Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

የጋላ አብይ የመውደቂያ ዘመን እየደረሰ መሆኑን በርካታ ምልክቶች እየታዮ ነው፡፡ ዋናው ጥያቄ ጋላ አብይ ኢትዮጵያን ይዞ ይወድቃል ወይስ ብቻውን ይወድቃል? ልዮ ትንታኔ!!

Post by Wedi » 28 May 2022, 06:31




የጋላ አብይ የመውደቂያ ዘመን እየደረሰ መሆኑን በርካታ ምልክቶች እየታዮ ነው፡፡ ዋናው ጥያቄ ጋላ አብይ ኢትዮጵያን ይዞ ይወድቃል ወይስ ብቻውን ይወድቃል? ልዮ ትንታኔ!!

Henok Kidane
·
ዶ/ር ዐቢይ ብቻቸውን ይወድቃሉ ወይስ ከኢትዮጵያ ጋር? / መታሰቢያ መልዓከ ሕይወት

በእኔ ዕድሜ የማውቃቸው መሪዎች ሁሉ ተዋርደው ከሥልጣን ተወግደዋል፡፡ ነገር ግን ሥልጣን ላይ እያሉ እንዴት እንደሚወድቁ ለመተንበይ ወይም ለመጻፍ የሞከረ የለም፡፡ አሁን ግን ሐሳብን በነፃነት መግለጽ የተፈቀደ በመኾኑ ስለ ዶ/ር ዐቢይ አወዳደቅ ያለኝን ምልከታ ለመግለጽ ይፈቀድልኝ፡፡ በዓለማችን በርካታ መሪዎች አገራቸውን ይዘው እንደወደሙ ከበቂ በላይ ታሪካዊ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡ ጋዳፊ ሊቢያ በኔቶ ቦንብ መቀጥቀጥ ስትጀምር “የለም እኔ ከኔቶ ጋር ልዋጋ አቅም የለኝም፤ እኔ ከሥልጣን ልውረድና አገሬን ከማፍረስ ላድናት” ብሎ ማሰብ ባለመቻሉ አገሩም ፈረሰች፤ እሱም ሽሽት ላይ እንዳለ ተይዞ በሞት ተቀጣ፡፡ ዛሬ ሊቢያ ውስጥ ከመቶ ስልሳ በላይ የታጠቁ ኃይሎች እርስ በርሳቸው እየተገዳደሉ አገሪቱ እጅግ የበለፀገ ኑሮ ከሚኖርበት አገር ወደ አቧራነት ተለውጣለች፡፡

ሳዳም ሁሴንም ከልጅነቱ ጀምሮ አሠልጥነው የኢራቅ ፕሬዚዳንት እስኪኾን ድረስ የረዱትን አሜሪካኖችን “ዞር በሉ አልፈልጋችሁም” ብሎ ጀርባውን ሲሰጣቸው፤ አሜሪካኖች ጦር ጭነው ወደ ኢራቅ በማምራት በመጀመሪያው ጦርነት ከኩዌት ያስወጡት ሲኾን በሁለተኛው ዙር ጦርነት እራሱን ሳዳም ሁሴንን ከነቤተሰቦቹ በያሉበት አድነው በመግደል አገሪቱ ሙሉ በሙሉ የመፍረስ አደጋ ውስጥ እንድትገባ አድርገዋታል፡፡ ኢራቅ ውስጥ የሃይማኖት፣ የብሔር፣ የጎሳ ውጥረት በእጅጉ ያለ በመኾኑ ይህ ውጥረት መጨረሻው ደረጃ ደርሶ አገሪቱ አሁን ድረስ ፈራርሳ ከዓለም ማሕበር ተገልላ ሕዝቦችዋም ለአስከፊ ድሕነት እና ችግር ተጋልጠው የመከራ ሕይወት እየመሩ ናቸው፡፡ የሶሪያውም መሪ በተመሳሳይ “በሥልጣኔ አልደራደርም” በማለት ዐይኑ እያየ አገሩን አፈራርሶ ይኸው እስከ አሁንም አለ፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት ክስተቶች ብቻ በመመልከት የአገራችንን መጪ ሁኔታ በዐይነ ሕሊና ስንመለከት የሚሰጠን አንድ ግልጽ የኾነ መልዕክት አለ፡፡

አገራችን በአሁኑ ጊዜ ጦር የጫነ የውጭ ኃይል እየወረራት ባይኾንም በአገሪቱ ሊሠራ የሚችል ሐገራዊ ሥርዓት በመጥፋቱ እና ብቃት እና ኃላፊነት የሚሰማው መሪ ማግኘት ባለመቻላችን ከፍተኛ ችግር ውስጥ ትገኛለች፡፡ አገራችን “ከዶ/ር ዐቢይ ጋር ትፈርሳለች ወይስ ዶ/ር ዐቢይ ’በቃኝ ችሎታ የለኝም’ ብለው ሐገሪቷ ከመፍረሷ በፊት ከሥልጣን ይወርዳሉ” የሚለውን ጥያቄ ማንም አገሩን የሚወድ ዜጋ ሊጠይቀውና መልስ እንዲገኝ የበኩሉን ጥረት የሚያደርግበት ተግባር ነው፡፡ አሁን እንደ አማራጭ የተቋቋመው አካታች የምክክር መድረክ ገና ከጅምሩ ሙሉ በሙሉ ከሽፏል፡፡ ምክንያቱም የምክክር መድረኩ የመጨረሻ ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ዶ/ር ዐቢይ “በሥልጣኔ አትምጡብኝ፤ ለሚቀጥለው አምስት ዓመት ተመርጫለሁ” ብለው በግልጽ አማርኛ ነግረውናል፡፡ አንድ አካታች የምክክር መድረክ በዋናነት የሚያስፈልገው በአንድ አገር ውስጥ ሰላማዊ በኾነ መንገድ ከብልሹ ሥርዓት ወደ ሠለጠነ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመሸጋገር የሚያስችል ለመኾን ነው፡፡ በተጨማሪ በምክክር መድረኩ ላይ የተወሰነው የመጨረሻው ውሳኔ ሁሉም ባለ ድርሻ አካል ተፈጻሚ ሊያደርገው የሚገባ አሠራር መኾን ሲገባው ዶ/ር ዐቢይ ገና አንድ እርምጃ ሳንራመድ “እንደፈለጋችሁት ተመካከሩ ሥልጣኔን ግን አልለቅም” ማለታቸው አካታች የምክክር መድረክ ተብሎ በፓርላማ የተቋቋመው ኮሚሽን ፋይዳ ቢስ ኮሚሽን ያደርገዋል፡፡

ከላይ በተጠቀሰው ወሳኝ ምክንያት ኮሚሽኑ ገና ከመነሻው ዓላማው የከሸፈ በመኾኑ በኮሚሽኑ ላይ የሚጣል ምንም ተስፋ የለም፡፡ እዚህ ላይ ሁላችንም ልንጠይቀው የሚገባ ጥያቄ ታዲያ ኢትዮጵያን የሚታደጋት መፍትሔ ምንድን ነው? የሚለው ነው፡፡ በአገራችን ያለውን የኢኮኖሚ ውጥረት፣ የፀጥታ መደፍረስ፣ የሥርዓት መጥፋት፣ ፀረ ሠላም ኃይሎች በየጊዜው እየገነኑ መሄድ፣ በክልሎች መካከል እየከረረ የመጣው አለመግባባት፣ በክልሎች እና በፌደራል መንግሥት መካከል መናናቅና መናበብ መጥፋት፣ ከአዲስ አበባ ውጭ የመንገድ ግንባታ የፋብሪካ ሥራ በውጭ ምንዛሬ ዕጦት ምክንያት እየተቋረጠ መቀጠሉና የመጨረሻው ውጤት ምን ሊኖን ይችላል? ብሎ መገመት ከማንም ሐገሩን ከሚወድ ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ በጣም የሚገርመኝ ነገር ብዙ ሰዎች በአገራችን ምንም ችግር የሌለ ይመስል የሚያማምሩ ልብስ ለብሰው ውድ መኪና እየነዱ የፖለቲካው ጉዳይ ምንም የማሳስባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ዜጎች እድሜ ልካቸውን ለፍተው ያፈሩት ሐብት በአንድ ጀንበር ሊፈርስ እንደሚችል የተገነዘቡ አይመስልም፡፡

ህወሓት ወርራ በያዘችው ከተሞች የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ሲፈርስ ምን ሊከሰት እንደሚችል ለሁላችንም በቂ ትምህርት የሰጠ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ከደርግ ዘመን ጀምሮ በፖለቲካ ጉዳይ በብቃት መሳተፍ እንዳይችሉ የመታገል ፍላጎታቸው እንዲኮላሽ በመደረጉ አሸባሪ ቤቱ ድረስ ገጀራ ይዞ እስኪመጣ እየጠበቀ መቀመጥን መርጧል፡፡ ስለኾነም ተማሪው ከፍተኛ ችግር ከመከሰቱ በፊት በጊዜ በንቃት በፖለቲካ ውስጥ በመሳተፍ አገሩን ለማዳን እየሠራ አይደለም፡፡ ድሮ ልጆች ኾነን የማውቀው የተማሪዎች ንቅናቄ ዛሬ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዘር የተከፋፈሉ በመኾኑ ለአንድ ዓላማ ቆመው የአገራቸውን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የተሻለ እንዲኾን እየሠሩ አይደለም፡፡ ታዲያ የዚህችን ሐገር የፖለቲካ ችግር ማን ያስወግድላት? ውጭ ሐገር ያሉ የሚዲያ ተቋማት የቻሉትን እየሠሩ ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ተቋማት በተግባር ሊከወኑ የሚገባቸውን ችግሮች ማስተናገድ የሚችሉበት አቅም የላቸውም፡፡

በአሁኑ ጊዜ እኔ በሰበሰብኩት መረጃ መሠረት በየመሥሪያ ቤቱ እጅግ በሚያሳፍር ሁኔታ ዘረፋ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ የሥርዓት አልበኝነት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ በመሄድ ላይ ነው፡፡ የዶ/ር ዐብይ መንግሥት በሾማቸው ባለስልጣናት እንኳን ከበሬታን አግኝቶ አገርን እንደ አገረ ማስተዳደር አልቻለም፡፡ በጽሑፍ መግቢያ ላይ አገራቸውን አፍርሰው እራሳቸውም የፈረሱ መሪዎች በቅርብ ጊዜ ታሪክ መከሰታቸውን ለማየት ችለናል፡፡ አሁን ደግሞ አገራችን ሳትፈርስ መሪዎች የፈረሱበትን የቅርብ ጊዜ የአገራችንን ታሪክ እንመልከት፡፡ የአፄ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓት ሲፈርስ አገራችን ሳትፈርስ መቀጠል ችላለች ደርግ በኢትዮጵያ ውስጥ ውጤት ያመጣ ተግባር ባይከውንም ኢትዮጵያን እንደ አገር ለአስራ ሰባት አገር ማስተዳደር ችሎ ነበር፡፡ ደርግ ደግሞ በራሱ ጊዜ ሲፈርስ ኢትዮጵያ ሳትፈርስ ለ27 ዓመታት መቀጠል ችላለች፡፡ ከዚያ ሕወሓት ኢሕአዴግ ሲፈርስ ኢትዮጵያ አሁንም እንደ አገር መቀጠል ችላ ነበር፡፡ ከአምባገነን መሪዎች ጋር አብራ አልፈረሰችም፡፡

አሁን ግን የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅን እያሳሰበኝ ያለው ጉዳይ (አሁን ያለው ተጨባጭ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ) አገራችን ከዶ/ር ዐቢይ የተበላሸ ሥርዓት ጋር አብራ ትፈርሳለች ወይስ የዶ/ር ዐቢይ ሥርዓት ብቻውን ይፈርሳል? የሚለውን ጥያቄ ማሰላሰል ከጀመርኩ ሰንበትበት ብያለሁ፡፡ ማንኛውም አገሩን የሚወድ ዜጋ የፈለገ መሪ ይምጣ፤ ይሄድ አገር ግን ምን ግዜም መቀጠል እንዳለባት ሁሉም ዜጋ የፀና ዕምነት አለው፡፡ ምናልባት የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት ተፍረክርኮ አገር ማስተዳደር የማይችልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ ኢትዮጵያ በሦስት ምክንያቶች መንግሥት ባይኖርም በቀላሉ ከካርታ ላይ የምትሰረዝ አገር አትኾንም፡፡ የመጀመሪያው ምክንያት የማዕከላዊ መንግሥት መንገዳገድ ሲጀምር ጠባብ ብሔርተኞች የራሳቸውን መንግሥት ለመመሥረት መሯሯጣቸው አይቀርም፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከሙከራ አልፎ ማዕከላዊ መንግሥት ባይኖርም ሊሳካላቸው አይችልም፡፡ ምክንያቱም አሁን ለመፍጠር የተሞከረው የብሔር ክልል በወረቀት ላይ እንጂ በመሬት ላይ የተቸከለ ምልክት ባለመኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች በቀጥታ መሬት ይገባኛል ጥያቄ እያነሱ ወደ ግጭት መሄዳቸው አይቀርም፡፡ በመኾኑም መቼም ተረጋግተው የብሔር መንግሥት የሚመሠርቱበት ሁኔታ አይፈጠርም፡፡

ሁለተኛው ምክንያት የማዕከላዊ መንግሥት ሙሉ በሙሉ የመፍረክረክ አደጋ ውስጥ ቢገባ ሕይወት በባሕላዊ ሥርዓት ትቀጥላለች፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ 60% የሚኾነው አሁንም መንግሥት ኖረም አልኖረም እየኖረ ያለው በባላሕዊ ሥርዓት ነው፡፡ አብዛኛው ያገራችን ዜጋ ያለ ገንዘብ፣ መድኃኒት፣ ባንክ፣ ቴሌ የመሣሠሉ አገልግሎቶች ባይኖሩም ወደ ቀደምቱ የባሕላዊ ሥርዓት በመመለስ ኑሮን ማስቀጠል ይችላል፡፡ ሦስተኛው እጅግ የሚደንቀው ባሕላችን ደግሞ ከተለያየ ሃይማኖቶች፣ ባሕሎች፣ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ተቻችሎ የመኖር እጅግ አስገራሚ ባሕላዊ እሴቶች ያለን ሕዝቦች በመኾናችን ይህ ትልቅ ቅርሳችን በመኾኑ የማዕከላዊ መንግሥት ባይኖርም ሕይወት መቀጠሏ አይቀርም፡፡ እዚህ ላይ በቅርቡ የታዘብነው እጅግ አስደናቂ ክዋኔ መጥቀሱ ተገቢ ነው፡፡ የህወሓት አሸባሪ ቡድን የትግሬ ወጣቶችን አሠልፎ በአማራ ሕዝብ ላይ እጅግ የሚዘገንን ወንጀል ከፈፀመ በኋላ ወደ ኋላ ተገፍቶ ወደ ትግራይ እንዲያፈገፍግ ከተደረገ በኋላ የትግራይ ሕዝብ እሚበላው ሲያጣ “በረሐብ ከመሞት በአማራ ጥይት እንሙት” ብለው በርካታ የትግራይ እናቶች እና ቤተሰቦቻቸው ወደ አማራ ክልል ሲሰደዱ እነሱ እንደጠበቁት አማራ ክልል ሲገቡ ሞት ሳይኾን የጠበቃቸው እጅግ የሚያስገርም እንክብካቤና የወዳጅነት አቀባበል ነበር፡፡ በዚህ እጅግ የሚደነቅ ኢትዮጵያዊ ባሕላችን እኔ በግሌ በእጅጉ ኮርቻለሁ፡፡

ህወሓቶች ከትግራይ ክልል ወጥተው አማራ ክልል ከ1983 በፊት ገብተው ወልቃይት ውስጥ በአማራ ሕዝብ ላይ ያደረጉትን ዘግናኝ ወንጀል በቴሌቪዥን መስኮታችን እያየን ሌላ ቻናል ስንቀይር ደግሞ የትግራይ ሕዝብ በረሐብ ምክንያት አማራ ክልል ገብቶ ወንድማዊ አቀባበል ተደረገለት የሚል ዜና እንሰማለን፡፡ ይህ በዕውነቱ የአማራ ሕዝብ ከልብ ሊያኮራው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ለሌሎችም በርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ትምህርት የሚሠጥ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ለአዲሱ ትውልድ እንዲህ ዐይነት አስደናቂ ታሪኮችን በማስተማር የተሻለ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ ሲጠቃለል በዓለማችን ታሪክ ሐገራዊ ሥርዓት በመፍጠር ሂደት ውስጥ ሐገሮች ከመሪያቸው ጋር ፈርሰዋል፡፡ ወይም መሪዎቹ ብቻቸውን የፈረሱበት አጋጣሚ በታሪክ በስፋት ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ ከሁለቱ አማራጮች በእርግጠኝነት የሚሻለው መሪዎች ብቻቸውን ቢወድቁ ነው፡፡ መሪዎች “የሚተካኝን ሰው ካዘጋጀሁ የኔ ዕድሜ ያጥራል” ብለው ያምናሉ፡፡ በዕርጅና እና በሕመም ውስጥ ከመኾናቸውም በተጨማሪም በእነሱ አመራረ ሐገሪቱ አስፈሪ በኾነ የኢኮኖሚ ድቀት ውስጥ ኾና እንኳን ከሥልጣን ወርዶ ተራ ሰው መኾን እንደ ውርደት ይቆጥሩታል፡፡ “ሥልጣኔን አለቅም” እያሉ አገርን እጅግ ለከፋ መከራ ይዳርጋሉ፡፡

ሊቢያን እንደ ምሳሌ ብንወስዳት የሊቢያ ሕዝብ በነዳጅ ሐብት ምክንያት እጅግ የተንደላቀቀ ኑሮ እየኖረ የዴሞክራሲ መብቱን ለማስከበር ባደረገው ሙከራ ዴሞክራሲውም ቀረ የነበረውም የበለፀ የአኗኗር ሥርዓት እጅግ በአጭር ጊዜ ከጥቅም ውጭ ኾነ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መሪዎችን የሚፈጥሩትን በደል የመሸከም ብቃት አለው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ብቃት ያዳበረው ከብዙ መቶ ዓመታት ጀምሮ ወደ ሥልጣን የሚመጡን ጉልበተኞች ተሸክሞ የመኖር ባሕል በማዳበሩ ነው፡፡ በድሮ ዘመን በሁለት መሳፍንቶች መካከል ጦርነት ተደርጎ አንደኛው ማሸነፉ ከተረጋገጠ የተሸናፊ ሠራዊት ወደ አሸነፈው መሳፍንት ሠራዊት ለመቀላቀል ጊዜ አይወስዱበትም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄ ሁሉ ሰቆቃ በመንግሥት እየተፈፀመበት ችሎ መኖር (አንድ ኰርኳሪ ምክንያት እስኪያገኝ ድረስ) ያቅበታል፡፡ እዚህ ጎረቤታችን ሱዳን ውስጥ እንኳን ዳቦ ላይ ሳንቲም ተጨመረ ብሎ አደባባይ መውጣት በእጅጉ የተለመደ ነው፡፡

በጣም የሚገርመን የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት አገር ማስተዳደር ሙሉ በሙሉ ቢያቅተውና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ማቅረብ ቢሳነው እና ሕዝባዊ አመጽ ቢነሣ ከላይ ያሉት መሪዎች መሄጂያቸውን አዘጋጅተው ይኾናል፡፡ ከስር ያለው በቀጥታ ከዜጎች ጋር ግንኙነት ያለው የካድሬ መንጋ ምን እደሚውጠው የምናየው ይኾናል፡፡ ተመሣሣይ ክስተት በኔ ዕድሜ ሦስት ጊዜ አስተናግጃለሁ፡፡ የመጀመሪያው የንጉሡ ሥርዓት ብቻውን ሲፈራርስ በየገጠሩ እና በየከተማው ያሉ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች የደረሰባቸውን ችግር ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ የደርግ ሥርዓት ፈርሶ የደርግ አባሎች እና ካድሬዎቻቸው የደረሰባቸውን ሁኔታ በቅርብ የሚታወስ ነው፡፡ ከዚያ በመቀጠል ህወሓት ከሥልጣን ሲወገድ ትግሬዎች በኦሮሞዎች ሲተኩ ብዙ የትግራይ ተወላጆች ለችግር ተዳርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ እስከ አሁን ከነበሩት ሥርዓቶች ሁሉ በባሰ ሁኔታ የዶ/ር ዐቢይ መንግሥት የመስቀል ደመራ መኾኑ እጅግ ግልጽ ኾኗል፡፡ የመስቀል ደመራ ነዶ ሲያልቅ መውደቁ አይቀርም፡፡ ጥያቄው “እንዴት ይወድቃል?” የሚለው ነው፡፡

Tadiyalehu
Member
Posts: 664
Joined: 29 Jul 2014, 09:53

Re: የጋላ አብይ የመውደቂያ ዘመን እየደረሰ መሆኑን በርካታ ምልክቶች እየታዮ ነው፡፡ ዋናው ጥያቄ ጋላ አብይ ኢትዮጵያን ይዞ ይወድቃል ወይስ ብቻውን ይወድቃል? ልዮ ትንታኔ!!

Post by Tadiyalehu » 28 May 2022, 07:50

ጅል አይሙት እንዲያጫውት! 😀🤣😀 ነውወይስ
ጅል ቆምጬ አይሙት እንዲያጫውት!
ኩንታል መኅይም! እናንተን ብሎ የፖለቲካ ተንታኛ እና ፕሪዲክተር! እኔምለው የአእምሮ ቀንጨራነት በዘር ነው እንዴ የወረሳችሁት?
ጽንፈኛ ነፍጠኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ ማለት የኢትዮጵያ መንግሥት አበቃለት ማለት ነው? ( በጭቃ አንጎል ነፍጠኛ አስተሣሰብ መሠረት!)
ይልቁንስ ሀገር ያፈርስ የነበረው የናንተን ትምክት እና ቀረርቶ በሆደ ሰፊነት ችሎ ማስታመሙ ነበር።
"አህያና ነፍጠኛ ዱላ እንጂ ፍቅርና ዴሞክራሲ አያውቅም" እየተባለ አብይ የለም ሆደሰፊ እንሁን ብሎ ... ለጥቂት ዓመታት ሽቅብ ሸናችሁ!
አሁን የትምክህት ልጋጋችሁ መራገፍ ሲጀምር ... ኢትዮጵያ አበቃላት?! ናና ሞክረን! እናሣይሃለን!
አህያ የአህያ ዘር!
እንኳንም ከናንተ አንዱ አድርጎ ያልፈጠረን!
እበት አንጎል ነፍጠኛ!!!

Post Reply