Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት መንግስት 124 ቢሊየን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ። 22% of annual national budget of 561 Billion Birr!!

Post by sarcasm » 26 May 2022, 07:37

መንግስት የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት 124 ቢሊየን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት መንግስት 124 ቢሊየን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው የነዳጅ ግብይት ሪፎርም ትግበራ ማስተዋወቂያ መድረክ በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በመድረኩ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ፣ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ላይ ያሉ ፈተናዎችን የሚዳስስ ሰነድ አቅርቦ ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ ሪፎርሙ በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን በዘላቂነት ለመፍታት ወሳኝነት አለው።
በተለይ የትግበራ ሂደቱ እንዲሳካና ፍሬያማ እንዲሆን የፖለቲካ አመራሩን ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ገልጸው፥ ዘርፉ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የግብይት ሥርዓቱን ማዘመን ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ እንደሆነም አንስተዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የተነደፈው ሪፎርም የግብይት ሥርዓቱን ወደ ዓለም አቀፍ የግብይት ሥርዓት ለመቀየር ታስቦ መዘጋጀቱም ነው የተገለጸው።
መረጃው የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትና የኢዜአ ነው

https://www.facebook.com/fanabroadcasting


Ethiopian parliament approves annual budget for 2021/2022 fiscal year

Source: Xinhua| 2021-07-06 01:35:06|Editor: huaxia


ADDIS ABABA, July 5 (Xinhua) -- The Ethiopian parliament on Monday approved a budget of 561.67 billion Ethiopian birr (about 12.9 billion U.S. dollars) for the country's 2021/2022 fiscal year that starts on July 8.

The Ethiopian House of People's Representatives (HoPR), the lower house of the Ethiopian parliament, approved the draft budget that was tabled by the Ethiopian Council of Ministers last month.

Out of the total proposed 561.67 billion Ethiopian birr annual budget, 203.95 billion birr is assigned for regional states' budget, 183.5 billion birr for capital expenditure, 162 billion birr for government spending, while the remaining 12 billion birr is allocated for implementation of sustainable development goals, according to the draft motion presented to the HoPR.

Meanwhile, the Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed on Monday told members of the HoPR that the East African country's export volume registered an 18 percent increase during the just-concluded 2020/2021 Ethiopian fiscal year.

According to Ahmed, resettling thousands of displaced persons, strengthening the country's COVID-19 response efforts, finishing mega development projects, as well as rehabilitating migrant returnees are major current priorities for the Ethiopian government. Enditem