Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by temari » 24 May 2022, 10:53

https://www.facebook.com/natnaelmekonne ... 8355403951
Please wait, video is loading...

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by Horus » 24 May 2022, 13:47

ተማሪ
እኔ ለየት ያለ ስሜት አለኝ። በአቢይና በዱባዩ መስፍን መሃል ያለው የዝምድና አይነትና ልክ አናውቅም ። ይህ ቤተ መንግስት መስፍኑ ለአቢይ የሚሰጠው ስጦታ ከሆነ፣ የግምባታ ወጪ እንደዚያ ስለሚል አቢይን ማስቆም አይቻልም ። ባብዛኛው የታክስ ፈፋዮች ገንዘብ ካልሆነ ማለት ነው። እንደዚህ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ፊት ታሪክ ነው የሚሆኑት ። በእርግጠኘነት እነአጼ ፋሲል የጎንደርን ቤተ መንግስት ሲያሰሩ፣ እነ አጼ ላሊበላ እየዚያ አቢያተ ክርስቲያናት ሲያሰሩ ልክ እንደ ዛሬው አቢይ ላይ የሚቀርበው ሂስ የቀረበባቸው ይመስለኛል። እኔ ካቢይ ጋር ያለኝ ጠብ ስለ ፕሮጀክቶቹ አይደለም ። የዘር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ያለው ቁርጠኘት አለማሳየቱ ነው።

Abere
Senior Member
Posts: 10890
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by Abere » 24 May 2022, 14:12

በእውነቱ እንድህ ያሉ እርምጃዎች ብኩንነት እና ርካሽ ዝና ፈላጊነት እንጅ ከአገሪቱ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የማይዛመዱ ቢፈጸሙም አብረው የማይሄዱ ግንጥል ጌጦች ናቸው። አንገብ ጋቢው የአገሪቱ ችግር ቤተ-መንግስት እያለ ቤተ መንግስት እሰራለሁ ሳይሆን ስንት ህዝብ ከችግር ላወጣ እችላለሁ ነው። በእርዳታ እንኳን ቢሰራ ትርጉም አልባ ነው። ማናቸው የኢኮኖሚ ሰቀቀን ይዞት የሚሰራ ስራ አንድም ደረጃውን አይጠብቅም፤ እርሱም ደረጃውን የጠበቀ ውብት ይዞ ሊዘልቅ አይችልም። ቤተ-መንግስት በእርዳታ የስብሰባ አዳራሽ በእርዳታ መየዕለት ምግብ በዕርዳታ ምን አይነይ ስሜት እና ታሪክ ነው ይኸ የሚፈጥረው። አሳፋሪ ነው።ገሪቱ በህጻን ተረኛ ኦሮሙማ እየታመሰች መሆኑ ያሳዝናል።

kibramlak
Member
Posts: 2155
Joined: 26 Sep 2013, 09:27

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by kibramlak » 24 May 2022, 15:00

ላልገባችሁ ምክንያቱን ልንገራችሁ፣

የሚንልክን ታሪክ ጠል ሲያቀነቅኑ ከነበሩት ጋር ይያያዛል፣፣
ኦነጎች ሚንልክ የሚለው ይጥፋልን ሲሉ እንደነበር አስተውሉ፣፣

በምትኩ አፄ ኦሮሙማን ለመተካት ነው፣፣ ቆሻሻ የታናሾች የፖለቲካ ቀመር ነው፣፣ ቀስ በቀስ ታሪክን ለመደለት ነው

temari
Member
Posts: 3743
Joined: 28 Dec 2014, 21:18

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by temari » 24 May 2022, 15:13

Horus wrote:
24 May 2022, 13:47
ተማሪ
እኔ ለየት ያለ ስሜት አለኝ። በአቢይና በዱባዩ መስፍን መሃል ያለው የዝምድና አይነትና ልክ አናውቅም ። ይህ ቤተ መንግስት መስፍኑ ለአቢይ የሚሰጠው ስጦታ ከሆነ፣ የግምባታ ወጪ እንደዚያ ስለሚል አቢይን ማስቆም አይቻልም ። ባብዛኛው የታክስ ፈፋዮች ገንዘብ ካልሆነ ማለት ነው። እንደዚህ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ፊት ታሪክ ነው የሚሆኑት ። በእርግጠኘነት እነአጼ ፋሲል የጎንደርን ቤተ መንግስት ሲያሰሩ፣ እነ አጼ ላሊበላ እየዚያ አቢያተ ክርስቲያናት ሲያሰሩ ልክ እንደ ዛሬው አቢይ ላይ የሚቀርበው ሂስ የቀረበባቸው ይመስለኛል። እኔ ካቢይ ጋር ያለኝ ጠብ ስለ ፕሮጀክቶቹ አይደለም ። የዘር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ያለው ቁርጠኘት አለማሳየቱ ነው።
ይሄ እጅግ ብዙ ብር ከውጪ የመጣ ኢንቬስትመንት ከሆነ እሰየሁ፤ ነገር ግን የውጭ መንግስት ለምን ቤተመንግስት ላይ ኢንቬስት ያደርጋል? እንደ ሪፖርተር ዘገባ በከፊል ነው ኤምሬትስ የምታወጣው ስለዚህ በዋናነት ወጪው ከመንግስት ካዝና ይመስላል።

ለማናቸውም "ሸኔ ነኝ"፤ ማናምን ነኝ እያለ በየቦታው ችግር የሚፈጥር ስራ-አጥ ወጣት በበዛባት ሃገር ወጣቱን ወደ ስራ የሚያስገባ ነገር ላይ ቢውል መልካም ነው እላለሁ። ያለበለዚያ ታሪክ የምናወራበት ሃገር አይኖረንም። ሃገር ሊያፈርስ ያለ ብዙ ወጣት ስራ-አጥ እያለ የታሪክ ቅርስ ለመስራት መሞከር ብዙም ፋይዳ የለውም። ታሪክ እኮ ሃገር ሲኖር ነው።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by Horus » 24 May 2022, 15:55

temari wrote:
24 May 2022, 15:13
Horus wrote:
24 May 2022, 13:47
ተማሪ
እኔ ለየት ያለ ስሜት አለኝ። በአቢይና በዱባዩ መስፍን መሃል ያለው የዝምድና አይነትና ልክ አናውቅም ። ይህ ቤተ መንግስት መስፍኑ ለአቢይ የሚሰጠው ስጦታ ከሆነ፣ የግምባታ ወጪ እንደዚያ ስለሚል አቢይን ማስቆም አይቻልም ። ባብዛኛው የታክስ ፈፋዮች ገንዘብ ካልሆነ ማለት ነው። እንደዚህ ያሉ ፕሮጀክቶች ወደ ፊት ታሪክ ነው የሚሆኑት ። በእርግጠኘነት እነአጼ ፋሲል የጎንደርን ቤተ መንግስት ሲያሰሩ፣ እነ አጼ ላሊበላ እየዚያ አቢያተ ክርስቲያናት ሲያሰሩ ልክ እንደ ዛሬው አቢይ ላይ የሚቀርበው ሂስ የቀረበባቸው ይመስለኛል። እኔ ካቢይ ጋር ያለኝ ጠብ ስለ ፕሮጀክቶቹ አይደለም ። የዘር ፖለቲካን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ያለው ቁርጠኘት አለማሳየቱ ነው።
ይሄ እጅግ ብዙ ብር ከውጪ የመጣ ኢንቬስትመንት ከሆነ እሰየሁ፤ ነገር ግን የውጭ መንግስት ለምን ቤተመንግስት ላይ ኢንቬስት ያደርጋል? እንደ ሪፖርተር ዘገባ በከፊል ነው ኤምሬትስ የምታወጣው ስለዚህ በዋናነት ወጪው ከመንግስት ካዝና ይመስላል።

ለማናቸውም "ሸኔ ነኝ"፤ ማናምን ነኝ እያለ በየቦታው ችግር የሚፈጥር ስራ-አጥ ወጣት በበዛባት ሃገር ወጣቱን ወደ ስራ የሚያስገባ ነገር ላይ ቢውል መልካም ነው እላለሁ። ያለበለዚያ ታሪክ የምናወራበት ሃገር አይኖረንም። ሃገር ሊያፈርስ ያለ ብዙ ወጣት ስራ-አጥ እያለ የታሪክ ቅርስ ለመስራት መሞከር ብዙም ፋይዳ የለውም። ታሪክ እኮ ሃገር ሲኖር ነው።
temari

ይህኮ የፖለቲካ ተፈጥሮ ነው። እያንዳንዱ የፖለቲካ መሪ ወይ ባልስልጣንን የሚነዱት አራት ፍላጎቶች አሉ ፤(1) ስልጣን/ሃይል፣ (2) ገንዘብ/ህብት፣ (3) ዝና/ስመ ገናናነት፣ (4) ማንነት/ክብር ... ማግኘት ወይም ማካበት! ከዚህ ውጭ ሌላ ገፊ ሞቲቪሽን የላቸውም ። ለምሳሌ ስልጣን የማይፈልግ ሕዝብ አገልጋይ ቄስ ይሆናል ። ስልጣን የማይፈልግ ሃብታም ነጋዴ ይሆናል ውዘተ ። አቢይን ከዚህ ለይቶ ማየት የራሱ የተመልካቹ ስህተተ ነው። ጥያቄው አንድ ፖለቲከኛ ላገርና ለህዝብ እየሰራ እንዚያን ፍላጎቶች ማሟላት ነው ያለበት እንጂ ቅዱስ ጥቅም የለሽ ፖለቲከኛ ባለም የለም። ለምሳሌ ሃብት የሌላቸው እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ ያሉት ስልጣን አያስቀምሱም።

አቢይ ባንደኛ ደረጃ ዝናና ገናናነት የሚሻ ሰው ነው። ቀጥሎ ስልጣን ። ለግል ሃብትና ለኦሮሞ ማንነቱ ብዙ የሚጨነቅ ሰው አይደለም! በኔ እይታ!!

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 11626
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia Highlands

Re: ጠ/ሚ ዓብይና ህዝብ አልተገናኝቶም ሆነዋል

Post by Noble Amhara » 24 May 2022, 16:07

Noble Amhara wrote:
04 Jan 2022, 22:50
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...
Please wait, video is loading...

Post Reply