Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 10889
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ህዝብ ለዐብይ አህመድ ያለድ ድጋፍ ዜሮ በወረደበት ሰዓት፤ ዐብይ ለሚመካበት መከላከያ ሰራዊትም ያለው የህዝብ ድጋፍም ዜሮ ወርዷል።

Post by Abere » 17 May 2022, 10:11

ህዝብ ለዐብይ አህመድ ያለድ ድጋፍ ዜሮ በወረደበት ሰዓት፤ ዐብይ ለሚመካበት መከላከያ ሰራዊትም ያለው የህዝብ ድጋፍም ዜሮ ወርዷል። የወደቀ ወይም ኮማ ውስጥ ያለን ከዚህ በላይ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡እስከ ምናውቀው ድረስ በዘመናችን እንደ ዐብይ አህመድ የህዝብ ድጋፍ ያገኘ መሪ አልሰማሁም - ምንም እንኳን በርካታ ኦሮሞዎች ተቃውሙ ቢኖራቸውም እና ድጋፋቸውን ቢነሱትም። የተቃውሟቸው ምክንያት ደግሞ አብይ አህመድ በጁሃር ሙሃመዲ እንድተካላቸው ነበር ፍላጎታቸው። ጁሃር በፈጣን እርምጃ የኦሮሙማ ራዕይ ሊያሳካ ይችላል የሚል ሲሆን የዐብይ አህመንድ እርምጃ ቀርፋፋ የኦሮሙማ የለውጥ ሂደት ነው በማለት። ይህ እውነታ ደግሞ አሁን በግልጽ እየታየ ነው - አብይ አህመድን ይደግፍ የነበረው ህዝብ ግልብጥ ብሎ አሁን ተቃዋሚ ሲሆን ኦሮሙማዎች ደግሞ ተገልብጠው የአብይ ደጋፊዎች ናቸው።አሁን ከጁሃር ዳውድ ኢብሳ ወዘተ ተቃውሞ አንሰማም። አንዳንዶች እንድሁ እንደ መራራ ጉዲና ከአንገት በላይ ይቃወማሉ እንጅ። ይህ ማለት አብይ ትንሽ ድጋፍ ያለው ከኦሮሙማ ወይም ኢትዮጵያ ብትኖ ካምፕ ነው ማለት ነው። በሌላ መልኩ ያረጋገጠው ነገር ቢኖር የአብይ ሙሉ ስብዕና 100 % በሃሰት የተገነባ ነበር። ቁም ነገሩ ኦሮሙማ በብዙሃኑ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ውግዝ ከመዐርዮስ የተባለ መሆኑ ነው። ታዲያ አሁን መሰረታዊ ድጋፍ ህዝብ የነሳው መሪ እርሱ ብቻ ሳይሆን መከላከያውም ድግፍ አጥቷል። ይህ ማለት በቀላሉ በጥላት ሊማረክ፤ትጥቁን ሊፈታ እና ሊሸነፍ ይችላል። በእርግጥም መከላከያ እጅግ ደካማ እንደ ሆነ በግልጽ ታይቷል አሁንም ደካማ ነው። አብይ አህመድ ምንም አይነት የይዘት ለውጥ ሳያደርግ የወያኔን ርዕዮት የስርዐቱን ሶፍትዌር ቋንቋውን በኦሮምኛ እና ኦሮሞዎች ብቻ በመቀየር አስቀጥላለሁ ብሎ ቢያስብም በግልጽ የእርሱ ወያኔያዊ ኦሮሙማ መንግስት ደቅቋል። በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ እንኳን ባለ ጎመኔውን ባለዛፍ የኦነግ ባንድራ ለማሰቀል ግብረ ሃይል ማሰማራቱ የቱን ያህል ጭምልቅልቁ ወጥቶ እንደ ፈራረሰ ይመሰክራል። ታዲያ አክ እትፍ የተባለ ስርዐት እንደ ት ይቀጥላል? ተጨማሪ ጥያቄ አለኝ። ወያኔ እንደ አለፈው ክረምት ወሎን አቋርጣ ሸዋን አጋምሳ ብትገሰግስ የወሎ እና የሸዋ አማራ አሁን ተገልብጦ ይደግፋታል ወይስ ይዋጋታል? የቅዠታሙ ኦሮሙማ መሪ ዐብይን ሊያምኑት ሊደግፉት ይችላሉ? በተለይ ወሎ ምንም ያገኘው ነገር የለም እርስት ግዛቱን ራያን ለወያኔ ስጥቶለታል የሞት ሞት ታግሎ አሸንፎ ሲያበቃ?
የውታፍ ነቃዮች መልስ አልፈልግም።