Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ከጥቂት ዓመታት በፊት 380 ብር ይገዛ የነበረውን አራት ሌትር የመኪና ዘይት ሰሞኑን ከ1,800 በላይ ዋጋ ተጠይቆበታል - 374% increase!! (ሪፖርተር)

Post by sarcasm » 16 May 2022, 06:41

መንግሥት በተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ገበያ ላይ የነበረውን ቁጥጥር ማንሳቱ ያመጣው መዘዝ
15 May 2022
ዳዊት ታዬ


እንደ ምግብ ዘይት ሁሉ የመኪና ዘይትና ቅባት ሳይታሰብ ዋጋቸው ሰማይ ከነካ ሰነባብቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ዋጋቸው ከሁለትና ከሦስት እጅ በላይ ጭማሪ አሳይቷል።

የተሽከርካሪዎች የዘይትና የቅባት ምርቶች በጥቂት ወራት ውስጥ ዋጋቸው በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረበት ምክንያት ግን ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንደሌለው እየተነገረ ነው፡፡ የታክሲ ሾፌር በመሆን ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረው ያሬድ ገዙ እንደሚለው ከጥቂት ዓመታት በፊት 380 ብር ይገዛ የነበረውን አራት ሌትር የመኪና ዘይት ሰሞኑን ከ1,800 በላይ ዋጋ ተጠይቆበታል፡፡ ከሦስት ወራት በፊት ከነበረው ዋጋ አንፃር ሲታይ ደግሞ ዋጋው በእጥፍ መጨመሩን ገልጿል፡፡

ከስድስት ዓመታት በፊት አንዱን ሌትር መቶ ብር ባልሞላ ዋጋ ይገዛው እንደነበር ያስታወሰው ያሬድ፣ የሰሞኑ ጭማሪ ግን አስደንጋጭ ነው ብሏል፡፡ እንደ ያሬድ ሁሉ አስተያየታቸውን የሰጡን ሌላው የታክሲ አሽከርካሪ፤ የተሽከርካሪ ዘይት እንደ ምርቱ ዓይነት የዋጋ ልዩነት ያለው ቢሆንም፣ አሁን በገበያ ላይ ያሉት ሁሉም ዓይነት ምርቶች በተለይ ባለፉት ሦስት ወራት የታየባቸው ጭማሪ ከሁለትና ከሦስት እጅ በላይ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ሰዎች ትኩረት ስለማይሰጡት እንጂ በኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ የዋጋ ንረት ከታየባቸው ምርቶች መካከል የመኪና ዘይት ምርት አንዱና ዋነኛው ነው።

በኢትዮጵያ ነዳጅና ተያያዥ ዘርፎች ላይ የዓመታት ልምድ ያላቸው የዘርፉ ባለሙያው ሠርካለም ገብረ ክርስቶስ (ዶ/ር)፣ የሞተር ዘይትና ቅባት ዋጋ ተገማች ባልሆነ ሁኔታ እጅግ መጨመሩንና በተጋነነ ዋጋ የመሸጡ ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን ይጠቅሳሉ፡፡

ከዓለም አቀፍ ዋጋ አንፃር ሲታይ አሁን የሚሸጥበት የችርቻሮ ዋጋ ፈፅሞ የማይገናኝ እንደሆነም አስረድተው ከሌላው ጊዜ የተለየ መልኩ በከፍተኛ ዋጋ የመሸጣቸው ዋና ምክንያት ደግሞ የዘይትና የቅባት ምርቶች ላይ ይደረግ የነበረው ቁጥጥር ይፋ ባልሆነ መንገድ እንዲቋረጥ በመደረጉ ነው ይላሉ፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/index ... icle/25496