Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"በንፅፅር ካየነው ከዛሬው ስርዓት ይልቅ ኢህአዴግ በጣም በብዙ መልኩ የተሻለ ነበር።"

Post by sarcasm » 24 May 2022, 07:38

ህውሃት ተመልሶ ቢመጣ ቅሬታ የለኝም!

አነስታይን በዩንቨርሱ ውስጥ ቋሚ የሆነ ቦታ የለም ይላል።

በንፅፅር ካየነው ከዛሬው ስርዓት ይልቅ ኢህአዴግ በጣም በብዙ መልኩ የተሻለ ነበር። በዘመነ ኢህአዴግ የነ ብርሃኑ አባት እነ ነጋ ቦንገር በሰላም አዲስ አበባ ይነግዱ ነበር። የታማኝ ቤተሰቦች ጋይንት በሰላም ያርሱ ነበር። እኛ ኢህአዴግን ስንቃወም በቤተሰቦቻችን ላይ አንዳች ነገር ደርሶ አያውቅም።

ዛሬ ጎጃም ላይ የዘመተው የብልፅግና ሰራዊት አባቱን መያዝ ቢያቅታቸው የአንድ አመት ህፃን ልጁን አስረውታል። አዎ የአንድ አመት ህፃን ልጅ ለመያዣነት ተብሎ ታስሯል። እኛ ባንደርስበትም በታሪክ ጣሊያን የበላይን ልጅ አግቶ ነበር ይባላል። ኢህአዲግን ስንቃወም የተሻለ ስርአት ናፍቀን ነበር፤ ዛሬ እንኳን ከኢህአዲግ ይቅርና ከፋሽቶችና ከናዚዎች የከፋ አገዛዝ ስር ወደቀን።
Please wait, video is loading...
ጎጃም ባሶ ሊበን የጁቤ ላይ ብልፅግና የአንድ አመት ህፃን ልጅ አስሯል! አባትዬው መቶ አለቃ አበበ እጅ ካልሰጠ በሚል ነው ! ይህን ሽፍታ እንኳ የማይሰራውን አስነዋሪ ድርጊት የሚፈፅም ሀይል መንግስት ተብሎ ሊጠራ አይችልም።