Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ ኤትኖክራሲና የሱማሌ ዘውገክራሲ ትብብር፤ ዱቄትና አመድ !!

Post by Horus » 16 May 2022, 13:25

አቢይ አህመድ የትግሬ ዘረኞች የጠፈጠፉትን የጎሳ ቂጣ እንደ ፖለቲካ ስርዓት ወስዶ (ኤትኖክራሲ ጸረ ፖለቲካ ስለሆነ) ከሱማሌ የዘውግ (የክላን) ፖለቲካ መሰል ቀውስ ጋር 'ቀጠናዊ ትብብር' የተባለ ምናባዊ ስሌትና ስህተት ይህው እንደ እምቧይ ካብ ፈረሰ ። የዱቄትና አመድ ትብብር ማለት ነው ። ከዚህ የላቀ የፖለቲካ ስሌት ስህተት ሊኖር አይችልም ።

አቢይ አህመድ መጀመሪያ በኢትዮጵያ ምድር የዘር፣ የጎሳ፣ የዘውግ ፖለቲካ ተብዬ ኢትኖክራሲ ሳያፈርስና በኢትዮጵያ ምድር የጸና ዘመናዊ የፖለቲካ ሰርዓት ሳያቆም ባልታኘከ ሃሳብ ሄዶ ከሱማሌ የቤተ ሰብና የክላን ሽኩቻ ውስጥ ገብቶ የቀጠና ጂኦፖለቲካ አደርጋለሁ ማለት እብደት ነው ። ሁሉም ባንድ ቀን ይፈርሳል ። ኢትዮጵያ እራሷ ከኋላቀርና ዘውጌነት ነጻ የሆነ ስነሴራ ሳይኖራት የአፍሪካ ቀንድ የክላን ትርምስ ውስጥ መዘፈቅ ትርፉ ውድቀት ነው ።

ዝንጀሮ እንኳን መጀመሪያ መቀመጫዬን ብላለች! እስቲ መጀመሪያ ኢትዮጵያን ከጎሳና ዘውግ ትርምስና ቀውስ ለማውጣት ዘመናዊ እና የሚሰራ ፖለቲካ ሲስተም እንፍጠር !

Last edited by Horus on 16 May 2022, 14:45, edited 3 times in total.

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4070
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: የኢትዮጵያ ኤትኖክራሲና የሱማሌ ዘውገክራሲ ትብብር፤ ዱቄትና አመድ !!

Post by Za-Ilmaknun » 16 May 2022, 14:07

All I see is a total implosion before things settle, if they ever would. The PM is more worried about the ascendance of Ethiopianism centered on citizenry than the fire that is fast consuming the country because of the identity politics he is promoting insidiously. His words are becoming more hollow and his action speaking lauder in the reverse. He is losing constituency faster because of his wobbling leadership and indecisive actions that are informed of his convince or confuse mantra. At this point no one could speak with any certainty where this man is standing in relation to the monumental problems the country is facing. All the signs of a crumbling regime are written in bold for all to see be it in the economy, political or social realms.

Horus
Senior Member+
Posts: 30829
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ኤትኖክራሲና የሱማሌ ዘውገክራሲ ትብብር፤ ዱቄትና አመድ !!

Post by Horus » 16 May 2022, 15:08

Za-Ilmaknun wrote:
16 May 2022, 14:07
All I see is a total implosion before things settle, if they ever would. The PM is more worried about the ascendance of Ethiopianism centered on citizenry than the fire that is fast consuming the country because of the identity politics he is promoting insidiously. His words are becoming more hollow and his action speaking lauder in the reverse. He is losing constituency faster because of his wobbling leadership and indecisive actions that are informed of his convince or confuse mantra. At this point no one could speak with any certainty where this man is standing in relation to the monumental problems the country is facing. All the signs of a crumbling regime are written in bold for all to see be it in the economy, political or social realms.
ትክክል፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ሰሜን ሄዶ ልዩ ልዩ የአማራ ማህበረሰብ አባላትን ሰብስቦ ሲማጸን በትኩረት ተከታትዬው ነበር ። ሴት ልጁ እንዴት ግማሽ ኦሮማ (አንዳንዴ ጂማ ይል ነበር) እና ግማሽ ጎንደሬ እንደ ሆነች ሲገልጻት ልብ የሚበላ ነው ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ እሷን መሰል ኢትዮጵያዊያን አሉና! በዚያ ስብሰባ ውስጥ ብዙ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው መልስ ሰጥቷል።

አንድ ቁልፍ ጥያቄ ቀረበለት፤ ሕገ መንግስቱን ስለማሻሻል (ስለመለወጥ)። ያን ጥያቄ ላለመመለስ ለማድበስበስ ያደረገው ሙከራ ሰውዬው በፍጹም የወያኔን ሕገ ጎሳ ለመቀየር ሃሳብም ፍላጎትም እንደሌለው በግልጽ አጋልጦበታል ። አሁን በከንቱ ነው የሚለፋው እንጂ እሱ የሚናገረውን የሚያምን ጥቂት ሰው ነው ። እምነት ማጣት ማለት እጅግ ግዙፉ የመሪነት ውድቀት ነው ። ይህን እምነት ሊመልስ የሚችል ከፍተኛ ቆራጥ የተግባር ለውጥ በማሳየት ብቻ ነው ።

ሌላው የሚገርመው ነገር የብልጽግና ፕሮፓጋንዳ ዲፓርትመንት የዛሬ አመትና ሁለት አመት የተናገራቸው (በህዝብ ፍቅር ተምበሽብሾ በነበረ ግዜ) እንደ ገና መለጠፍ ጀምረዋል ። የሩሲያው ሌሊን 'መጥፎ ቲኦሪ የሚታረመው በጥሩ ተግባር ነው' ይል ነበር። ይህን የወያኔ ትግሬ የጎሳ ዝተት ተሸክሞ አቢይ የትም እንደ ማይደርስ ለሁሉም ግልጽ የሆነ ጉዳይ ነው።

Post Reply