋችኋል። እነደት?

Post by Abere » 28 May 2022, 16:48


አንዳንድ ወገኖች በጁሃር ሙሀመድ መፈታት ሊደነቁ የሚችሉ ከሆነ የስብሃት ነጋን ተከትሎ መለቀቅ በምን አግርሞት ያዩት ይሆን? አንድ ቁም ነገር ግን መገንዘብ የግድ ይላል፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ እጅግ ያለተረጋጋ የተፈታው ተመልሶ የሚታሰርበት የታሰረው የሚፈታበት የቲያትር መድረክ እንጅ የማህበራዊ ህግጋት የሚከወኑበት አይደለም።

ዐብይ አህመድ አውራ ወንጀለኞችን በግል ትዕዛዝ ከእስር ቤት ይልቀቃቸው እንጅ ጁሃር ሙሃመድ እና ስብሃት ነጋ በወንጀል ታስረው እና ተተብትበው ነው የሚኖሩት። የቁም ሳይሆን የህዝብ እስረኞች ናቸው። ወንጀለኛ ወንጀለኛን ሊያስረው አይችልም - አብይ ወንጀለኛ ነው እነ ስብሃት እና ጁሃርም ወንጀለኞች ናቸው። ገና ብዙ ማዕበል ይመጣል መደነቅ በኢትዮጵያ ብርቅ አይደለም

Post Reply