Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የሰበዓዊነት ድንበር .... (ጦርነት)

Post by sarcasm » 20 May 2022, 07:25

የሰበዓዊነት ድንበር .... (ጦርነት)


Finfinne Times


TDF አራት ሺህ ምርኮኛ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሊለቅ ወይም ለፌደራሉ መንግስት አሳልፎ ሊሰጥ ነው። እኔማ ሻቢያን ሲወጋ ተሃድሶ ሰጥቷቸው ያዋጋቸዋል ብዬ ጠብቄ ነበር 😀

ለማንኛውም የትግራይ ህዝብ ጠባቂ ሰራዊት የሆነው TDF እጅግ ከፍተኛ ግፍ የፈፀሙ ፣ የተባበሩ ፣ በጦርነት የተሳተፉ ፣ ትግራይን የወረሩ ፣ ከሻቢያ ወራሪ ጋር በህብረት የሰሩ ...

ከወታደራዊ ህግ ወጥተው ንፁሃንን የገደሉ ፣ የደፈሩ ፣ የዘረፉ በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ ተባባሪ የነበሩ ከ4 ሺህ በላይ የመቀሌ ምርኮኞችን ሊፈታ እንደሆነ ገልጿል።
ከሁሉም በላይ የትግራይ ህዝብ ሊወረው ሊገድለው ሊዘርፈው የመጣውን ሰራዊት ከአንድ አመት በላይ የሚበላውን አብልቶ ፣ የሚጠጣውን ሰጥቶ ፣ ካለው ላይ አካፍሎ ..

ተቸግረው የሚበሉት እህል እንዳይገባ መንገድ ተዘግቶባቸው እንኳን ከአመት በላይ ምርኮኛን በአግባቡ ይዘው ለመልቀቅ በመቻላቸው በደማቅ ብዕር የሚፃፍ የሰብዓዊነት ጥግ ነው።

በእርግጥ አይደለም ምርኮኛ ቀርቶ የትግራይ ተወላጅ በመሆናቸው ብቻ በአደባባይ የገደሉ ፣ ያቃጠሉ ፣ በድንጋይ ቀጥቅው የገደሉ ፣ አስረው ያስራቡ ፣ ኢ-ሰበዓዊ እርምጃ የወሰዱ ፣ ያሰቃዩ ፣ የዘረፉ ፣ ከስራ ገበታቸው ያፈናቀሉ ..

ከተከራዩበት ቤት ያባረሩ ፣ ጓደኝነታቸውን ያቋረጡ ።፣ ጠቁመው ያሳሰሩ ፣ ይብዛም ይነስም በግፍ ላይ የተባበረውና የፈፀመው ህዝብ ... የትግራይ ህዝብ ምርኮኛን የያዘበት መንገድ ብቻውን እጅጉን አስተማሪና ያሉበትን የሀይማኖትና የባህል እሴት ጠቋሚ ነው።


ከፖለቲካ አንፃር ደግሞ ይህ ውሳኔ ተራ አይደለም። የድርድሩን ሂደት ፣ የመተማመን አጥሩን ፣ የስምምነቱ ቅርንጫፍ ሆነ ያሉበትን ተጨባጭ ሁኔታን በአግባቡ የሚገልፅ ነው።

ከሻዕቢያ ጋር ያለውን የጦርነት አሰላለፍንም ማንበብ ያስችላል። የፖለቲካ ውስጠ ወይራውን የሚያነድ በአግባቡ ቀኑን ጠብቆ የተመዘዘ ካርድ ነው።
በአንድ ነገር እርግጠኛ ሁኑ ... TDF የሚመዘው ካርድ የተሰላ የሚቆርጥ እንጅ ለአውሊያው የሚቀርብ መስዕዋትነት አይደለም። ምክንያቱም ፖለቲካ ነዋ !!

Finfinne Times