Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ዘላለማዊ የጉራጌ ከዋክብት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡ ሃብተ ጎርጊስ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ራስ ደስታ፣ ገብረ ማሪያም ጋሪ፣ በቀለ ወያ !!

Post by Horus » 17 May 2022, 02:23

ሊሴ ገብረ ማሪያም የፈረንሳይ ት/ቤት በስሙ የቆመለት ደጃዝማች ገብረ ማሪያ ጋሪ የ ደ/ች በቀለ ወያ አጎት ናቸው ። ጣሊያን ባይሮፕላን የደመሰሳት ጎጌቲ ከተማ (ሶዶ) ያገር ጌቶች፤ ራስ ደስታ ዳምጠው የመስቃኑ፣ ባልቻ ሰፎ የሜልኮው እና ሃብተጎርጊስ ዲነግዴ የጨቦው ... እኒያ ገናና የታላቁ ራስ ዘሚካኤል ተከታዮች የጉራጌ ክብርና ኩራት ምንጮች !!! ምስጋና ይድረሳችሁ ለተዋችሁልን ክቡር ሌጋሲ !!!!
በደ/ች በቀለ ላይ አርቲክል ..
http://tuckmagazine.com/2019/03/14/patr ... kele-weya/

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘላለማዊ የጉራጌ ከዋክብት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡ ሃብተ ጎርጊስ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ራስ ደስታ፣ ገብረ ማሪያም ጋሪ፣ በቀለ ወያ !!

Post by Horus » 17 May 2022, 14:19

የባንዳ ልጅ ከዳተኛ ሁላ ለምን በጉራጌ ላይ እንደ ሚቀኑኮ ልብ ብለን እናውቃለን !!


ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ዘላለማዊ የጉራጌ ከዋክብት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡ ሃብተ ጎርጊስ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ራስ ደስታ፣ ገብረ ማሪያም ጋሪ፣ በቀለ ወያ !!

Post by ethiopianunity » 17 May 2022, 21:56

ኣይ ያልታደለ ሕዝብ, በእምነት በስመ ልቦና በአርቆማሰብ የታነፀ ማሕበረሰብ መስዋእት አድርጎ ለቀጣዩ ትውልድ አገር ትቶ ያልፋል ታሪክ እንኳን ለነዚህ ጀግኖች እንዳይመሰክርላቸው ተነፍገዋል.
ካለ ታሪክ አገር የለም. እነ ኢቶአስ ኢአር ላይ በክፉ ስመ ልቦና የተመቱ በጎሳ ታሪክ አይጠቅምም ይላሉ. የነ ፕረዚደንት ዋሽንግተን ሊንከንን ወዘተ በደንብ በተለይ የበፊቶቹ መሪዎቻቸው ታሪክ ወጣቱና ኢሚግራንቱ ሳያጠኑና ፈተና ካላለፉ በሂወታቸው ስኬታማ መሆን በአሜሪካ ዘበት ነው. ሌሎችም አገራት የገባቸው በታሪካቸው በመመካት እንደነ ቻይና ብዙ ህዝብ በኮሚኒስት የሞተባት ከቁስሏና ከስህተቷ ተምራ በአለም እየመነጠቀች ትገኛለች. ቴዲዬ እንዳለው የሗላው ከሌለ የለም የፊቱ ሲል እሱ ነው የገባው.
እንደ ኢትዮጲያኖች በአለም ከመረብ መላሽ [ኤርትራ] እስከ ደቡብ ድረስ ከውጭ ጠላት ጋር ተዋድቆ ኢትዮጲያን እየወደቀ እየተነሳ ብዙ ጀግኖችን አፍርቶ እስከ 30 አመት አልፏል. ዛሬም ፈተናችን እንዴት የውጭ ጠላትን ለመታደግ ኢትዮጲያ መሪዎቿን ማውጣት አለባት ከዶር አብይ ጀምሮ የእውነት መሪ መሆናቸውን በታሪክ ላይ ተመርኩዘው [የተዛባና የጠላትን ታሪክ ሳይሆን]ማስመስከር እየተጠበቁ ነው.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘላለማዊ የጉራጌ ከዋክብት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡ ሃብተ ጎርጊስ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ራስ ደስታ፣ ገብረ ማሪያም ጋሪ፣ በቀለ ወያ !!

Post by Horus » 17 May 2022, 22:51

እኔ ሳይንሳዊ የሆነ ማረጋገጫ ወይም ሌላ ሎጂክ አቅርቤ የማረጋግጠው ነገር አይደለም። ግን ከ1960 እስከ 2022 ባሉት ዘመናት ያለፉት ትውልዶች ሊያደርጉ የሞከሩት የጦረነትና የማያባራ እርስበርስ ውድመት ባንድ በኩል እና በሌላ በኩል ይህቺን አገር ለማፍረስም ሆነ ያሰቡትን ለመገንባት አለመቻላቸው የነዚህ ሁሉ ተገጣዮች ጥረት መጨረሻው የራሳቸው ውድቀት ይሆናል የሚል ጥልቅ ስሜት ነው ያለኝ። ትግሬዎች 17 +2 = 19 አመት ተዋግተው የመፍትሄ ጭላንጭል እንኳ የላቸውም።

ትግሬዎች ሌላ 10 አመት ከኢትዮጵያ፣ ካማራ፣ ከኤርትራ እና እርስበርሳቸው ተዋግተው እንኳ አገር ልሁን ቢሉ ሌላ የ20 አመት ጦርነት ይጠብቃቸዋል ። ኤርትራዊያን ለ30 አመት ተዋግተው 30 አመት አገር ከሆኑ በጓላ (ከ60 አመት በኋላ) ከኢትዮጵያ ኢኮሲስተም አልተላቀቁም። ኦሮሞ የሰላም ምድር የሚሆነው እንደዛሬ የኢትዮጵያ ምድር እስከሆነ ነው እንጂ እራሱ ከ30 ጎሳዎች ጋር ድምበርተኛ ሕዝብ ነው ።

በአንድ ቃል የማንም ጂል የጎሳ ቅዠታም ተነስቶ ይህን አፈርሳለሁ፣ ይህን እቀርጻለሁ አለ እንጂ ኢትዮጵያ ማፍረስ የማይቻል ነገር መሆኗን የተገነዘቡት አይመስለኝም። አሁንም እየሆነ ያለው ያ ነው። የተወሰነ ሕዝብ አስጨርሰው፣ ንብረት አውድመው፣ እራሳቸው ወደመው፣ ደህይተው ከዛሬ 5፣ 10፣ 20 አመት በጓላ እዚሁ ባሉበት እናገኛቸዋለን።

በሱማሌ፣ ኦሮሞ፣ ትግሬና ኤርትራ ባለፉት 60 አመታት የ60 አመት ጦርነት ተደርጓል (30 አመት ኤርትራ + 20 አመት ትግሬና + 10 አመት ሌላው ተደማምሮ)። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ሕዝብ ነው ፤ ጦርነቱን ያደረጉት የትግሬና ኤርትራ ቁጥር ቀንሰን ማለት ነው። ይህ ነው ሃቁ ።

የትግሬ ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ የሚያመጣ እጅግ መሰረታዊ ለውጥ የለም ። ኢትዮጵያ የትም አትሄድም ! የሽብሩና የቀውሱ ባለቢቶች ሁሉ ወድመው ደምተው ሲበቃችሀው ያቆማሉ ። ይህ ነው እኔ በውስጤ የሚሰማኝ የታሪክ ሂደት !!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ዘላለማዊ የጉራጌ ከዋክብት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች፡ ሃብተ ጎርጊስ፣ ባልቻ ሰፎ፣ ራስ ደስታ፣ ገብረ ማሪያም ጋሪ፣ በቀለ ወያ !!

Post by Horus » 18 May 2022, 03:22

ንበል እንከነ ! እንበል እምቢ !! ይዝጌር ነሽ ኢትዮጵያ ... ኢትዮጵያ የእግዚአብሄር ነሽ!

Post Reply