Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abaymado
Member
Posts: 4191
Joined: 27 Sep 2017, 21:56

ፋኖ ምንም እማራጭ የለውም መከላከያን መግጠም እና ይህን መንግስት ማስወገድ ነው።

Post by Abaymado » 15 May 2022, 17:09

የአማራ ህዝብ ለዚህ የተቀደሰ አላማ መተባበር አለበት።
በለው



Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: ፋኖ ምንም እማራጭ የለውም መከላከያን መግጠም እና ይህን መንግስት ማስወገድ ነው።

Post by Ethoash » 17 May 2022, 10:45

ፋኖ በአሜሪካም አለ ። ወታደሩ ሲሽነፍ በደጅን ወጣቱ በሙሉ ጠመንጃ ተስጥቶት አገር ለመከላከል ወድ ጦር ሜዳ ይሄዳል ይህ ያለ ነው ። የነበረ ነው። በዩክሬንም ይህ ሆኖዋል። ግን አንዴ ስራው ካለቀ በኋላ ፋኖወ ጦሩን መልሶ ወድ ግሉ ኑሮ መመለስ አለበት ፣ ወታደር የሚሆነው እኮ ጠቅላላው ህዝብ አይደለም ግፋ ካለ አንድ በመቶ ነው በስላም ግዜ ፣ በጦርነት ግዜ ፍኖ ተፈላጊ ነው እናም ለአገሩ ቢዋጋ ለአብይ ወለታ ማረጉ አይደለም ። አሁን ስላም መጥቶዋል ትጥቕህን ፍታ ማለት መንግስት ይችላል። አለበለዚያ እንዴት አገር ይምራ። ሁለት መንግስት በአንድ አገር ይሆናል።

ፍኖ ትጥቁን ካልፈታ ታድያ ኦሮሞ ፋኖም (ሼኔ ቅቤም ) ትጥቃቸውን መፍታት የለባቸውም ማለት ነዋ።

እንደኔ ከሆነ ሁሉም ክልል ፋኖ ቢኖረው ዲሲፕሊን ያለው በክልሉ ፕሬዘዳንት የሚመራ ክልሉን ብቻ ለመከላከል የቆመ ፣ ከክልሉ ውጭ ውጥቶ ጦርነት የማያስነሳ በሕግና በዲሲፕሊን የታነፀ ስራዊት መኖሩ ትልቅ ለኢትዬዽያ ጥቅም አለው። እንዴት በሉኝ።

ለምሳሌ ትግሬን እንውስድ። አብይ ልግዛቹሁ፣ ልርገጣቹሁ ሲላቸው እንቢ ብለው ጦርነት ገጠሙት፣ ስለዚህ መብታቸውን አስከበሩ ማለት ነው። ዝም ብሎ አብይ ጠቅላላ አገሩን ረግጦ አይገዛም ። ከዚህ በፊት ሱማሌ የሆነውን አይተናል አብዲ አሌን አንጠልጥሎ እስር ቤት ከተተውና የሚፈልገውን ስወ ሾመ። እንግዲህ እዚህ ላይ የአብይ ጦር ትክክል ስርቶ ይሆናል ስላም ለማስከበርና የቤት ክርስቲያን ማቃጠል ለማስቆም ፣ ታድይ ይህ ጥሩ ሆኖ ሳላ አብይ የፈደራሉን ጦር ሌሎችን ክልሎች ለመጮከን ሊጠቀምበት ይችላል ለጥሩም ለበጎ ። የዚህ ሁሉ አስተማማኝ የሚሆነው ሁሉም የራሱ ጦር ኖሮት በተጠንቀቅ ሲቆም ብቻ ነው።

ለምሳሌ ፓርላማውን ብትመለከቱ ምድረ አጨብጫቢ ብቻ ነው ያለው ግን ። እንበል ከትግሬ አገር አንድ ከንቲባ ቢላክ አብይን ልክ ልኩን መናገር ይችላል ለምን ቢባል ደጅን ትግሬ ላይ አለው። አብይ የትግሬውን ከንቲባ አንጠልጥሎ ማስር አይችልም ለምን ቢባል እኩል ሀይል ፈድራሉም ክልሉም ስላላቸው ይህ የኢትዬዽያን የፖለቲካል ባላንስ ይጠብቃል ማለት ነው።

እንደገና ሌላ ምሳሌ ላቅርብ። እንበል አንዱ የጠገበ አብይን ከልብጦ ስልጣን ቢይዝ ትግሬዎ፣ አማራው ፣ ኦሮሞው አልገዛም ካለ የአዲስ አበባ መንግስት ሆኖ ቀረ ማለት ነው ። ስለዚህ የመንግስት ግልበጣ ይቀራል ማለት ነው። ፋኖ ወግድ ይለዋልና። ስለዚህ ሁሉ ነገር በሕግና በስምምነት ይሆናል ማለት ነው።

እንዳልኩዋቹሁ የፋኖ ጥቅም ታውቆ ፋኖ መስመር ገብቶ በሕግና በክልሉ መንግስት ብቻ የሚተዳደር ከሆን፣ የፈደራል መንግስት ሳይሆን ክልሉ ደሞዙን የሚከፍለው ከሆነ ለአገር ጉዳትም ፣ ወይም ጥቅምም ሊወል ይችላል ። ብዬ አምናለሁኝ።

ስለዚህ አብይ ፋኖን አስፈታለሁ ብሎ ግርግር ባይፈጥርና መላ ቢፈልግ ይሻላል ባይ ነኝ።

Post Reply