Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Y3n3g3s3w
Member
Posts: 531
Joined: 22 Dec 2017, 00:56

የመራራ ጉዲና ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ትዝብቶች

Post by Y3n3g3s3w » 13 May 2022, 11:54

የመራራ ጉዲና ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳንድ ትዝብቶች

ግን በመጀመሪያ ዶክተሩ ለፕላስቲክ ሰርጀሪ ነበር እንዴ አሜሪካ የሄደው? ቀልበጭ ብሎ በጣም አምሮበት ነው የተመለሰው:: እንዲህ ነው ንግድ ሲያዋጣ ! አሉ እንጂ እነ ኤርሚያስ ለገሰ ሀብታሙ አያሌው ልደቱ ክደቱ ሰተት ብለው ወያኔ ጋ ዳይቭ የገቡ ጅሎች , መራራ ጮሌው ፖለቲካዋን ጥላ ጥላውን ነው ሀሩር ፀሃይ ወስጥ ማን ይገባል! ምን አለ በሉኝ በቅርቡ መራራ ኦፌኮን NAZDAQ ወይም Dow Jones ወይም TFX ላይ ያስመዘግበዋል .

አንድ ደሞ በጣም የገረመኝ ነገር። በተደጋጋሚ "ሶስተኛ አካል (ፈረንጆቹ እንደሚሉት third party) ገብቶበት እንወያይ" ማናቸው ገለልተኞቹ ? አይኑ ያለው አሜሪካ ላይ መሰለኝ- ወይ ህዝብ መናቅ!

እኔ የምለው አንድ "የተከበረ ሰው" እንዴት እዚህ ደረሰ? 40 ሚሊየን ህዝብ የመረጠውን መንግስት አንዲተ ጥሩ ነገር ሰራ ማለት እንደኔ ለመንግስትና ለመረጠው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለራሱም ክብር ነው, አለማለት ደሞ ህዝብን መናቅ ረስን ማዋረድ ይመስለኛል

ሌል ፈገግ ያረገኝ , "ፈረንጆች እንደሚሉት - dead on arrival ' በማለት የምክክር ኮሚቴውን አፈር ድቤ ለማብላት የሞከረው ነው:: ቆይ መራራና አሜሪካ ከሌሉበት ምንም አይነት ሰራ ኢትዮጵያ ውሰጥ አይከናወንም ማለት ነው?


እስቲ ሁሉንም እንተውና የመግለጫው አላማ ምን ነበር?? ልክ ወያኔ እዛጋ ሰብሬ ካልወጣሁ እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ሲጀምር ኦፌኮ እዚህ ለወያኔ መንግስትን ለማወከብ የህዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ተጠምዱዋል ብንል በጣም ተሳሳትን ይሆን???

እውነት እውነት እላቺሁአለሁ መራራ ጉዲና ኢትዮጵያን ክዷል !!

TheManWhoSawTomorow