Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Thomas H
Senior Member
Posts: 12608
Joined: 27 Jan 2007, 16:30
Location: Kaliti
Contact:

Must Read: The gloves are off ! ዲያቆን ዳንኤል ክስረት ዓብይን አህያ ብሎ ሰደበው

Post by Thomas H » 11 May 2022, 19:27

" የአህያ መሪ ይስጠን "
ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
አህያ በረሐ ውስጥ እስከ 60 ማይል እርቀት የሌላውን አህያ ጩኸት መስማት የምትችል ፍጡር ናት፡፡ ዛሬ ዛሬ ጉርብትና እየጠፋ ጎረቤት ጎረቤቱን መስማት ባቆመበት ዘመን ወዳጁን ከ60 ማይል መስማት ከሚችል ፍጡር በላይ ምን ወዳጅነት አለ፡፡ የአህያ ጆሮ ይህ ብቻ አይደለም ጥቅሙ፡፡ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ተናገሩት የተባለውን ነገር የሚያረጋግጥልን ነገርም አለው፡፡ ንጉሡ ወደ ደብረ ዘይት ሲሄዱ የአየር ንብረት ዘገባ በሬዲዮ ይሰማሉ፡፡ ቀኑ ፀሐይ ነው የሚል ነው ትንበያው፡፡ ንጉሡም ይህንን አምነው ወደ ደብረ ዘይት ያመራሉ፡፡ መንገድ ላይ ግን አንድ ገበሬ አህያውን እያስሮጠ ሲሄድ ያዩታል፡፡ ንጉሡም ‹ምነው አህያዋን ታስሮጣታለህ› ይሉታል፡፡ ገበሬውም ‹ዝናብ ሊመጣ ስለሆነ ነው› ይላቸዋል፡፡ ንጉሡም ‹እንዴት ዐወቅህ› ይሉታል፡፡ ገበሬውም ‹አህያዋ ጆሮዋን ጥላለች› ይላቸዋል፡፡ እርሳቸውም ገርሟቸው ይሄዳሉ፡፡ እልፍ እንዳሉም የአየር ትንበያው የተናገረው ፀሐይ ቀርቶ ገበሬው የተናገረው ዝናብ መጣ ይባላል፡፡
የአህያ ጆሮ የአየር ንብረትን በተመለከተ ለአህያዋ ሁለት ነገር ይጠቅማታል፡፡ በአንድ በኩል የውስጧን የሙቀትና የቅዝቃዜ ሁኔታ ለመጠበቅ ሲያገለግላት፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአካባቢውን የአየር ሁኔታ ገምግማ ርምጃ ለመውሰድ እንድትችል ያግዛታል፡፡ አህያ እንደነፈረስ ዝናብ የሚችል ቆዳ የላትም፡፡ ያላት ዝናብ መምጣቱን ዐውቆ እንድትጠለል የሚመክር ጆሮ ነው፡፡ ከፈጣሪ ካገኘችው አደጋን ቀድማ የመገመት ችሎታ ጋር ተጨምሮ ጆሮዎቿ የአካባቢውን ቀጣይ የአየር ሁኔታ ዐውቃ ሰውነቷን ለማዘጋጀት እንድትችል ያደርጓታል፡፡ የደብረ ዘይቱ ገበሬም ይህንን ነገር ነው የደረሰበት፡፡
ባይሆን አህያ በሆዳምነት መታማቷ እውነት ሳይሆን አይቀርም፡፡ አህያ እስከ 40 የሚደርሱ ጨጓራዎች እንዳሏት ስትሰሙ ኡኡ ማለታችሁ አይቀርም፡፡ የአሁኑ ይባስ እንድትሉ ሁለት ነገሮች እንጨምር፡፡ አህያ በእድሜ በገፋች ቁጥር የጨጓራዋን መጠን እየጨመረችው ትሄዳለች፡፡ እድሜ ለዐርባ ጨጓራዎቿ 18 ኪሎ ካሮት እምሽክ ለማድረግ አንድ ሰዓት አይፈጅባትም፡፡ እስካሁን በአህዮች ታሪክ ከፍተኛውን ጨጓራ ያስመዘገበችው የኡዝቤክስታን አህያ ናት፡፡ 59 ጨጓራ አስመዝግባለች፡፡ አንድ አህያ እግዜርን ካልፈራች 2722 ኪሎ ምግብ በዓመት ትፈጃለች፡፡ እንኳን የሸመተ ያረሰም አይችልሽ ማለት አሁን ነው፡፡
የአህያን መሥዋዕትነት ብነግራችሁ ግን ‹ትብላ፣ ደግ አረገች› ትሏታላችሁ፡፡ የአህያ መንጋ የቡድን መሪ አለው፡፡ ጠራጣራዋ አህያ አደጋ ሊመጣ መሆኑን ከጠረጠረች አካባቢዋን ታስሳለች፡፡ ቀጥላም የአደጋውን አቅጣጫ ታረጋግጣለች፡፡ ከዚያም አደጋው በመጣበት በኩል ራስዋን ታሠማራለች፡፡ በመጨረሻ አደጋውን ትጋፈጣለች፡፡ የአህያ መሪ አደጋውን ስትጋፈጥ ሌሎቹ በቂ ጊዜ አግኝተው ከአካባቢው ይሸሻሉ፡፡ በመሪዋ መሥዋዕትነት ሌሎቹ ይተርፋሉ፡፡
መሪ ማለት እንዲህም አይደል፡፡ ራሱን ሠውቶ ሕዝቡን የሚታደግ፡፡
የአህያ መሪ ይስጠን፡፡
Last edited by Thomas H on 11 May 2022, 21:31, edited 1 time in total.


simbe11
Member
Posts: 2087
Joined: 23 Feb 2013, 13:02
Location: Addis Ababa

Re: Must Rad: The gloves are off ! ዲያቆን ዳንኤል ክስረት ዓብይን አህያ ብሎ ሰደበው

Post by simbe11 » 11 May 2022, 19:44

What's happening?
I thought you said Suyum mesfin is dead!!

Post Reply