አዎ የተረቱን ሐቀኝነት ባላውቅም ድባይ አዋራማ ነበረች በስልሳዎቹ። ግን ቤንዚን ስታገኝ የአገሪቱዋ መሪ ለሕዝቡ ያገኘነው ቤንዚን ትንሽ ስለሆነ ሌላ የኢንከም ምንጭ መፈለግ አለብን አለና። በመጀመሪያ ወደቡን ማስፋፋት አንዳለበት ተረድቶ ብዙ ብድር ተበድሮ ወደቡን ጥልቀት እንዲኖረው አሽዋውን ፍቆ አውጥቶ ወደብ ስራ።
ከዚያም ልጆቹ ይመስሉኛል የአየር መንግድን እቋቁመው አለምን ለመቆጣጠር ፈለጉ ከዚያ ደግሞ አንድ ታላቅ ነገር አረጉ።
፩። የወጭ ካምፓኒዎች መቶ በመቶ የራሳቸውን ካምፓኒ ዱባይ ውስጥ የማቋቋም መብት ስጡ፣
፪ተኛ የውጭ ካምፓኒዎች መቶ በመቶ ታክስ አይከፍሉም
፫ተኛ የውጭ ካምፓኒዎች መቶ በመቶ ያተረፉትን ሀብት ማስወጣት ይችላሉ
ይህ በአለም የሌለ ፖሊሲ ነው። ሲንጋፖር ታክስ ፍሪ ፖርት ስትል አለም ተገርሞ ነበር ግን ዛሬ እሱዋ ናት የምት ስቀው።
ትናንሽ አገሮች በካረቢያን ያሉ ልክ እንደሲውዝ ታክስ ከለላና የድብቃ አካወንት መክፈት ጀምረው ትልቅ ዶላር ለአገራቸው ማስገባት ጀምረው ነበር ። ባንካቸውን ብቻ በማንቀሳቀስ።
ታድያ ኢትዬዽያ ይህንን ሁሉ ማረግ አትችልም ሁሉም የተበላበት ነው። ስለዚህ ምንደነው ኢትዬዽያ ያላት ሌላው የሌለው። መሬት ነው ለም መሬት ነው። ልክ መለስ እንዳረገው ሜጋ እርሻዎችን መሳብ አለብን መሬት በነፃ በመስጠት፣ ነፃ ታክስ በማረግ ይህ ብቻ ለግዜው በቂ ነው ስላምም ማወረድ መስረታዊ ሲሆን ሕዝባችንንም ማንቃት እንዱስትሪ ማቃጠል ማለት የራሳቸውን ንብረት እንዳቃጠሉ እንዲቆጥሩት ማሳመን መቻል አለብን ፣ እኛም ካምፓኒዎች ለሕብረተስቦ ባካባቢ የሚኖሩትን እንዲጠቀሙ ማረግ አለብን ምንም ሳንሽዋወድ የዛን ግዜ ሁሉም ሕብረተስብ ካምፓኒዎችን እንደራሱ ይጠብቃል ማለት ነው። የዛን ግዜ እንነሳለን።
ይህ ቪድዬ በአጭሩ እንዴት አረብ ዱባይ ሀብታም ሆነች የሚለውን ይመልሳል። ቤንዚን አላት ለሚሉትም አፍ የሚያዘጋ ምላሽ አለው