Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የትግራይ መንግስት በትግራይ በተካሄደው ግልፅ የወረራ ጦርነት የተሳተፉ 4 ሺህ የፋሽስት አብይ አህመድ ሰራዊት በምህረት እንዲለቀቁ ወሰነ

Post by sarcasm » 19 May 2022, 14:22

የትግራይ መንግስት በትግራይ በተካሄደው ግልፅ የወረራ ጦርነት የተሳተፉ 4 ሺህ የፋሽስት አብይ አህመድ ሰራዊት በምህረት እንዲለቀቁ ወሰነ

የትግራይ ሙርኮኞች ማእከል አስተባባሪ የሆኑት አቶ ብርሃነ ከበደ እንደገለፁት ከሆነ እነዚህ በትግራይ ህዝብና መንግስትና ምህረት የተደረገላቸው ሙርኮኞች ወደ ቤተሶቦቻቸው እና ወደየመጡበት አካባቢያቸው ይመለሳሉ ብለዋል።

እነዚህ የፋሽስት አብይ አህመድ ሰራዊት ሙርኮኞች በዋናነት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀሙት ወንጀል በሚገባ ተጣርቶ፣ ተመርም እና ታይቶ አብዛኛዎቹ በቅርብ ከትግራይ ውጭ ባሉ አካባቢዎች የተማረኩ እና በፍሽስቱ ቡድን በግዳጅ በ2013 እና በ2014 ዓ/ም ወደ ውትድርናው የተቀላቀሉ ናቸው።

በተጨማሪም ወደ ትግራይ በገቡበት ወቅት በነበራቸው የጄኖሳይድ ወንጀል ተሳትፎ ታይቶ፣ ተጣርቶ የተመለመሉ ናቸው ።

በመሰረታዊነቱ ግን ይህን ውሳኔ የትግራይ ህዝብ ታሪክ፣ ስነ ልቦና፣ ስብእና እና አስተሳሰብ የላቀ መሆኑ የሚታይበት መሆኑ አቶ ብርሃነ ገልፀዋል ።

ይህን እድል የተሰጣቸው በጦርነቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ በህመም ፣ በወሊድ ምክንያት እና ሌሎች ችግሮች ግምት ውስጥ ያስገባ ነው ያሉት አቶ ብርሃነ የትግራይ ህዝብ ይቅርባይነት፣ በሰብአዊነት የሚያምን ፣ በአስተሳሰቡም ጭምር ከጥንት ጀምሮ ይዞት የመጣው መልካም ተግባር መሆኑን ማጤኑ አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት የትግራይ ህዝብ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ሆኖ እንኳ ችግሩን ችሎ ካለችው እያካፈለ፣ ከሌለው የህክምና አገልግሎት ህክምና እንዲያገኙ እያደረገ እንደመጣ እና ይህን ተግባር በአለም አቀፍ የሙርከኞች አያያዝ ህግ መሰረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

አቶ ብርሃነ አክለውም ይህን ዘመን ተሻጋሪ ተግባር ታሪክ የሚዘክረው የትግራይ ህዝብ የአስተሳሰብ ልዕልና እና ሰብአዊነት የሚያሳይ ተግባር ነው ብለውታል።
ግንቦት 11/2014 ዓ/ም
ድምፂ ወያነ ትግራይ

የትግራይ ህዝብ መሓሪነት ከትናንት እስከ ዛሬ

የትግራይ ህዝብ በየዘመናቱ ሊወሩትና ሊገድሉት ለመጡት ወራሪዎች ከማረካቸው ብኋላ እንኳን በምህረት ሲለቅ የመጣ የሞራል ልዕልና የተላበሰ ህዝቡ መሆኑን የትግራይ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለፁ።


የትግራይ መንግስትና ህዝብ ምህረት የተደረገላቸው ሙርኮኞች ያገኙት እድል ተጠቅመው ከቤተሶቦቻቸው ጋር በሰላም ሊኖሩ እንደሚገባም የሃይማኖት አባቶቹ መክረዋል።














https://www.facebook.com/dimtsiweyane1
Last edited by sarcasm on 19 May 2022, 16:03, edited 1 time in total.

Axumezana
Senior Member
Posts: 13219
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: የትግራይ መንግስት በትግራይ በተካሄደው ግልፅ የወረራ ጦርነት የተሳተፉ 4 ሺህ የፋሽስት አብይ አህመድ ሰራዊት በምህረት እንዲለቀቁ ወሰነ

Post by Axumezana » 19 May 2022, 15:08

Forgiveness is a wisdom and the gate way to be forgiven by our God!

Matthew 5: 7

Blessed are the merciful, for they will be shown mercy.

Matthew 6:14-15

For if you forgive other people when they sin against you, your heavenly Father will also forgive you. 15 But if you do not forgive others their sins, your Father will not forgive your sins.



Post Reply