Ethioscience; ሃሳብህ ይገባኛል፤ ቀድሞ የተናገርኩትንም ሳታስበው ቀርተሀል የሚል ዕምነት ኖሮኝ አይደለም። ነገር ግን፦ "የኢትዮዽያን ሠራዊት ትላንትና ማታ እራት፣ ዛሬ ጠዋት ደግሞ ቁርስ አደረግነው" እያሉ የሚፎክሩት ቁምቡርሶች ከተጎጂዎቹ መካከል ቢሆኑ እንዲህ ነጋ ጠባ በቤተሰቦቻቸው ሞትና እምባ የሚዘፍኑ ይመስልሃል? አይደሉም! ይህ አይነት ፎቶ ፈፅሞ አይሰማቸውም! አያስደነግጣቸውም! እነዚህ፦ ከቤተሰባቸው አልፈው ዘመድ አዝማዳቸውን ሰብስበው ኣውሮፓና አሜሪካ የመሸጉ … ፍቅር-የለሽ፣ የበሉትን የኣሳማ ሥጋ ከኮረት ጥርሳቸው መካከል የሚፈነቅሉበትን ፍልጥ የሚያክል tooth-stick ሰፊ አፋቸው ላይ ቀርቅረው፣ ኣንድ ሲኒ ቡና በማዘዝ ከStarbucks ጠረፔዛ የሃሰት ወሬ የሚነዙ … እምነት-የለሾች ናቸው። ይህን የምለው ማለት ስላለብኝ እንጂ ኣንተ አታውቅም ብዬም አይደለም።
የተጎጂ ቤተሰቦች'ማ … ልጆቻቸውን በግድ የተነጠቁ እናቶች'ማ፦ "ልጄ ምን ሆና ይሆን? ልጄ የት ወድቆብኝ ይሆን? ዳግም አይኗን አየው ይሆን? አምላክ ከዚህ ረሃብና በሽታ ጥቂት ዕድሜ ሰጥቶኝ ፊቱን ለማየት ያበቃኝ ይሆን?” እያሉ ዘወትር ባዶ አንጀታቸውን ኣምላክን የሚማልዱና፤ ከዛሬ ነገ ክፉ ወሬ እሰማ ይሆን በሚል ስጋት ከረሃብ የተረፈ ስጋቸውን ጭንቀት የሚያኝከው ምስኪኖች ናቸው። ስለዚህ … ማለት የፈለኩት … we must not fall to their immoral maneuver. በረቱን ከሚያውቅ እንስሳ ላነሰ ሀገር-ካጅ … ተገቢው መልስ ንቆ መተው ነው።
"እንዲህ ነን" የሚሉትን ሁሉ እንዳልሆኑ፣ "እንዲህ አደረግን" የሚሉትን ሁሉ እንዳላደረጉ እኛ ብቻ ሳይሆን እነርሱም ያውቁታል:
* መሳሪያ ግምጃ ቤት እንዲያስገባ ታዞ ባዶ እጁን የተኛ ወታደር በሴራ ገድለውና ማርከው በየከተማው እያዞሩ … "ተመልከቱ ጀግኖች ነን" ይላሉ። ያንን ወታደር ዕድሜውን ሙሉ ትግራይ ውስጥ ያስቀምጡት ይመስል። ዛሬ እንዲህ በየጎዳናው እያዞሩ እንደተዘባበቱበት፥ ነገ ወደ ትውልድ ቅዬው ሲመለስ … እርሱም ሆነ ቤተሰቡ መንገድ ግራና ቀኝ ይዞ ለሰደበው፣ ለተፋበት ማህበረሰብ ምን ዓይነት መልስ ይሰጣል የሚለውን ቀላል ሎጂክ እንኳን ማሰብ ያቃታቸው ድኩማን።
* የሀገርን ስንቅና ትጥቅ ለሃያ ሰባት ዓመታት ሲያግዙና ሲያከማቹ ከከረሙ ቦኃላ፥ ሁለት ሜትር እንኳ ያልሞላች ጨፈቃ የጨበጠን ኣርሶ-አደር ገጥመው … "የምስራቅ ኣፍሪካ ሃያላን ነን" በለው ይፎክራሉ። የወንድ ልጅ ሱሪ የሚለካው … ፈረሱም ሜዳውም እኩል ያለ አድሎ ሲቀርብና ግጥሚያውም ያለ ሴረኛ ዳኛ ሲዳኝ መሆኑ ያልገባቸው ከንቱዎች።
* ልፍስፍስ መሪ በሚያዝበት የጦር ሜዳ ውሎ፥ ሰባት ሀገር አይደለም ሰባት አህጉር እንኳን አንድ ላይ ቢጣመር ውጤት ማምጣት እንደማይቻል እያወቁት … "ጀግኖች ስለሆን ሀገራት ተዳምረው ገጥመውን እንኳ አላጠፉንም" ይሉናል።
ይኼ ሁሉ ባዶ ፉከራ ለከንፈራቸው እንጂ እውነታውን ልባቸው ያውቀዋል። ለምሳሌ፦ ከዚህ በታች ያለው ቪዲዮ ከተለጠፈ ኣመታት አልፈዋል፤ የህወሃት ሶሻል ሚዲያ ግን የዚህን ልጅና የጎደኞቹን ፎቶ ዛሬም ድረስ በየቦታው በመለጠፍ "አሁንም ልዩ ሀይላችን በሙሉ ቁመናው ላይ ይገኛል" ብለው በየቀኑ ይደነፋሉ። ሐቁ ግን … እኛም እነርሱም እነዚህ ልጆች ዛሬ የት እንዳሉ በሚገባ እናውቃለን። ነገ … ከነገ ወዲያ እንደተባለው "በፋና ላምሮት" ወይ "በባላገሩ አይዶል" ላይ ቀርበው … "ወይናዬ ወይናዬ ሆይ … ደርግ ስንኪ" እያሉ የሳሚን ሙዚቃ ሲያቀነቅኑ፥ የሶሻል ሚዲያው ቁምቡርሶችም ኮረት ጥርሳቸውን በፍልጥ እየቆፈሩ የሚያዳምጡበት ቀን ይመጣል።
በመጨረሻም Ethioscience; እነዛን አይነት ፎቶዎችን በተመለከተ ተስማምተናል የሚል እምነት አለኝ
ሰላም ሁን; Ethioscience