Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

መንግሥት ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኪራይ ግማሽ ቢሊዮን ብር ማጣቱን አስታወቀ (ሪፖርተር)

Post by sarcasm » 15 May 2022, 14:57

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለመጀመርያ ጊዜ ትርፍ አስመዝግበዋል

በኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶች ለስምንት ወራት ኪራይ መክፈል ስላልቻሉ፣ መንግሥት 500 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ገቢ ማጣቱን ገለጸ፡፡

ፓርኩና በውስጡ ያሉ ድርጅቶች በሕወሓት ኃይል ዝርፊያ ከተፈጸመባቸው በኋላ፣ ወደ ሥራ ለመመለስ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ ማውጣቱ ተነግሯል፡፡

በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ ድርጅቶች በአሁኑ ጊዜ ወደ ሥራ መመለሳቸው ቢገለጽም፣ የሥራ ማስኬጃ ብድሮችና ሌሌች ድጋፎች ለማቅረብ ጥናት እየተደረገ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ ገልጸዋል፡፡

‹‹ሕወሓት እስከ ደብረ ሲና ድረስ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ብዙ ጉዳት ደርሷል፡፡ የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክም ባለመረጋጋቱ ሥራ አቋርጦ ነበር፡፡ ሮኬት ወደ ከተማው ከተተኮሰ በኋላም የባህር ዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አቁሞ በሐምሌ ወር ብቻ ነው ምርት ወደ ውጭ የላከው፤›› ሲሉ አቶ ሰንዶካን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ከሰመራና ከመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውጪ አሥራ አንዱም ፓርኮች በሥራ ላይ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ካሏት 177 ሼዶች ውስጥ 98 ያህሉ ተከራይተው በማምረት ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

Continue reading https://www.ethiopianreporter.com/index ... icle/25486