Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት ይሻላታል? የግለሰብ ነጻነት + የቡድኖች ሃይል ሚዛን = ስነ ስርዓት

Post by Horus » 19 May 2022, 01:56

እኔ ሆረስ ቃላት መፍለጥ አይመቸኝም። ደሞም በዚህ አጭር አስተያየት ውስጥ ስለ ሕገ መንግስት ዝርዝር ይዘት ማንሳት አልሻም። አንድ ዘመናዊ የመንግስት አወቃቀር ሶስት ምድቦች ( ሕግ መወሰኛ፣ የፍትህ ና ስራ አስኪያጅ) ሊኖሩት እንደ ሚገባ በብዙዎች ተቀባይነት ያገኘ ሞዴል ነው። እንደ ስሙ ከሆነ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እነዚህ 3 የመንግስት ቅርንጫፎች አሉ ።

በጎሳ ፖለቲካ፣ በጎሳ ክልል፣ እና በጎሳ ፌዴሬሽን ስር እነዚህ 3 የመንግስት ቅርንጫፎች የአንድ ጎሳ መሳሪያ ስለሆኑና ስለሚሆኑ በስም እንጂ በተግባር ፋይዳ የሌላቸው የጎሳ ልሂቃን ጥቅም ማስጠበቂያ የብዝበዛ መሳሪያዎች ናቸው ። ስለሆነም ጎሳ የሚባለው ጽንሰ ሃሳብ ከፖለቲካ ማደራጃነት ማውጣት የመጀምሪያ የለውጥ እርምጃ ነው።

ጎሳን ከፖለቲካ ማስወጫ ዘዴ የጎሳ ክልሎችን በኢኮኖሚና እና በጂኦግራፊ ክልል ወይም ክፍለ ሃገር መተካት ነው። እያንዳንዱ ኢኮጂኦግራፊያዊ ክፍለ ሃገር ስንት ሕዝብ ይኑረው? የቋንቋና ባህል ስብጥሩ ምን ይምሰል የሚሉት ጉዳዮች በሳይናሳዊ ጥናትና ህዝብ ወይይት የሚወሰን ይሆናል።

ከዚያ ቀጥሎ ያለው ግዙፍ ጉዳይ የአገሪቱ ምግር ቤት አወቃቀር ነው ። በኢትዮጵያ ሁለት የስልጣም መሰረቶች (ዜጋና ጎሳ) አልታረቅ ስላሉ አገሪቱ የፖለቲካ ሰርዓት አልባ ሆና ትገኛለች ። የጎሳ ስሜትና የጎሳ ማንነት ለስንት ግዜ እንደ ሚቆዩ አይታወቅም ። በዚያ ሳቢያ ኢትዮጵያ ላልተሰነ ረጅም ዘመን መንግስት አልባ ሆና መኖር አትችልም ።

ስለሆነም ...

ኢትዮጵያ 2 ቤቶች ያሉት ምክር ቤት እንዲኖራት የግድ ይላል።

አንዱ 120 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ዜጋዎችን በዘር፣ ጎሳ፣ ብሄር፣ ቋንቋ ሳይለይ፣ አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚለ የዴሞክራሲ መርህ ላይ የቆመ የዜጎች ምክር ቤት ወይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ምክር ቤት መመስረት የግድ ይላል ።

ሁለተኛው ጎሳዎችን እንደየ ሰው ቁጥራቸው ለቡድን ጥቅሞች የሚሟገት የብሄረሰቦች ምክር ቤት ወይም የጎሳ ሸንጎ ማቆም ትልቅ መፍቴ ይሆናል።

በሁለቱ ምክር ቤቶች መሃል የሚኖረው መስተጋብር እና የስልጣንና ግዴት ዝርዝር በሳይንሳዊ ጥናትና አገር አቀፍ የሕዝብ ወይይት ይወሰናል ።

የምርጫ ክልሎችና የተመራጮች ምልመላ ከያንዳንዱ ኢኮጂኦግራፊዋኢ ክፍለ ሃገር፣ ዞን፣ ወረዳ፣ አውራጃ መሰረት ስለሚሆን እያንዳንዱ ሰው እንደ ዜጋም ሆነ እንደ ጎሳ ቡድን ድምጹን ሲሰጥ በነጻ ለፈለገው ዕጩ ይሆናል ። አንድ ሰው ከፈለገ ለጎሳ ምክር ቤት እንኳ የሌላ ጎሳ እጩ የሚመርጥበት መብትና ዕድል የሚሰጥ አወቃቀር ነው ።

የዚህ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አወቃቀር ችግር ከተፈታ ብዙ ሌሎች የስርዓት ችግሮች አብሮ ይፈታሉ ።

ሆረስ (በአ)
ሜይ 18 2022



Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት ይሻላታል? የግለሰብ ነጻነት + የቡድኖች ሃይል ሚዛን = ስነ ስርዓት

Post by Horus » 19 May 2022, 16:59

በፊዚክስ ውስጥ ጥቁር ቁስ (ዳርክ ማተር) እና ጥቁር ሃይል (ዳርክ ኤነርጂ) የሚባሉ ነገሮች አሉ ። ነገር ግን እነዚህ የማይታዩ ነገርና አይሎች ሙሉ ተፈጥሮና ምንነት እራሱ ፊዚክስ እንኳን አያውቃቸውም ።

በሰው ልጆች አለም፣ በተለይም በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሳይንስ ውስጥ ጥቁር ኦነት (የጭለማ እውነታ) የሚባል ህሳቤም ሆነ ክስተት የለም ። ይህን እጅግ ዝቅተኛ የግንዛቤ ደረጃ እንኳን ያልጨበጡ በመቶ ሺዎች ሳይሆን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህዝብ በእልፍ አእላፍ ጦርነቶቻን ሁከት እድሜና ዘመናቸውን ሲያባክኑ እንደ መመልከት የሚያሳዝን የሚያሳፍር ነገር የለም ።

እስከ አሁን ባለው የሰው ልጅ ታሪክ እውቀት ያለው ብርሃን ውስጥ ብቻ ነው ። ማንኛውም ህይወት፣ የሰው ልጆን እንቅስቃሴ፣ ባህልም ሆነ ካልቸር፣ ሃሳብም ሆነ አይምሮ፣ ስሜትም ሆነ ኮንሺየስነስ ሁሉም ያሉት በብርሃን ውስጥ፣ ሁሉም የሚገለጹት በብርሃን ነው ። እውቀት ብርሃን ነው ። ይህን የሃሳብ ሁሉ መነሻና የእውቀት ሁሉ መጀመሪያ ያለተማሩ የኢትዮጵያ ብኩን አህዛብ ነጋ ጠባ ለዘመናት የተያያዙት ብክነት እንደ ማስተዋል ያለ አሳዛኝ ነገር የለም ።

አንድ ምሳሌ ብቻ እናስተውል ...

አሁን በዚች ቅጽበት በመቶዎች የሚቆጠሩ ትግሎች ግጭቶች ሁከቶች ብክነቶች ይካሄዳሉ ። ከኤርትራ እስከ ቦረና፣ ከግጂግጂጋ እስከ ጭልጋ ሁሉም ይታገላል፣ ሁሉም ይሟሟታል ። ነገር ግን አንዳቸውም ለምን እንደ ሚታገሉ በትክክል አያቁትም ። ቢሸነፉ ለምን እንደ ተሸነፏ አያውቁትም ። ቢያሸንፉ ምን እንደ ሚያደርጉ አያውቁትም።

መሪዎች ደንቆሮ ናቸው፤ ተከታዮች ደንቆሮ ናችው፤ አክቲቪስቶች ደንቆሮ ናቸው ፤ ሚዲያዎች ደንቆሮ ናቸው። እንስቲ አንድ ግለሰብ ሆነ ቡድን ዛሬ የኢትዮጵያ የፖለቲክ፣ ኢኮኖሚ፣ ሶሺያል፣ ካልቸራል ወይም ስነዘውግ (ኢኮሎጂ) ስነ ስርዓት ይህ ነው መሆን ያለበት ብሎ የሚያቀርብ ስም ጥቀሱ? የሉም። እስቲ አንድ ሰው ወይም ቡድን ይህ ስነ ስርዓት ትክክለኛ፣ መልካም ፣የሚሰራ ፣ ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊ፣ መንፈሳዊ ስለሆነም ስኬታማ የሚሆን ብሎ ህዝብ ለማሳመን የሚያስተምር አንድ ስም ጥቀሱ? የለም ።

የኢትዮጵያ የፖለቲካና ሶሺያል አለም ጭለማ ነው ። ማንም ምንም የማያይበት ጭለማ ጥቁር ዩኒቨርስ ነው ። በዚህ ጥቁር ድቅድቅ ጭለማ ውስጥ በግምት የሚመላለሱ ደንቆሮዎች አለም ነው። እያንዳንዱ ተዋጊ፣ ሟች፣ ገዳይ ከትግሬ እስከ ሞያሌ ፣ ከቀበሌ እስከ 4 ኪሎ ቤተ መንግስት ለምን አይነት ሰርዓት ነው? ይህን ሁሉ የምትባክነው ምን አይነት ፋይዳ ለመፈየድ ነው ብላችሁ ጠይቁት? መለስ የለውም!

እውነተኛ ሃሳብ ያለውና የሚኖረው ብርሃን ውስጥ ነው ። ጭለማ ውስጥ ያለ የሰዎች ምናብ፣ ባዶ ምኞት እና ስሜት ድንቁርና ይባላል!

አንድ ማንኛውም ማህበራዊ ሰርዓት የሚቆመው በግለሰብ ነጻነት፣ ነጻ ፈቃድና በቡድኖች የሃይል ሚዛን (ጀስቲስ) ላይ ብቻ ነው ። ይህን ሃሁ ያልቀሰመ ደንቆሮ ነው አገርና ሕዝባችንን ለዘመና እያመሰ ያለው! ታዲያ ይህ እንዴት አያሳዝንም?

ሆረስ (በአ)
ሜይ 19 2022
Last edited by Horus on 20 May 2022, 01:53, edited 1 time in total.

ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ኢትዮጵያ ምን አይነት ስርዓት ይሻላታል? የግለሰብ ነጻነት + የቡድኖች ሃይል ሚዛን = ስነ ስርዓት

Post by ethiopianunity » 20 May 2022, 01:51

ይህ ትችት የምሰጠው ለበጎ ነው በተለያዩ ጉዳዮች መስተካከል ከሚገባቸው ነገሮች፥

1) ንግግርን በተመለከተ ኢትዮዽያኖች በዚህ ፈተና ዘመን ጊዜ በኢትዮዽያ ዕንኳን መስማማት ኣንድ ኣልሆንም፣ ወይ ኣንዱ ሲተች እንደ ስድብ ኣድርጎ ይናገራል የግብረገብ ትምህርት ጉድለት ነው የሚመስለኝ፣ ኣድማጩ ደሞ ስሜታዊ ይሆናል በሰውየው ኣነጋገር። በዚህ መሃል ያገር ጉዳይ ከንቱ ሆኖ ይቀራል

2) ብዙ ሰው ያልገባው ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ሁኔታ የኢትዮዽያ ብቻ ችግር ኣርገው በማየት (burying head in the sand )ጭንቅላታችንን ኣሸዋ ውስጥ በመቅበር፣ የኢትዮዽያም ችግር ካለም ጋር የተያያዘ መሆኑና ዕንዴት ተረድተን የውስጡንም የውጩንም ችግር መፍታት እንዳለብን ነው።

ዕንግሊዘኛ ትርጉም የሚያመጣው ችግር: burying head in the sand ላልኩት እንግሊዘኛ ኣዎ ባማርኛ ይሄንን ምሳሌ ማምጣት ባልፈልግ ምክኒያቱም ኢንግሊዘኛው ወደ ኣምርኛ ቢተረጎም ትርጉም ኣይሰጥም አንዲሁም ኣማርኛው ወደ አንግሊዘኛ። ዐብዛኛዎቻችን ድረ ገጽ ላይ እንግሊዘኛ ከኛ ጋር ስለተዋሃደ በቀላሉ እንገነዘባለን ብዬ ነው ምሳሌውን የሰጠሁት። ግን በኢትዮጵያ ምስኪን ህዝብ ላይ ወይ ለኣድማጩ በስርዐት ማስረዳት ተገቢ ነው ለምን እንግሊዘኛውን እንደተጠቀሙ። ይህ ለህዝብ ክብር መስጠት ነው ብዬ ኣምናለሁ። ኢትዮዽያ ውስጥ ለህዝብ ንግጝር የሚያደርጉ ሁሉ፣ ማንም ይሁኑ የተማረውም፣ ጥራዝ ነጠቁም ምስኪኑን ህዝብ ግራ እያጋቡና ማህበረሰቡ ኣስፈላጊውን ጉዳይ ሳይረዳው ያልፋል ማለት ነው። ዕንደምረዳው ከሆነ፣ በኦሮምያ ኣማርኛን ግዕዝን ቻው ስላሉ ህዝቡን ወደ እንግሊዘኛ ዕያንፏቀቁት ይመስላል ኢትዮዽያ ቅኝ የተገዛች ኣገር በማስመሰል። ዕንደነ ቱርክና ራሻ በዲፕሎማሲ በቋንቋቸው ነው የሚናገሩት።) በነገራችን ላይ፣ ደካማ ኣናሳ ኣገር(በመሬት መሸንሸንና በህዝብ ቁጥር ማነስ ) ነው ቶሎ ማንነቱን የሚተወውና የሃያላንን ነገሮች እዳለ የሚገለብጠው። ኢትዮዮዽያ በዚሁ ከቀጠልች፣ ማንነታችንም ዕናጣለን፣ የተቆራረጠ ድንበርና የወደቀ ሃያላን እንደፈለጉ የሚረማመድባት ሆና ነው የምትቀረው። ከይቅርታ ጋር ኣንተም ኣምርኛን ስትጽፍ ኢንግሊዘኛ በብዛት ትቀላቅልበታልህ ወትሮህ. በነገራችን ላይ ዕንግሊዘኛ የኢንግሊዞች ሲሆን የቅኝ ገዢዎዎችን መውረስ ሲሆን፣ የራስን ኣማርኛ ግን መተው ክፍተኛ የራስ ህመም ነው የሚመስለኝ

3) ኣሁን ለጠየከው ጉዳይ፤ ለምርጫው ህዝቡ የተሸወደው የሚመስለው፣ ገና ኣዲስ ፓርቲ በችኮላ የተመሰረተው ማንም ሳይወያይበት ህዝብ ሳይነጋገርበት የተመሰረተ የብልፅግና ፓርቲ ይመስለኛል። ኣብይ ህዝብ ወዲያው ስለወደደው ህዝብ ኣይኑን ዕሱ ላይ ኣትኩሮ ብልጽግና ውስጥ ማን ማን ነው የተካተተው, የፓርተው ኣላማስ ብልፅግና ለምን ተባለ? የወደፊቱ እቅዱ ላገሪቱ ምን ይዞ ይመጣል? ለሚለው፣ ህዝብ የሚያውቅ ኣይመስለኝም። ብልጽግና ፓርቲ ማለት ኢሃድግ ነው የሚመስለኝ ኣባሎቹ ከኢሃድግ የተለየ ቢመስልም። ዕንዴት? ከጊዜ በሗላ የዘር በኦሮሞ ኣገዛዝ እየሆነ ይመጣል። ይህ ጭላንጭል ዕየታየ ነው። የብልጽግና ፓርቲ ምናልባት በህዋሃት የታነጸ ነው ለምን የህዋሃት ኣባላት ኣገሩን በመዋቅር ይዘው ሃብትን ኣካብተዋል። ሃብት ማለት ደሞ ሃይል ነው። የብልጽግና ፗርቲም ያ ምኞት የፖለቲከኞችና የጎሳ ሊሆን ይችላል። ያለምን ድሃ ህዝብ እያናወጠ ያለው የምራባውያን ኣዲሱ ሲስተም ግሎባላይዜሸን እየመጣ ያለው ኣደገኛው ፊውዳሊዝም እስከመጨረሻ ድረስ ገደብ የሌለው ሃብት የሚለው መርህን ዕየዘረጉ ነው ለምን በሃይል ካልሆነ ሌላ ኣዲስ ሃያላን ዕንደነ ቻይናና ህንድ ብቅ ዕያሉ ስለሆነ ዕነሱን ለማሸነፍ ነው። ልምሳሌ ደካማ ኣገርን በመያዝ ሃይላቸው ዕያደግ ስለሚመጣ ቻይናን፣ ህንድን፣ ራሻን ወዘተ መቋቋም ስለሚችሉ ነው። ኣገርን ሲይዙ ደሞ ደካማው ህዝብ man power ያገኛሉ ማለት ነው። (ዶር ኣብይ ይህ የቁጥር ዘዴን በመጠቀም መደመር ማለቱ ኣርቆ ሃሳቢነት የመስለኛል ዕውነት ኢትዮዽያን በሃሳቡ ውስጥ ካደረገ። ኣለበልዝያ መደመር ማለት ካረቦች ጋር ዕንቀላቀል ማለቱ ካሆነ ዕንደ ኤርትራ ኣረብኛን በመናገር፣ ኣረብ ዕንጂ ኣፍሪካው ኣይደለሁም ዕንዳይሆን ። ለምሳሌ ዕንግሊዝ ህንድን ቅኝ ባትይዝ ኖሮ ሃያል ኣትሆንም ነበር። የህንድን ወታደሮች በየ ኣለማቱ በተለይ በኣፍሪካና በካሪቢያን ደሤት ኣገር ኣድርጋ በዝብዛ ቆይታ ህዝቦቿን በሰሜን ኣሜሪካና በኦሺያንያ (በኣውስትራልያና በኒውዚላንድ) ኣስፋፍታ ኣለምን ማንቁርቱን ይዛለች። ጥሩ ዘዴ ለራሧ ኣደረጃጅታለች። የኢትዮዽያ ዘረኞች ደሞ ዕስከ ኣፄ ሃስላሤ ድረስ ዕየተቋቋመ የነበረው ዲሞክራሲ ባፍጢሙ ደፍተውት ዕንዴት ጏሮ መስርተን ኣናሳ ሆነን ዕያነስንና ዕየጠፋን ዕንሂድ ነው ነገሩ።

የግለሰብ ነፃነት ዕንጂ ፓርቲ ቡድን ቲፎዞ ታማኒነቱ ለኣገር ኣይሆንም። ከሌላው ፓርቲ ጋር ደሞ ሽኩቻ ስታድረግ ስለ ቡድንህ እንጂ ስላገር ኣታስብም። ፓርቲ ማለት ኣሁን ኣሜሪካን ዕየተገነዘበ የመጣው የማፍያ ቡድንን ከጊዜ በሗላ የሚፈጥር ነው ህዝብ ላይ የሚነሳ መንግስትን በመቆጣጠር። ከህዋሃት ዕንደተማርነው፣ የራሳቸውን ህዝብን በበዘበዙት ሃብት መከላከያና ኣጥቂን በመፍጠር ሃብቱን የበዘበዙትን ህዝብ ራሱን ዕየገደሉ ዕያጠቁ ፪፯ ኣመት መግዛት ኣምባገነን መሆን ችለዋል። ኣሜሪካም ኮርፖሬሸኖች የህዝብን ጉልበት በልተው ቀስ በቀስ ፖለቲከኞቹን ገዝተው መንግስትን ተቆጣጥረው ኣምባ ገነን ለመሆን እየተራመዱ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ባሜሪካ። የኢትዮዽያ ፖለቲከኞች የማንነታቸውን ታሪክና ነባር ዕሤትን ኣውጥቶ በመጣል የምራባውያንን ዲሞክራሲ ወይም ጥሩ ዕሤታቸውን ሳይሆን ኮፒ እያደረጉ ያሉት፣ ኣገራቸውንና ህዝብን ለማውደም የሚሰጣቸውን ትዕዛዝ በመቀበል ግን ኪሳቸው ዶልቶና ኣገሩን በህንጻ በማጨናነቅ ጊዜያዊ የሆነን ኣርቲፊሻል መስካሪ ዕንዲሆን ማስመሰል ነው። ርዋንዳ ይህ ምሳሌ ነው። መሪውም ኣደገኛ ነው። ስለዚህ ፓርቲን በመመስረት ኮፒ ኣድርጎ የዕውነት ዲሞክራሲ ኣይመጣም። በዘርህ ፓርቲን ብትመሰርት ይህው ህዋሃት ዕንዳሳየን በሌሎች ህዝብ ላይ ትግራይን ጠላትና ፈንጂ ረጋጭ ኣድርጎ ዕራሱ ብቻ ቁንጮ ላይ ሆኖ ለ፪፯ ኣመት ወንበዴው ቡድን ገዝቷል ተዝናንቶ። ለዚህም ነው ትልቅ ክብር በምራባውያን ህዋሃት ያገኘው። ኢቶኣስ በኢኣር ዕንደነገረን ብሃይል መግዛት ማለቱ ኣምባ ገነን ፋሸን ዕየሆነ መምጣቱና፣ ብልጽግናም ወደ ኣምባ ገነን መሄድ ዕንዳለበት ነበር የሚነግረን። ኣላስፈላጊ ጦርነተ ህዝብን ሆን ብሎ የማጥፋት ኣምባ ገነንነት ማለት ነው።

ኣንጎል ያለው ህዝብና መንግስት, ሌላ የኣገዛዝ ሲስተም በመፍጠር ከህዝብ ጋር መድረክ ከፍቶ መወያየት ጥሩ ብልሃት ነው ከሌላው ኣገርም ይሰራል የሚባለውን ሲስተም ኣጥንቶ መጠቀም።

Post Reply