Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 16 May 2022, 23:27

አቢይ አህመድ የታላቁ የኢትዮጵያ አባት አጼ ምኒልክ ፈለግ ላይ ቆሞ ኢትዮጵያን በሚኒልክ ፋና አንድ አድርጌ ልመራት ራዕይ አለኝ ያለ ቀን እጅግ ተደስቼ ክበር ተሸለም ብዬዋለሁ! ያን ያልኩት እኔ ብቻ አይደለሁም። ዛሬም ያን ቢያደርግ ተመልሼ አሞግሰዋለሁ። ያ አልሆነም! ፈረንጆች ይህን መሰል ኩነት 'የሸማች ጸጸት' ወይም buyers remorse ይሉታል ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእኔ ቢጤዎች በሸማች ጸጸት ውስጥ ይገኛሉ።

የእኔ ጽዋ ለመጨረሻ ግዜ ሞልቶ የፈሰሰው ክቡር የኢትዮጵያ ዜጎች ታሪካዊና እውነተኛው ሰንደቅ አላማቸውን መስቀል አትችሉም የተባለ ቀን ነው ። እያንዳንዱ የህበረተሰብ ክፍል በአቢይ ላይ ላለው ጸጸት የራሱ ምክንያት እንዳለው አውቃለሁ ። ስለሆነም በአሁን ወቅት አቢይ አህመድ ...

(1) የኤርትራ ድጋፉ ወርዷል
(2) የአማራ ድጋፉ ታች ደርሷል
(3) አፋርም እንደ ነገሩ ነው
(4) ያዲስ አበባ ድጋፍ መሰረቱ የለም
(5) ዲያስፖራ መጸጸት አይደለም አዝኗል
(6) ደቡብ ምናልባትም አዲስ ከተፈጠረው ደቡብ ምራብ ውጭ ድጋፉ መዝቀጥ ብቻ አይሆን ሰው እሱን ማመን አቁሟል
(7) ሲዳማና ኦሮሚያ በሻሸመኔ ላይ ተፋጠዋል
(8) ስለ ሱማሌ ክልል አላውቅም
(9) አሜሪካኖች ሁለተኛ አቢይ ን አያምኑም
(10) ስለ ኬኒያ፣ ዩጋንዳ፣ ሱዳን ፣ ግብጽ አቁም ምንነት ሁሉም ያውቃል ።

ይህ ሁሉ ለምን ሆነ? የአቢይ መሰረታዊ የመሪነት ስህተትና ውድቀት ምን ነበር?

በእኔ እምነት የአቢይ አህመድ መሰረታዊ ስህተት ኢትዮጵያን እንደ ገና ጠፍጥፌ እሰራታለሁ የሚል ትግሬዎች የጀመሩትን ግብዝ መንገድ ለመቀጠል ይህና ያንን ሲሞክር በራሱ ትብታብ ተጠምጥሞ እየወደቀ ያለ መሪ ነው።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ የጀርባ አጥንት ኢትዮጵያ የምትባል ታሪካዊ አገርና ብሄራዊ ምንነቷ ነው ። አቢይ ለጥቂት ግዜ ባፉ ያን ሃቅ ጠቃቀሰና በተግባር ለ30 አመት ተሞክሮ የወደቀው የጎሳና የዘውግ ኢትዮጵያን በዚህ በዚያ ጎሳ አምሳል ለመቅረጽ የሚታለመው ህልምና የሚሰበከው ምናብ ውስጥ ገብቶ የቁልቁለቱን መንገድ ወሰደ ።

አቢይ አህመድ እራሱ ሌቦች ከሚላቸው የጎሳ መሬት ነጋዴና የሙስና መሳፍንቶች ጋር አብሮ ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅና ታሪካዊት አገር እንዲ የጨረባ ተዝካር አድርጓት ስኬታማ መሪ ሊሆን ከቶም አይችልም።

የወያኔ ትግሬ ለራሱ ጎሳ እንዲመች የቀረጸው ስርዓት በመጠቀም ተረኛው ኦሮሞን ከፍ አደርጋለሁ የሚለው ድብቅ ሞቲቭ ሌላው የተበላ ዕቁብ የሚለው መንገድ ነው ። ለዚህ ነው የኦሮሞ መሪዎች ቃልና ተግባር የሚጣረሰው!

አሁን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ፣ ወዳጅም ጠላትም ይህን የነአቢይ መሰረታዊ ድክመት አውቆታል። አሜሪካም ቻይናም፣ ሩስያም አውቀውታል። አቢይ በኢትዮጵያ ጽኑ የጀርባ አጥንት የቆመ መሪ አልሆነም ።

ያ እንዲሆን በግድ፣ በግድ የትግሬ ባንዳዎች የጠፈጠፉትን ስርዓት ኢትዮጵያዊያን በሚጠይቁት መሰረት መለወጥ እና መጠገን ያስፈልጋል፤ እጅግ በአስቸኳይ!!!
Last edited by Horus on 17 May 2022, 00:14, edited 2 times in total.

Temt
Member+
Posts: 5279
Joined: 04 Jun 2013, 22:23

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Temt » 16 May 2022, 23:54

Horus, I believe PMAAA has been trying to appease everybody, every group or organization. In my opinion, he wants to be praised by everybody and he has a showman-type personality, and certainly, he is not shy about bragging rights. Because of that, many times he utters words and phrases of appeasement to people and organizations of the likes of Weyanes! He is also a flip-flopper and dishonest with what he believes. Also, he is noncommittal to any principled stand. He is willing to change his allegiance from west to east and vice-versa abruptly if he believes an opportunity is calling. I do not believe Ethiopia needs an opportunist leader for it goes without saying that the Ethiopians may not pinpoint where exactly such leadership may lead them.

Axumezana
Senior Member
Posts: 13214
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Axumezana » 17 May 2022, 00:15

The Analysis on Abiy is superficial.

1st the existing Ethiopia was not only restructured by TPLF but with OLF and other nations and nationality parties. Hence, whether TPLF is around or dead the existing structure of Ethiopia and it's constitution shall survive with dynamic revisions and refinements.

2d The Minilik Ethiopia was only good for the archaic unitary Ethiopia dreamers not for most of the citizens of Ethiopia . It looks you may have misunderstood Abiy and expected he will bring back the Minilik Ethiopia but that was not realistic expectation.

3rd Abiy has already committed strategic and grave mistakes over the last four years but he has to be given a 2nd chance incase he apologies and is ready to make genuine changes.

4th Ethiopia under Abiy is in a perfect mess and turbulence in the areas of security, economy, job creation, corruption, accountability etc. He should take the blame and come up with a solution

5th Peace with TPLF, OLF and FANO is mandatory. No to war, Yes to peace!
6th Last but not list #Bring Back Our Access to Red Sea!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 17 May 2022, 00:39

Temt
በትክክል። መደመር የሚባለው ኤክሌክቲክ ጽንሰ ሃስብኮ ያ ነው ። እኔ የጀርባ አጥንት የለውም ያልኩት ያነው ። እዚህ ፎረም ላይ ብዙ ያልኩት ነገር አለ፤ እሱም አንድ የፖለቲካ መሪም ሆነ ተዋናይ ገፊ፣ ነጂ ሞቲቮች አሉት ። እነሱም ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ዝና እና ክብር (ማንነት) ናቸው ። አቢይ አህመድ ቁጥር 1 ነጂ ፍላጎቱ ዝና ነው፤ ለመወደድ መጣር ነው፣ ለመታወቅ፣ ሰለበርቲ ለመሆን ነው። ሁለተኛ ፍላጎቱ ስልጣን ነው ። ለምሳሌ ሚኒስትሮችና የፓርቲ ማዕከላዊ አባላት አገር ከሱ ጋራ ይመራሉ የሚባሉት አንድ ክፍል ውስጥ ሰብስቦ እንደ 6ኛ ክፍል ተማሪ እሱ ያስተምራል እነሱ ደብተር ላይ ይገለብጣሉ ። እጅግ እጅግ ያሳፍራሉ። እሱ ግን ያን ነገር ኢጆይ ያደርገዋል ። ያ ከፍተኛ የመሪነት ድክመት ነው ። ታላላቅ መሪዎች the party of equals ይባላሉ ። ታላቅ መሪ ለራሳቸው ታላቅ የሆኑ ተፎካካሪ፣ ብቃትና የራሳ መተማመን ባላቸው ሰዎች ይከበባል ። በትናንሽ ተከታይ ደቂቃን የሚከበብ መሪ እራሱ በራሱ ብቃት ላይ ችግር ያለው መሪ ነው ።

አው ያቢይ አንደኛ ሳይኮሎጂያዊ ፍላጎት ዝናና መወደድ ነው ። አሁን ጥያቄቅ መወደድ በማ? የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በሆኑት ኢትዮጵያዊያን መወደድ ከፈለገ የኢትዮጵያ አጀንዳ መምራት ይኖርበታል ። አሁን ማንም አይወደኝም ብሎ ወደ አምባ ገነን መሪነት ሊሸጋገር ይችላል። ያ የሚታይ ይሆናል ። ችግሩ አንድ የፖለቲካ መሪ ስልጣንና ዝና መፈለጉ አይደለም ዋናው ችግር ። ዝና ማትረፍ የሚችለው ከማ? ስልጣኑን ለምን አላማ? ተብሎ ሲጠየቅ መልሱ ኢትዮጵያዊያን ይሚል እንጂ በየጥሻው ስር ያሉና 1000 አይነት ግላዊ ፍላጎት ያላቸውን ጎሳዎች ፓንደር የሚያደርግ ከሆነ አሁን ያለበት ውድቀት ጋ ይወስደዋል ።

ኢትዮጵያዊነትና የጎሳዎች ጸረ ኢትዮጵያዊነትን አንድ አደርጋለሁ የሚለው የመደመር ምናብ የትም እንደ ማይሄድ አሁን ሁሉም አይቶታል። መደመር የተረሳ ቃል ነው ! የኢትዮጵያ አንድነት የሚለው ክቡርና ታሪካዊ ቃል ነው! ያ ለሱ በቂ ነበር !!!

ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by ethiopianunity » 18 May 2022, 10:46

You are assuming Aby had pro Ethiopia intention in the first place? Aby' s heart beat could be one of the three: 1. either he has pro ethio intention and as the chaos of the world continues he can't be expected to solve issues because foreigners want that and it is blind for most not to see that. 2. like Tplf, for 5 years who pretended to rule properly, changed tactics it was ethnic rule until Tplf got hold of Ethiopia well. Aby is maybe following this method, his intention could be all along Olf domination. 3. Aby could also be following Arab integration method, like Eritrea and reduce or destroy everything Ethiopia. What ever the plan, the usual suspect outsiders method, history shows us since the 70s their support is always weak nation and creation of war lords against citizens. If Aby goes along with this, like Tplf, Olf will be the war lord, and nailing the coffin of Ethiopia. I think that is what the liberation fronts of course, Olf,Tplf and shabia and foreigners who have now say on Ethiopia issue, wants him for Olf leadership. Even for the Oromos, just like Tigrayans, in the end, the picture will not be attractive.

Right
Member
Posts: 2722
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Right » 18 May 2022, 11:21

Horus,
Your analysis is good. This was the Horus that attracted my attention a few years ago before one of the group you identified with joined the government and put you off balance.

It is true, based on what he said, we all thought Ethiopia finally got a leader that might get it done until we found out it is a con job.

People can have different opinion and that should be commendable. As long as opinions are based on principle, honesty and respect. After all this country belongs to all of us.

I will never have any respect to those who gives and deny their support to the people of Ethiopia based on self interest, greed, ethnicity and political agenda.
I advocate for this kind of people to be shot on public square.

sesame
Member+
Posts: 5764
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by sesame » 18 May 2022, 11:35

For me, what he did last Christmas was the worst crime that any leader can commit. He invited a million Diaspora Ethiopians to come back home. Many answered his call. The #nomore movement was spreading like a wild fire. A huge #nomore demonstration was planned in Addis in which millions would have participated. And then, Abiy did the unthinkable. He released the likes of Sibhat Nega and effectively killed the #nomore movement. He back-stabbed Ethiopians. Why, he would want to do that is not clear to me. But I lost all respect for the man then. I felt sorry for Ethiopians.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 18 May 2022, 13:09

sesame:
በትክክል፤ ሰው በቢሄቪየሩ እንጂ በቃል አይለካም። ያኔ የሰራው ስራ የደበቀውን እውነት ገሃድ አወጣው። ያ ሁሉ አይተን ግን አቢይ 180 ዲግሪ ለምን ዞረ ለሚለው ምክኛት አይታወቅም ነበር ። ያ ምክያት ብርሃኑ ጁላና ደብረጽዮን ባሜሪካ ማካይነት የሆነ አፍሪካ ደሴት ላይ ያደረጉት ስምምነት መሆን አለበት ።

አዲስ አምባአደር ዲሲ የተላከው፣ ያለም ባንክ አዲስ ብድር ወዘተ ከዚያ ጋር የተያያዙ ናቸው

የኖሞር ንቅናቄና የኢትዮጵያ ሕዝብ አሜሪካ ውጡ ያለ ግዜ ነው አሜሪካኖች በረቀቀ መንገድ አቢይ አምቢ የማይለው ጉቦ ሰጥተውት ሕዝብና አገሩን እንዲከዳ ያደረጉት ። ስለዚያ ነበር ያ ድንገተኛ ዲያስፖራን መክዳት፣ ኢትዮጵያዊያንን ስለባንዲራቸው መግደል የመጣው።

ይህ ያሜሪካና ያቢይ ዱለታ ሰፊ ከሆነው ያፍሪካ ቀንድ፣ ሱማሌ፣ ኤርትራ፣ ቻይና ወዘተ ጋር የተያያዘ ይመስለኛል ። ለኢትዮጵያ ዜጎች ግን አንድ ግልጽ ያደረገው ነገር አለ ። አቢይ የኢትዮጵያዊነትን ፈረስ መጋለብ አለመቻል አይደለም፣ እራሱ ፈረሱን ነው የፈራው። ያኔ ተነስቶ የነበረው የኢትዮጵያዊነት ፈረስ ከኦሮሞነት ሆነ ሌላ የጎሳ ፈረሰ ጋር በቀጥታ ተጻራሪ ስለሆነ ነው። ግን እኛ ኢትዮያጵዊያን አገራችንን ስለ ወደድን አቢይ ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲለን ወደድነው፣ አለመሆኑን ስናውቅ ጠላነው። ያ ነው ትክክለኛ አመለካከት እንጂ ምንም ነገር ከፋክት በፊት መደምደምና መፈረጅ የኮኚቲቭ ስህተት ነው ።

ኦሮሞች ተረኝነት እንደ ማይሰራ ገብቶአቸው እንደ ገና የኢትዮጵያን አጀንዳ ካነሱ እንዲሁ እንደ ገና እንደግፋቸዋለን ። በትግሬ ባንዳዎች መንገድ ከጸኑ ከዚህ በፊት እንደ ወደቁት መንግስታት ሁሉ ታግለን እናወርዳቸዋለን ። ይህ የታሪክ ሕግ ነው ።

በአሁን ወቅት የቦሌ ቋንቋ ከትግርኛ ወደ ኦሮሞኛ ተለውጧል። ከላይ እስከ ታች ኦሮሞ ነው ። ፖሊሱ ኦሮሞ ነው ። አዲስ አበባ የሌባና የማጅራት መቺዎች መናሀሪያ ሆናለች ። ሰው ጨለም ካለ መንገድ መውጣት እየፈራ ነው። ዲያስፖራው እንደ ጉድ ይዘረፋል! በአንድ ቃል ወያኔ የጠፈጠፈው የጎሳ ቂጣ በኦሮሞች እጅ ፍርክስክሱ እየወጣ ነው ።

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4063
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Za-Ilmaknun » 18 May 2022, 13:40

The man has no principled stand. His leadership style is mostly based on seeking immediate gratification that easily gives away the long term good for all. He has no integrity. True leadership calls for integrity, for it is is the very core of influence. Living the values they profess is what gives true leaders credibility and entice others to place their trust in them. True leaders are able to say “do as I do” rather than just “do as I say”, for they lead by example.

Because of his flip-flopping on almost all issues, he has become one of the very detested and mistrusted leader. His own supposed constituency is gravely concerned about his actions and directions. He is now resorting in to abduction of opponents, promoting servitude, and blaming others for his failure. We are consistently witnessing that he is subtly sabotaging the will of the people to depart from identity politics by his passive-aggressive strategy of friendly candor and compliant to camouflage his sinister intentions. The end is in sight!!!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 18 May 2022, 14:03

There is no physics without energy; there is no politics without power.


Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 18 May 2022, 15:07

አበበ ገላው መለስን የገደለበት ቀን 10ኛ አመት ዝክር፤ መልዕክት ለአቢይ አህመድ አሊ !


union
Member+
Posts: 6044
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by union » 18 May 2022, 16:42

Exactly
Right wrote:
18 May 2022, 11:21
Horus,
Your analysis is good. This was the Horus that attracted my attention a few years ago before one of the group you identified with joined the government and put you off balance.

It is true, based on what he said, we all thought Ethiopia finally got a leader that might get it done until we found out it is a con job.

People can have different opinion and that should be commendable. As long as opinions are based on principle, honesty and respect. After all this country belongs to all of us.

I will never have any respect to those who gives and deny their support to the people of Ethiopia based on self interest, greed, ethnicity and political agenda.
I advocate for this kind of people to be shot on public square.

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9755
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by DefendTheTruth » 18 May 2022, 16:43

sesame wrote:
18 May 2022, 11:35
For me, what he did last Christmas was the worst crime that any leader can commit. He invited a million Diaspora Ethiopians to come back home. Many answered his call. The #nomore movement was spreading like a wild fire. A huge #nomore demonstration was planned in Addis in which millions would have participated. And then, Abiy did the unthinkable. He released the likes of Sibhat Nega and effectively killed the #nomore movement. He back-stabbed Ethiopians. Why, he would want to do that is not clear to me. But I lost all respect for the man then. I felt sorry for Ethiopians.
Yes, there was a huge and momentous #NOMORE and the rallying of the diaspora behind the government was unprecedented.

But huge rallies around the world and that #NOMORE couldn't feed the starving nation of over 120 millions.

#NoMore and others have some degree of freedom to stay the course, but the government has and had many obligations to fulfil all at the same time.

If America's debilitating sanctions continued as it started before a year or so up to now, then the majority of Ethiopian people would have been at each other's throats by now.


Any party has just its own interest at a given time in sight, but government is duty bound to have many many interests at the same time to tend to.

Horus' basic problem is that he starts from false premises and makes the wrong conclusion as a consequence. He thinks Abiy Ahmed is a king who could impose anything on everybody as a government policy. He also permanently considers that disobeying the rule of law and just pursuing any issue he or his group deemed right is the right way to go. A fatal error in my view.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 18 May 2022, 19:38

DTT

የኔ ህሳቤ የሎጂክ ስህተት ካለው ያን ስህተት አንድ ሁለት ብለው ማሰረዳት ያንተ ስራ ነው ። አንተ መለስን፣ ወያኔ ስቃወም ሁሉ ትቃወመኝ ነበር። ምን አይነት የፖለቲካ ጥቅም እንዳለህ ድሮ ጀምሬ አውቃለሁ ። እኔ የፖለቲካ ቲፎዞ አይደለሁም ። የራሴ የኢትዮጵያ አጀንዳ ይዤ ሌሎችን በዚያ አጀንዳ ልክቼ ኢትዮጵያን ሲያራምዱ ደግፌ ሲወድቁ የምቃወም ሰው ምሁር ነኝ።

አቢይ አህመድን ዘ ቤኒፊት ኦፍ ዳውት ሰጥተነዋል! አቢይ ትልቅ የታሪክ እድል አግኝቶ ነበር ። በፍትነት እያባከነው ነው! ሞኝና ገንዘቡ እንደ ሚባለው ማለት ነው። ታሪክ የሚሰራ ሕዝብ ነው። አቢይ አሜሪካኖች ሊያነሱት ሲሉ ተላላኪ አልሆንም፣ እኔ ከነሚኒልክ ዉሃ የተቀዳሁ ነኝ አለ። ግና ጥርስ ነቅሎ ያሳደገው የጎሳ መሰረቱ ስቦት አህያ ካመዱ ሰው ከዘመዱ ሆነ ነገሩ ሁሉ።

ታላቅ መሪ የምትሆነው፣ ታላቅነት የምታገኘው ከታላቋ ኢትዮጵያ ብቻ ነው! ካሜሪካም አይደለም! ከሆነ ጎሳህም አይደለም! ያቢያ አላማ አሜሪካንን አለማስቀየም ከሆነ የምኒልክን ነጋሪት ማን ጎሽም አለው? እንደ ማንኛውም ያፍሪካ ቅኝ ተገዥ መሪ ነኝ ባይ እዚያው ከጌቶቹ ጋር መጨረስ ነበረበት!! ልብ በል መሪን የሚፈጥሩ ሕዝቦች ናቸው። አቢይ ብቁ መሪ ነው ወይ አይደለም ብለው የሚወስኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው ።

አሁን ውሳኔና ፍርዳቸውን በትግስት ጠብቅ! The people, the people alone are the makers of history! ይህ ማክሲም ዝንፍ አይልም !

Right
Member
Posts: 2722
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Right » 18 May 2022, 23:30

DTT,
But huge rallies around the world and that #NOMORE couldn't feed the starving nation of over 120 millions.

Is this the best excuse you can come up with?
Being dictated in exchange for a hand out? You know if Abiye is not capable of leading a nation (which I believe is beyond his ability) then he has to let other capable people do it. No one is putting a gun on his head to be the PM of Ethiopia. He forced himself on Ethiopians and now he is selling our interests for cash.
However demeaning and embarrassing, at least you are honest and said the truth.

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Assegid S. » 19 May 2022, 08:34

ሰላም Horus; ባስቀመጥካቸው ነጥቦች ላይ እኔም እስማማለሁ። ለምን? ለሚለው ጥያቄም፥ አብዛኛው ሰው የእኔን ሃሳብ ጠቅለል ባለ መልኩ ገልጾታል፤ በተለይም Temt። Thank you ወንድም Temt።

ከዛ ባለፈ ግን፦ የER ተሳታፊዎች ከላይ ከጠቀሱት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታዎች (ምክንያቶች) በተጨማሪ … በወርቅና ብር የተቀረፀ መስቀል አንገት ላይ ማንጠልጠል ብቻ በራሱ "ክርስቶስን መምሰል" አድርገው የሚቆጥሩ እምነት የለሽ ሰባኪዎችና "ትንቢት" ተናጋሪዎችም ሌላው ለሰውየው መውደቅ አስተዋፆ ያላቸው ስውር እንቅፋቶች ናቸው።

ይህ ብቻም አይደለም። ጠቅላይ ሚንስትሩ ገና የሰባት ዓመት ልጅ ሳሉ በእናታቸው (ነፍስ ይማር!) ትንቢት እንደተነገረላቸውና ይህ የስልጣን ቦታም ቀድሞ እንደታየላቸው ያምናሉ። ለእናታቸውና ስለልጃቸው ለነበራቸው "ራዕይ" ትልቅ አክብሮት እንጂ ፍፁም ተቃውሞም ሆነ ነቀፋ የለኝም። ችግሩ ግን ጠቅላይ ሚንስትሩ ስኬታማ መሪ ነኝ ብለው የደመደሙት ያኔ ገና የሰባት ዓመት ህፃን እያሉ መሆኑ ነው። ለምን? ምርጫቸው ከሰው ድምፅ ሳይሆን "ከአምላክ ፈቃድ" የመጣው ነው ብለው ስለሚያስቡ።

የትኛውንም አይነት ስህተት ቢሰሩ፣ በየትኛውም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መርህ ቢጎዙ፣ ስልጣኑ ከአምላክ የተሰጣቸው ነውና በተዓምራት ውሃው የወይን ጠጅ፣ ባህሩ ደግሞ ደረቅ መሬት እየሆነ ሰኬታማ፣ አሸናፊና አሻጋሪ እሆናለሁ ብለው ያስባሉ። ስለዚህ መሬት ላይ ሲፈስ ለሚያዩት ደምና ለሚሰሙት እሮሮ ዓይናን ጆሮ ለመስጠት አይፈልጉም። ሌላው ቀርቶ … ክፉን አይቶ እንዳላየ ማለፍና ስለበጎ ነገር ብቻ ማውራት (positive thinking) "አሸናፊ ያደርጋል!” የሚል እጅግ በጣም አደገኛ ፍልስፍና አላቸው። እዚህ ላይ … ህይወት ሁልጊዜም real እንጂ ideal እንዳልሆነች መገንዘብ ያስፈልጋል። የስነ ልቦና ምክሮችና አስተምሮቶች መሲህ ሆኖ የሚታየው “How to Enjoy Your Life and Your Job”, “Life Changing Secrets”, “How to Stop Worrying and Start Livingetc የሚሉ በርካታ መፅሐፍቶችን ለአንባብያን በማብቃት ትልቅ ስምና ዝና የነበረው ደራሲ … Dale Carnegie (RIP) … ህይወቱና ፍፃሜው ምን ይመስል እንደነበረ ቆም ብሎ ከሁሉም angle መመርመሩ ጠቃሚ ነው።

የሆኖ ሆኖ ... ወደ ሌላ አቅጣጫ ሳልጓዝ፥ ጠቅላይ ሚንስትሩ በኣምላክ ንግርትና ትንቢት ወደ ስልጣን የመጣ ሁሉ የሚጓዝበት መንገድ "ለበጎና ለበጎ ብቻ ነው!” ብለው ስለሚያስቡ ተሳስተዋል። በኣምላክ ፈቃድ የመጡ መሪዎች ተግባርና ምሪት አውዳሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ ብቻ ሳይሆን አምላካዊ ምሪት የነበረው መሪነታቸው እንጂ አመራራቸው እንዳልሆነ ሊገነዘቡ የቻሉ አልመሰለኝም። ስለዚህ ... ቆም ብለው እርምጃቸውን ብቻ ሳይሆን የከበቡዋቸውን የእምነት ሰዎችና ስለ እርሳቸው የሚያዥጎደጉዱትንም "መገለጥ" በማሰተዋል ለመመርመር ፍላጎት የላቸውም።

ከዛ በተረፈ ግን … በተራ ቁጥር 8 ላይ… " ስለ ሱማሌ ክልል አላውቅም" ላልከው። የሶማሌ ክልል የተረጋጋና ከጠቅላዩ ሐሳብ ጋር አብሮ እየተጓዘ ያለ የሚመስለው … በዋነኛነት አሁን ባለው አመራር ጥንካሬ ቢሆንም፥ የጎረቤት ሀገር ሱማሊያ የፖለቲካ አቋምም ትልቅ ድርሻ ነበረው። ነገር ግን አሁን፣ የቀድሞው ፕሬዚደንት (ፎርማጆ ) ከስልጣን ስለተወገዱ … ኣፍቃሪ-አሜሪካን ከምትሆነው ጎረቤት ሀገር የሚወረወረው ተጻራሪ አይዲዮሎጂ ክልሉን ሌላው የከፍተኛ ቀውስና አለመረጋጋት ቀጠና ያደርገዋል የሚል ግምት አለኝ። ወይ ሰውየው ወደ ኣሜሪካን … ወይ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚደንት ወደ ብልፅግና ካልተደማመሩ በስተቀር። አለበለዚያ፦ ጠቅላይ ሚንስትሩና ክልሉ መለያየታቸው የጥቂት ጊዜ ጉዳይ ነው።

መልካም ሰንብት, Horus

DefendTheTruth
Member+
Posts: 9755
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by DefendTheTruth » 19 May 2022, 10:14

Horus wrote:
18 May 2022, 19:38
DTT

የኔ ህሳቤ የሎጂክ ስህተት ካለው ያን ስህተት አንድ ሁለት ብለው ማሰረዳት ያንተ ስራ ነው ። አንተ መለስን፣ ወያኔ ስቃወም ሁሉ ትቃወመኝ ነበር። ምን አይነት የፖለቲካ ጥቅም እንዳለህ ድሮ ጀምሬ አውቃለሁ ። እኔ የፖለቲካ ቲፎዞ አይደለሁም ። የራሴ የኢትዮጵያ አጀንዳ ይዤ ሌሎችን በዚያ አጀንዳ ልክቼ ኢትዮጵያን ሲያራምዱ ደግፌ ሲወድቁ የምቃወም ሰው ምሁር ነኝ።

አቢይ አህመድን ዘ ቤኒፊት ኦፍ ዳውት ሰጥተነዋል! አቢይ ትልቅ የታሪክ እድል አግኝቶ ነበር ። በፍትነት እያባከነው ነው! ሞኝና ገንዘቡ እንደ ሚባለው ማለት ነው። ታሪክ የሚሰራ ሕዝብ ነው። አቢይ አሜሪካኖች ሊያነሱት ሲሉ ተላላኪ አልሆንም፣ እኔ ከነሚኒልክ ዉሃ የተቀዳሁ ነኝ አለ። ግና ጥርስ ነቅሎ ያሳደገው የጎሳ መሰረቱ ስቦት አህያ ካመዱ ሰው ከዘመዱ ሆነ ነገሩ ሁሉ።

ታላቅ መሪ የምትሆነው፣ ታላቅነት የምታገኘው ከታላቋ ኢትዮጵያ ብቻ ነው! ካሜሪካም አይደለም! ከሆነ ጎሳህም አይደለም! ያቢያ አላማ አሜሪካንን አለማስቀየም ከሆነ የምኒልክን ነጋሪት ማን ጎሽም አለው? እንደ ማንኛውም ያፍሪካ ቅኝ ተገዥ መሪ ነኝ ባይ እዚያው ከጌቶቹ ጋር መጨረስ ነበረበት!! ልብ በል መሪን የሚፈጥሩ ሕዝቦች ናቸው። አቢይ ብቁ መሪ ነው ወይ አይደለም ብለው የሚወስኑት የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው ።

አሁን ውሳኔና ፍርዳቸውን በትግስት ጠብቅ! The people, the people alone are the makers of history! ይህ ማክሲም ዝንፍ አይልም !
Yes, in my view your claims lack one, if not more, basic logical tenets of government based on a party system.

Abiy Ahmed is accountable to his party, more than anybody else. If the party says tomorrow NOMORE, then he has to comply ASAP.

Ethiopia is governed by a party, not by an individual. The partys compete for power and one of them (or caolation of them) will win and overtake the government.

The party in power in Ethiopia has won a relatively fair and free election last summer and is now entitled to rule. Those who have lost have to concede their lose.

If a party loses the election and still seeks to govern (as a sort of shadow government or somehting else) then there is no meaning in winning or losing an election.

You are demanding from Abiy Ahmed to implement the programs of those who have lost in the election, by-passing those who actually won the election and put him in office to implement their own agenda.

This is a blunder of democratic rights!

If there is no logical flaw in such a claim, then there will not be any anywhere else as well.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Horus » 19 May 2022, 13:15

አሰግድ
አመሰግናለሁ ። በልጅነቴ ባማርኛ ትርጉም ያነበብኩትን የዴል ካርኔጅ 'የሰው ጠባይና አብሮ የመኖር ዘዴ'ን አስታወስከኝ ። እኔም ውይይቱን ወደ ሌላ ርዕስ መለወጥ አልሻም እንጂ ባነሳሃው ቁልፍ ነጥብ ላይ ብዙ ማለት እችል ነበር። ግን አንድ ሁለት ነገሮች ነግሬህ ላቁም ።

በሳይኮሎጂስቶች ፕሮፋይል ማድረጊያ መንገድ ከሄድን አቢይ አህመድ ከአባቱ ጋር ሳይሆን ከእናቱ ጋር አይደንቲፋይ የሚያደርግ ሰው ነው ። የአቋሙ መዋዠቅ የሚመጣው ከዚያ ፐርሰናሊቲ መሰረት ሊሆን ይችላል።

መሪና ባለስልጣን ለመሆን የተወልድኩ፣ የተመርጥኩ ሰው ነኝ የሚለው ሚቶሎጂ ወይም ተረት በትክክል ቢጠቀምበት ቢያንስ ጥሩ መስፍን ሊያደርገው ይችል ነበር ። ያ ሚትዝም ተረትም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ስለማያምንበት ለስብዕናው ምሰሶ አልሆነም ። ለምሳሌ ስልጣንና እርካብ በሚለው ጽሁፉ ሃሳብ የሚወስደው ከነ ማኪያቬሊ፣ ሱን ጹ እና ሌሎች ጥንታዊ የፖለቲካ አገዛዝና የዉጊያ ብልሃተኞች ከጻፉት ነው ።

ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ 'መደመር' የሚለው ሃሳቡ አንተም በትክክል እንዳልከው የወሰደው ከ'positive psychology' ነው ። በእኔ እምነት የአቢይ አህመድ ጉሩ ምህረት ደበበ የተባለ ሳይኮሎጂስት ነው ። ምህረት ደበበ Mindset እያለ የሚያስተምረው ህሳቤ Carol S. Dweck, Mindset:The new psychology of success (2006) ብላ የጻፈችው የፖዚቲቭ ሳይኮሎጂ አንድ ትንሽ ቁራጭ ሃሳብ ነው ። ፕሮፌሰር ድወክ የስታንፎርድ መምህር ናት ። ፖዚቲቭ ሳይኮሎጂ አሁን እጅግ ግዙፍ ፊልድ ነው። ምህረት ደበበ ይህን Growth Mindset የተባለውን ህሳቤ ወስዶ ነው አሁን አቦይ መደመር እያለ ላይና ታች የሚልበት ፍሬምወርክ ።

አቢይ ድሮ እንደ ጀመረው ከማኪያቬሊ ወደ ዘመናዊ የፖለቲካ ፈላስፎች ወደነ ሩሶ፣ ሎክ፣ ወይም ወደነ ምኒሊክና አታቱርክ ማደግ ሲገባው ኢፖልቲካዊ ወደ ሆነው ፖዚቲቪዝም፣ ሃይማኖት፣ ሄደ። ለምሳሌ service leadership ተብሎ ምህረት ደበበ ሚኒስትሮችን የሚያሰለጥንበት ቲኦሪ ከክርስቶስ አገልጋይነት በሜታፎር የተወሰደ ውዥንብር ነው ።

እንደምታውቀው ምህረት ደበበ የአፍሪካ ልህቀት አካዳሚ ስራ አስኪያጅና የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ አሰልጣኝ ነው ። እናም ልነግርህ የፈለኩት ያነሳሃው የፖዘቲቭ ሳይኮሎጂ ጉዳይ አንዱ ቁልፍ ነገር ነው ። አቢይ የፖለቲካ እንሰሳ ሆኖ መመራት ያለበት በፖለቲካ ሳይንስ መሆን ሲገባው ከሃይማኖትና ሚቶሎጂ የተወለደው፣ ሃሳብ እንዴት ቁሰ አካላን ይገዛል (mind over matter) የሚባለው ውዝንብር ውስጥ ገብቶ ሲዋዥቅ ይገኛል ።

ሳይኮሎጂ ቦታ አለው። ሃሳብ ቦታ አለው ። ፖለቲካን የሚገዛው ህሳቤ ግን የሰዎች ቁሳዊ ጥቅምና የሃይል ሚዛን፣ የሃይል ዳይናሚክስ ነው። አቢይ በፖዘቲቭ ስብከት የፖለቲካ ትግል ሊፈታ ይሞክራል! አይሰራም ።

Last edited by Horus on 19 May 2022, 20:24, edited 1 time in total.


Right
Member
Posts: 2722
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: ቀውስ የዕድል መፈልፈያ ረግረግ ነው፤ አቢይ አህመድ ለምን ሁሉን ያጣ መሪ ሆነ?

Post by Right » 19 May 2022, 16:05

But Abiye has a brilliant adviser in Berhanu Nega.
Together they are navigating the leaky boat slowly going under.

Post Reply