Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Horus » 25 May 2022, 18:36

የአንድ ፈጣሪ እምነት የፈለሰፈው ታላቁ የግብጽ ንጉስ ፈራኦን አከናተን !!በአንድ ፈጣሪ የማመን ካልቸር የሰጡን እነዚህ ጥንታዊ ግብቶች ናቸው !!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Naga Tuma » 28 May 2022, 01:48

ሆረስ፥

ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ትልቅ ግኝቶች ዉስጥ ኣንዱ በ1964 የተጻፉት የሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን “ለካ ኣንተ ነህ” የሚሉት ሶስት ቃላት ናቸዉ ብዬ ሳስብ ነበር። ግምቴ እነዚህ ሶስት ቃላት ስለእነዚህ ጥንት ፈረኦኖች ይመስለኛል። ድንቅ ታሪክ ኣላቸዉ።

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Naga Tuma » 04 Nov 2022, 16:39

ሎሬት ፀጋዬን በዝና እንጂ በከካል ተገናኝተን ኣላዉቅም።

ለካ ኣንተ ነህ የሚለዉን በ1964 የጻፈዉን ስሰማ ከእሱ በላይ ከቦረና ጀምሮ ኢትዮጵያን በእዉቀት ነጻ ያወጣ ኣለ ወይ ብዬ እጠይቃላሁ።

ለካ ኣንተ ነህ ሲል ምን ማለት ፈልጎ ይሆን? የሚከተሉትን ማለት ፈልጎ ይሆን?

በኣማርኛ

ለካ ኣንተ ነህ፣
ሙጬን ኣንስተህ ኣንድ ኣምላክ ያልክ፣
ፈረኦንን መስርተህ ፈረቃን ያስተማርክ፣
ዲሞክራሲን ፈጥረህ የዘራህ፣
ፊደልን ፈጥረህ መጻፍን ያሳየህ፣
ፒራሚድን ገንብተህ ያቆምክ።

በአፋን ኦሮሞ

ኤዳ ስኢ ከን፣
ሙጫ ካፍቴ ዋቀ ቶክቸ ባፍቴ፣
ፈረኦ ኡምቴ ፈረቃ ባፍቴ፣
ዲሞክራሲ ኡምቴ ፈጫፍቴ፣
ፍደለ ኡምቴ በሬሱ ጀልቀብዴ፣
ፒራሚዲ ሆጀቴ ዻብዴ፣

union
Member+
Posts: 6044
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by union » 04 Nov 2022, 18:07

ቁጭራ ሆረስ

የትኝውን አምላክ ነው የምታወራው አንተ ደደብ። የፀሀዩን አምላክ ነው :lol:

ክርስትና እኮ የስም ለውጥ ያደረገ እንጂ የሁለት ሺህ አመት እድሜ ብቻ ያለው ሀይማኖት አይደለም

የኛ የፓለቲካና የታሪክ ተመራማሪው። እስቲ ንገረን መለከፃዲቅ ስንት አመቱ ነው ዛሬ። ሄኖክስ? የግብፅ ወይም የምስር ሰዎችስ እነማን ናቸው። ከግብፅ ወይም ከታችኛው ኢትዮጵያ ብልፅግና በፊት የነበረው የኦሪት አምላክስ?

የህገ ልቦናው አምላክስ

ደደብ ሽማግሌ :lol: :lol:

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Horus » 04 Nov 2022, 21:25

ናጋ ቱማ፣
የጸጋዬ ገብረ መድህን ስራዎች ያደኩበት ስነጽሁፍ ነው። ስለግጥም ቤቶች ካወቅክ የጸጋዬ ቤት የሚባል የራሱ የግጥም ሜትር አለው ፣ ልክ መደበኛ፣ ሆያሆዬ ወዘተ ቤት እንደሚባለው ፤ ግጥም በአንድ ስንኝ ውስጥ ባሉት ቃላት ቁጥር ካታጎሪው ይመደባል። ሊሞት ሲል ሁሉ ዲሲ ድረስ ሄጄ አይቼዋለሁ ። ወደ መጨረሻ ላይ በትንሹ የቀምጥ ቃላት ፊሎሎጂ ጀምሮ ነበር ። ለምሳሌ ካ ባ ራ እያለ ! ግ ን በሱ ዘመን የጥንት ግብጽ ጽሁፎች ዲሳይፈረድ ሆነው ትርጉማቸው አይታወቅም ነበር ። ያኔ ብዙ ነገር መላ ምት ነበር። ዛሬ ብዙዎቹ የቀምጥ (ኮፕት) ቃላትና ጽሁፎች ተተርጉመው ይነበባሉ ።

ስለዚን አከን አተን የሚለው የንጉሱ ስም አንተ እንደ ምትለው ሳይሆን የአተን አገልጋይ፣ የአተን ካህን ማለት ነው፤ ልክ ዛሬ ገብረ እግዚአብሄር እንደ ምንለው ማለት ነው ። አተን ብርሃን የሚተፋው ጸሃይ ወይም ሰን ዲስክ ነው። ግብጾች ህይወትን የሚፈጥረው ብርሃን ብለው ነበር የሚያምኑት ! Light is the creative force of the universe! ብርሃን ከሌለ ህይወት ላይፍ የሚባል ነገር የለም! አይኖርም ነበር! ይህ ዛሬ አይደለም ሃይማኖት ፊዚክስ አረጋግጦታል ! አብራሃሚክ ሃይማኖት ማለት የብርሃን ሃይማኖት ማለት ነው ። ክርስትናና እስልምና የሚለያዩት ከርስትና በጸሃይ ብርሃን ፣ እስላም በጨረቃ ብርሃን መመራታቸው ብቻ ።

የክርስትና አምላክ የብርሃን አምላክ ነው! ምልክቱም እሳት ነው! ለዚህ ነው ጧፍ ይዘህ ለማስቀደስ ሄደህ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ፣ ለብርሃነ ጥምቀቱ፣ ለብርሃነ ስቅለቱ አደረሰህ የምትለው!!!

የግብጽ ንጉሶች እራሳቸው እንደ እንደ ጳጳስና አቡን የፈጣሪ ወኪሎች ነን ይሉ ነበር። ድሮ ድሮ ጎድ ነንም ይሉ ነበር ። ዛሬ ስዩመ እግዚብሄር እንደ ሚባለው ። ካህን ማለት ቀነየ ፣ ከወነ፣ ተቀኘ፣ አደረገ ማለት ነው። አከን አተን የፈጣሪ ካህን፣ የፈጣሪ አገልጋይ ማለት ። ካህን የሚለው ቃል እንደ ብዙዎቹ የግዕዝ ቃላት ኬሚቲክ (ቀምጥ) ቃል ነው ። ልክ ምርቃት፣ በረከት እንደ ሚባሉት ቃላት!!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Naga Tuma » 11 Nov 2022, 17:39

ሆረስ፥

ወደዚህ ርዕስ ኣሁን መመለሴ ነዉ። እኔ ኣንብቤ የገባኝ አክናተን የመጀመርያዉ ሞኖቴይት ሰባኪ ነበረ ነዉ። ወደ ፀሃይ በመዞር ፖሊቴይዝምን ያስተወ ነዉ። ኣንተም የምትለዉ ከዛ የሚቃረን ኣይመስለኝም። መሰረተ ሀሳቡ ኣንድ ከሆነ ለየብቻ ትንታኔ ሌላ ነዉ።

በነኣክናተን ዘመን የነበረዉ ሳይንሳዊ ዕዉቀት ዛሬ ካለዉ ጋር ስናወዳድር ሰማይ እና ምድር ናቸዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም። ያኔ የነበረዉን መላ ምት እና ማስተዋል በዚህ ዘመን ሳይንስ እዉነት መሆኑን ብያረጋግጥ የዛን ዘመን ማስተዋልን ኣለማድነቅ ኣይቻልም።

ስለግጥም ቤቶች እዉቀቱ የለኝም። ስለዚህ የእኔን መጣጥፎች ምኞት እንጂ ግጥሞች ናቸዉ ማለት ኣልችልም።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Horus » 11 Nov 2022, 23:52

Naga Tuma wrote:
11 Nov 2022, 17:39
ሆረስ፥

ወደዚህ ርዕስ ኣሁን መመለሴ ነዉ። እኔ ኣንብቤ የገባኝ አክናተን የመጀመርያዉ ሞኖቴይት ሰባኪ ነበረ ነዉ። ወደ ፀሃይ በመዞር ፖሊቴይዝምን ያስተወ ነዉ። ኣንተም የምትለዉ ከዛ የሚቃረን ኣይመስለኝም። መሰረተ ሀሳቡ ኣንድ ከሆነ ለየብቻ ትንታኔ ሌላ ነዉ።

በነኣክናተን ዘመን የነበረዉ ሳይንሳዊ ዕዉቀት ዛሬ ካለዉ ጋር ስናወዳድር ሰማይ እና ምድር ናቸዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም። ያኔ የነበረዉን መላ ምት እና ማስተዋል በዚህ ዘመን ሳይንስ እዉነት መሆኑን ብያረጋግጥ የዛን ዘመን ማስተዋልን ኣለማድነቅ ኣይቻልም።

ስለግጥም ቤቶች እዉቀቱ የለኝም። ስለዚህ የእኔን መጣጥፎች ምኞት እንጂ ግጥሞች ናቸዉ ማለት ኣልችልም።
ነገር ግን ለጥያቄህ የሰጠሁህን መልስ አትርሳ፤ አከን አተን የሚለው የንጉሱ ስም ምን ማለት እንደ ሆነ ነበር ያንተ ጥያቄ! አከን ማለት ካህን፣ የአተን ቄስ፣ የአተን ፕሪስት፣ የአተን አገልጋይ፤ ዘ ሰርቨንት ኦፍ አተን ማለት ነው ። አተን ሁሉም እንደሚያውቀው ጸሃይ ሲሆን ለግብጾች ፈጣሪ ጸሃይ ወይም ብርሃን ነው ። ይህን ቁም ነገር መዘንጋት አይገባህም ። በግዕዝ ካህን ማለትና በዕብራስጥ ኮሀን ማለት ቄስ፣ ፕሪስት የፈጣሪ አገልጋይ ማለት ነው ልክ አከናተን ዘመን እንደ ነበረው ማለት ነው ። ይህ ነው እግጅ ትልቁ ነገር ለኛ ኢትዮጵያዊያን !!!

Naga Tuma
Member+
Posts: 5496
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

Re: ፈጣሪ ብርሃን ነው ... ንጉስ አከንአተን

Post by Naga Tuma » 16 Nov 2022, 16:12

Horus wrote:
11 Nov 2022, 23:52
Naga Tuma wrote:
11 Nov 2022, 17:39
ሆረስ፥

ወደዚህ ርዕስ ኣሁን መመለሴ ነዉ። እኔ ኣንብቤ የገባኝ አክናተን የመጀመርያዉ ሞኖቴይት ሰባኪ ነበረ ነዉ። ወደ ፀሃይ በመዞር ፖሊቴይዝምን ያስተወ ነዉ። ኣንተም የምትለዉ ከዛ የሚቃረን ኣይመስለኝም። መሰረተ ሀሳቡ ኣንድ ከሆነ ለየብቻ ትንታኔ ሌላ ነዉ።

በነኣክናተን ዘመን የነበረዉ ሳይንሳዊ ዕዉቀት ዛሬ ካለዉ ጋር ስናወዳድር ሰማይ እና ምድር ናቸዉ ቢባል ስህተት ኣይመስለኝም። ያኔ የነበረዉን መላ ምት እና ማስተዋል በዚህ ዘመን ሳይንስ እዉነት መሆኑን ብያረጋግጥ የዛን ዘመን ማስተዋልን ኣለማድነቅ ኣይቻልም።

ስለግጥም ቤቶች እዉቀቱ የለኝም። ስለዚህ የእኔን መጣጥፎች ምኞት እንጂ ግጥሞች ናቸዉ ማለት ኣልችልም።
ነገር ግን ለጥያቄህ የሰጠሁህን መልስ አትርሳ፤ አከን አተን የሚለው የንጉሱ ስም ምን ማለት እንደ ሆነ ነበር ያንተ ጥያቄ! አከን ማለት ካህን፣ የአተን ቄስ፣ የአተን ፕሪስት፣ የአተን አገልጋይ፤ ዘ ሰርቨንት ኦፍ አተን ማለት ነው ። አተን ሁሉም እንደሚያውቀው ጸሃይ ሲሆን ለግብጾች ፈጣሪ ጸሃይ ወይም ብርሃን ነው ። ይህን ቁም ነገር መዘንጋት አይገባህም ። በግዕዝ ካህን ማለትና በዕብራስጥ ኮሀን ማለት ቄስ፣ ፕሪስት የፈጣሪ አገልጋይ ማለት ነው ልክ አከናተን ዘመን እንደ ነበረው ማለት ነው ። ይህ ነው እግጅ ትልቁ ነገር ለኛ ኢትዮጵያዊያን !!!
ሆረስ፥

ምናልባት ጥያቄዬ ግልጽ ኣልሆነም። ሎሬት ጸጋዬ "ላካ ኣንተ ነህ" ሲል ምን ማለቱ ይሆን ያልኩኝን ኣክነ አተን ምን ማለት ነዉ እንደማለት ከተነበበ ያንን መጠየቄ ኣልነበረም። የሎሬቱን ጥያቄ ከሰመሁ ጊዜ ጀምሮ እስከ ኣሁን ድረስ ስለማህበረሰብ እንጂ ስለ ኣክነ አተን ወይም ግለሰብ መሆኑን ተገንዝቤ ኣላዉቅም። ምናልባት ልዩነቱ እዛ ላይ ይሆናል። ከጥያቄዉ ጋር ያለዉ በአፋን ኦሮሞ የተጻፈዉ ትንታኔ የበለጠ ማብራርያ ሊሆን ይችላል።

Post Reply