Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

Post by Wedi » 22 May 2022, 07:29

"ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

መስፍን አማን!!

በትህነግ መንደር እየታየ ያለው ኤርትራን አብዝቶ የመተንኮስ ዳርዳርታ፣ የፌደራሉ መንግስት ለሰላም እንቅፋት ናቸው ባላቸው አክራሪ የአማራ ልሂቃን ላይ እየወሰደ ያለው አፈና እየተካሄደ ያለው አደገኛ ቁማር አካል ነው። ለሰላም የሚከፈል ዋጋ እስከሆነ የሰብዓዊ ቀውስን የሚያስቀር ስምምነት ላይ መደረሱ ማንም ተቃውሞ የለውም። ችግሩ ሰላምን በሌሎች ኪሳራ ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ሽር ጉድ ላይ ነው።

ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም ዘላቂ እንደማይሆን በአስተማማኝነት መናገር ይቻላል። እንዲ ባለው የማምታታት ፖለቲካ ስልጣንን ማስቀጠል አይደለም ፣ ሃገርን እስከ መበታተን የሚያደርስ አደጋ ለመፍጠሩ በዚህ መንገድ የሄዱ መሪዎችን ታሪክ ብቻ መለስ ብሎ መመልከቱ በቂ ነው።
***********************************

Zehabesha

·
ከመስፍን አማን

ትህነግ መጠነሰፊ የሆነ የጦርነት ዝግጅቱን አጠናቆ ዳግም የወረራ ጥቃት ምልክቶች በግልጽ እየታየ ይገኛል። በዚህ የወረራ ስጋት ደመና ባጠላበት ሁኔታ፣ባለፈው ዓመት የጦርነቱ ቀጥተኛ ሰለባ በሆነው የአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው መጠነሰፊ የአፈና ዘመቻ የሚያስከትለው አደጋ ከወዲሁ የታሰበበት አይመስልም። ከምንም ነገር ባላይ ወስጣዊ አንድነት አስፈላጊ በሆነበት፣ በዚህ ወሳኝ ወቅት፣ በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያላችውን ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞች፣የጦር መሪዎች እና የፋኖ አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው እመቃ ከትህነግ የጦርነት ዝግጅት አንጻር አማራን በመከፋፈል እና በማዳከም ለጥቃት አሳልፎ የመስጠት እርምጃ ነው። ከቅርብ ወራት ወዲህ እየተሰሙ ያሉ ቁርጥራጭ መረጃዎችን ስናገናኝ የምናገኘው ምስል በክህደት እና ሽፍጥ ቀለም የተቀባ ሆኖ እናገኘዋለን።

በፌደራሉ መንግስት እና አማጺው ትህነግ መሃከል ከወራት በፊት ድርድር መካሄድ ተጀመረ ከተባለ ወዲህ የሚስተዋሉ ነገሮችን አንድ በአንድ ስንመለከት የአብይ አህመድ መንግስት ለውጪ ጫና እጅ ስለመስጠቱ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ያስችለናል። በዚህም የትህነግን አንዳንድ ፍላጎቶች የመፈጽም እርምጃዎች መጀመራቸውን ማረጋገጥ ይቻላል። ዝርዝር ውስጥ ሳይገባ የመንግስትም እና ትህነግ መግለጫዎች ይዘት መለሳለስ መኖሩን ሲያመላክት፣ በትህነግ በኩል የሚሰጡ መግለጫዎች የፌደራሉን መንግስት ተወት ያደረጉ፣ የቃላት ጦርነቱን በኤርትራ መንግስት እና የአማራ "ተስፋፊዎች" ባሏቸው ሃይላት ላይ ማተኮሩ በራሱ የሚገልፀው ነገር አለ።

ይህ ጦርነት ከተጀመረ ለመጀመሪያ ግዜ ከአሜሪካን መንግስት ለመንግስት እየተቸረ ያለው ሙገሳ በዲፕሎማሲ ቋንቋ ብዙ የሚጠቁመው ነገር አለ። ይህ ብቻ አይደለም የዓለም ባንክ ለመልሶ ግንባታ በሚል ብድር መስጠት መጀመሩ እንዲሁ ከሰማይ የወረደ የገንዘብ ሲሳይ ስላለመሆኑ ከብዙ ምንጮች ማረጋገጥ ተችሏል። ከሱዳን ወደ መቀሌ ከራዳር እይታ ውጭ ከሚደረጉ ምስጢራዊ በረራዎች፣ በአንድ የምስራቅ አፍሪካ ሃገር ተደረገ እስከተባለው የጀነራሎቹ ግንኙነት ውስጥ ለውስጥ እየተብላላ ስላለው ፖለቲካዊ ገቢር አስረጂ ነው።

በትህነግ መንደር እየታየ ያለው ኤርትራን አብዝቶ የመተንኮስ ዳርዳርታ፣ የፌደራሉ መንግስት ለሰላም እንቅፋት ናቸው ባላቸው አክራሪ የአማራ ልሂቃን ላይ እየወሰደ ያለው አፈና እየተካሄደ ያለው አደገኛ ቁማር አካል ነው። ለሰላም የሚከፈል ዋጋ እስከሆነ የሰብዓዊ ቀውስን የሚያስቀር ስምምነት ላይ መደረሱ ማንም ተቃውሞ የለውም። ችግሩ ሰላምን በሌሎች ኪሳራ ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ሽር ጉድ ላይ ነው።

ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም ዘላቂ እንደማይሆን በአስተማማኝነት መናገር ይቻላል። እንዲ ባለው የማምታታት ፖለቲካ ስልጣንን ማስቀጠል አይደለም ፣ ሃገርን እስከ መበታተን የሚያደርስ አደጋ ለመፍጠሩ በዚህ መንገድ የሄዱ መሪዎችን ታሪክ ብቻ መለስ ብሎ መመልከቱ በቂ ነው።

Asmara
Member
Posts: 1366
Joined: 24 May 2007, 05:09

Re: "ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

Post by Asmara » 22 May 2022, 07:42

It is just cheap talk. TPLF cannot retake Badme ever again let alone overthrow Shaebia. There is a saying in Tigrigna.. it goes like this. " Zigebir nediU zeynegir" .. roughly translated it means, he who is action oriented never reveals his plans to his mom, he implements them quietly. TPLF is not endowed with that quality and anyways they don't have the capability anymore to do anything now. The sun is setting upon them now.

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

Post by Wedi » 22 May 2022, 07:43

እውነት ለመናገር የኢትዮ 360 ጋዜጠኞች ተናግረውት/አጋልጠውትና አብይ አህመድ ያልፈፀመው አንዳችም ነገር ማግኘት አይቻልም፡፡

ከ2 አመት በፊት የኢትዮ 360 ጋዜጠኞች እንዲህ ብለው ነበር፡፡ "ትንሽ ጠብቁ አብይ አህመድ ኤርትራ አና የአማራ ህዝብን ይክዳል፣ አሁን በትግራይ ላይ አይደረገ ያለውን ጦርነት በአማራ እና ቤርትራ ላይ ያደርጋል" ብለው ተናገረው ነበር!! የሚገርም እውነታ ነው!!

+

*
*
*
በዚህ ቪድዮ እንደምታዳምጡት አብይ አህይመድ "አሁን ጦርነት እንገጥማለን እያሉ የምተነኳኩስን በተደጋጋሚ "ሺህ ግዜ ገጥመውን ሺህ ግዜ ያበጦርነት ያሸናፍናቸው ሃይሎች ናቸው" ሲል የኤርትራን ስም ሳይጠቅ መልዕክት ተንግሯል!!

+

Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

Re: "ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

Post by Wedi » 22 May 2022, 07:47

Asmara wrote:
22 May 2022, 07:42
It is just cheap talk. TPLF cannot retake Badme ever again let alone overthrow Shaebia. There is a saying in Tigrigna.. it goes like this. " Zigebir nediU zeynegir" .. roughly translated it means, he who is action oriented never reveals his plans to his mom, he implements them quietly. TPLF is not endowed with that quality and anyways they don't have the capability anymore to do anything now. The sun is setting upon them now.
You are talking about TPLF. TPLF is dead fish!! The greatest treat to Eritrea's sovereignty is coming from USA and its new trojan horse Abiy Ahmed

Right
Member
Posts: 2722
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: "ኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ በማምጣት፣ ወልቃይትን አሳልፎ በመስጠት፣ የአማራ ሃይልን በማዳከም የሚገኝ ሰላም የለም" መስፍን አማን!!

Post by Right » 22 May 2022, 11:56

Wedi,
You got it.
The US cornered and pinned down Abiye Ahmed & told him what to do. Just follow the pattern. Stopping the war when the TPLF was on the run, the release of Sebhat N, the cooling of relationship with Eritrea etc.
I have a great respect to the folks @ Ethio360 with the limited resources they have they did a great service for the people of Ethiopia.
As I have said before Abiye is a dead man walking. His end will be very ugly- he is not a honest man. When leaders are with the people it is hard for the enemy to destroy them. But when leaders are against the people they are alone. It will not take long for the US and TPLF finish off this wounded animal.

Post Reply