Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Post Reply
Horus
Senior Member+
Posts: 23180
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ይህ የጴንጤዎች የሠርግ እንሾሽላ ነው ለማለት አያስደፍርም !! ድንቅ ነው !!

Post by Horus » 11 May 2022, 15:58

ዘማሪው (ደራሲው) አለማዊ ዘፋኞች ይበልጣቸዋል ! ባህል ሁል ግዜ ከሃይማኖት ይቀድማል ! ሃይማኖት ሁልግዜ የሚከወነው በባህል ነው !


Assegid S.
Member
Posts: 588
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ይህ የጴንጤዎች የሠርግ እንሾሽላ ነው ለማለት አያስደፍርም !! ድንቅ ነው !!

Post by Assegid S. » 11 May 2022, 17:27

Horus wrote:
11 May 2022, 15:58
ባህል ሁል ግዜ ከሃይማኖት ይቀድማል ! ሃይማኖት ሁልግዜ የሚከወነው በባህል ነው !

ሰላም Horus; thanks a lot for the clip.

ከላይ በደረስክበት ድምዳሜ ላይ ግን ጥያቄ አለኝ፤ በተለይም ሁልጊዜ በሚለው ቃል ላይ። ልማድ ወይንም ተግባር ኣንዱ የባህል መገለጫ ነው። ለምሳሌ፦ ኣንድ ኦርቶዶክስ የሆነ ግለሰብ ሀይማኖቱን ሳይቀይር በፊት ከኣንድ በላይ የትዳር አጋር እንዲኖረኝ እፈልጋለሁ ብሎ ሁለትና ሦስት ሚስቶች ቢያገባ ከባህሉ ጋር አይጋጭምን? ይህ ማለት ደግሞ ባህል የሚገለፀው በሀይማኖት ነው ማለት አይደለምን? ይኸው ግለሰብ ሀይማኖቱን ከቀየረ ቦኃላ ግን ( እንበልና እስልምናን ቢቀበልና) በህግና ሥርዓቱ ሁለትና ከዛም በላይ ሚስቶች ቢኖሩት ማን ይቃወመዋል? ምክንያቱም ቀድሞ የተቀበለው (የቀየረው) ሀይማኖቱ ወይም እምነቱ ተግባሩን ስላፀደቀለት አይደለምን? በቀን ኣምስት ጊዜ መስገዱና የመሳሰሉትም ተግባራት (ልማድ) ...የባህል መገለጫዎች ማለት ነው ... የሚመጡት ወይንም የሚገለጡት ከሀይማኖት ቦኃላ ነው። እምነቱን ከእስልምና ወደ ኦርቶዶክስ ለቀየረም ግለሰብ እንዲሁ፦ ጥምቀቱ፣ እሮብ ኣርብ ፆሙና የመሳሰሉት ባህላትም የሚገለጡት በሀይማኖቱ (ቀድሞ በቀየረው) እምነቱ ላይ ተመርኩዞ ነው ባይ ነኝ።

ይህን ስል ግን፦ ሀይማኖት በባህል አይከወንም ለማለትም አይደለም። ነገር ግን "ባህል ሁል ግዜ ከሃይማኖት ይቀድማል ! ሃይማኖት ሁልግዜ የሚከወነው በባህል ነው!" ከሚለው አጠቃላይ ድምዳሜህ ጋር ስላልተሰማማሁ ነው።

መልካም ጊዜ Horus.

Horus
Senior Member+
Posts: 23180
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ይህ የጴንጤዎች የሠርግ እንሾሽላ ነው ለማለት አያስደፍርም !! ድንቅ ነው !!

Post by Horus » 11 May 2022, 23:04

ሰላም አሰግድ፣
ከጥቂት ቀናት በፊት የሃይሞት ግጭት ሲበራከት የለጠፍኩት ረዘም ያለ አለ በኋል ከፍ አደርገዋለሁ ። 'ሁሉ' የሚለው ቃል ሆነ ብዬ ያልኩት ነገር አይደለም፤ በጣም ጄኔራላይዝ አድራጊ ከመሰለ እስቲ እንመርምረው ። ይህን ለማለት ያስነሳኝ እነዚህ የጉራጌ ሴቶች ያደረጉትን አይቼ ነው ። እንሾሽላ ምንም ከእምነት ጋር የማይገናኝ የሴት ልጅ ሰርግ ሶስት ቀን ሲቀረው በተሰብ እሷን የሚሸኝበት ባህል (ካልቸር) ነው ። የሴቶቹ ጭፈራ አለማዊ የጉራጌኛ ጭፈራ ነው ። መዝሙር ተብሎ የሚዜመው የጉራጌኛ ሪዝምና ምት የአለማዊ ሙዚቃ አርት ነው ። ሃይማኖታዊ የሚያደርገው የዜማው ግጥም (ሊሪክስ) ብቻ ነው። ልብ እንበል ተግባሩ (ኢቬንቱ) እራሱ ፈጣሪ ማክበሪያ ሳይሆን ሰርግ የሰዎች ባህል (የጋብቻ ካልቸር) መተግበሪያ ነው ።

በሌላ በኩል ማንኛውም ሃይማኖት ዶግማ (የእምነቱ ቲኦሪ ወይም ዶክትሪን) አለው። እንደዚሁን የዶግማው መተግበሪያ ቀኖና (ሪቿል) አለው። ለምሳሌ ቅዳሴ፣ ማህሌት፣ ወረብ፣ ሽብሸባ፣ የከበሮ ምት፣ የጽናጽን እና መቋሊያ መተግበሪያ ቀኖናዎች ናቸው ። እኔ ያ ካልቸር ነው የምለው ። ለምሳሌ ሌሎች ኦርቶዶክስ አማኞች ግሬክ ወይም ሩሲያ የኢትዮጵያ ወረብና ሽብሸባ ቀኖና የላቸውም ። ይህን የዶግማና ቀኖና (የእምነትና ካልቸር) ጉዳይ ጴንጤዎች በጣም ጫፍ አድርሰውን አሁን ፈጣሪ በማንኛውም ዘፈን ይመሰገናል ማለት ነው። የዶግማው ቃላት ፈጣሪን እስካመሰገኑ ድረስ ።

ባህል (ካልቸር) ሁልግዜ ከሃይማኖት ይቀድማል ያልኩት አስቤበት ነው ። ትክክል ነኝ ብዬ አምናለሁ። እምነት ሃሳብ ነው ። ካልቸር (ቀኖና ተግባር) ነው ። በማህበረ ሰብ ደረጃ ባህል(ብሂል) ወይም ካልቸር የምንለውኮ ሶሺያል ፕራክቲስ ነው፣ ያ ደሞ በየግዜው በመደበኛነት ደጋግመን የምንፈጽመው ተግባር ነው፤ አንተ ልማድ ያልከው ማለት ነው ። አንን ብሂል ነው መንፈሳዊ እምነታችንን በተግባር (እንደ ሶሺያል ቢሄቪየር) የምንፈጽምበት ። ሌላ እምነት በተግበሪያ ሶሺያል ፕራክቲስ የለንም። ለዚህ ነው እነዚህ ገዳም ገብተው ያሬዳዊ ካልቸር ያልተማሩት የጉራጌ ሴቶች በሚያውቁት ካልቸር በጉራጌ ዘፈን አላካቸውን የሚያመሰኙት ። የነሱ ቀኖና የምታየው ጭፈራቸውና የጉራጌኛ ዜማዎች ናቸው ።

አው ይበልጥ ሳስብበት ሃይማኖት የሚከወነው በካልቸር ነው ። አንተ ያነሳሃው ትክክለኛ ነገር የሃይማኖቱ ዶግማን የሚጻረር ቀኖና ወይም ባህል በሃይማኖቱ ውስጥ አይኖርም ። ከርስቲያ አንድ ባልና አንድ ሚስት ብቻ የሚደነግግ ዶግማ ስላለው ሶስት ሚስት ማግባት የክርስቲያን ካልቸር ሊሆን አይችልም ። ስለሆነም አንተ እንዳልከው አንድ ሙስሊም ሶስት ሚስቶች ካገባ በኋላ ክርስቲያ ልሁን ካለ ወይ ሁለቱን ሚስቶች መፍታት አለበት፤ ወይ የሚያጠምቁት ቄሶች አንድ ነገር ማድረግ አለባቸው እንጂ ክርስትናን በሙስሊም ካልቸር ፣ ማለትም ኦርቶዶክስ ዶግማ በሙስሊም ቀኖና ሊከውን አይችልም። አው ካንተ ጋር የምስማማው ሃይምኖት ከካልቸር በኋላ የተፈጠረ የካልቸር አንድ አካል በሆንም የሃይማኖት ዶግማ ሲጻፍ አብሮ መተግበሪያ ቀኖናው ስለሚገለጽ እምነት በማንኛውም የሰው ስራ ወይም ባህሪ መትግበር አይችላም። ለምሳሌ በቤተ መቅደስ ወስጥ ሰው ሁሉ ጠጅ እየጠጣ ሊያስቀድስ እንደ ማይችል ማለት ነው ።

ስለዚህ ቀኖና እራሱ ሞራል ኮድና መንፈሳዊ ሰነምግባር (ኤቲክስ) መከተል ይኖርባቸዋል ። በዚያ መሰረት እምነት ካልቸርን ይቀርጻል፤ ዶግማ ቀኖናን ይቀርጻል ያልከው ትክክል ነው ። ግን አንዴ ያ ከሆነ በኋላ ሁልግዜ እምነት የሚገለጸው በካልቸር ነው። ሌላ እምነትን ፕራክቲስ ማድረጊያ መንገድ የለንም ።

ኬይር

Assegid S.
Member
Posts: 588
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: ይህ የጴንጤዎች የሠርግ እንሾሽላ ነው ለማለት አያስደፍርም !! ድንቅ ነው !!

Post by Assegid S. » 12 May 2022, 08:50

ሰላም Horus; ለተጠቀምከው ጊዜና ሰፊ ትንታኔህ እጅግ በጣም አመሰግናለሁ። በገለፃህ ውስጥ ካሉት የኣንተ ሐሳቦች መካከል የምጋራቸው እንዳሉ ሁሉ የማልስማማባቸውንም አመልለካከቶች አግኝቼበታለሁ። እነርሱን አሁን እዚህ ጋር ለማስቀመጥ ብሞክር ብዙ ብዙ እንሄዳለን። ስለዚህ፦ የተለያየ ሀይማኖት የሚከተሉ ሰዎች ኣንድ አይነት የባህል ተግባራት እንደሚኖራቸው ሁሉ፥ የተለያየ የባህል ተግባራት ያላቸውም ማህበረሰቦች ኣንድ አይነት እምነት (ሐይማኖት) ሊኖራቸው ይችላል በሚለው መደምደሚያ ብንቋጨውስ? ከተስማማህ? 8) አለበለዚያ በሁለት የተለያየ school of thought እሳቤ በሚመስል መልኩ ... we gonna argue for ages 8)

በነገራችን ላይ፦ ሓሳቡ ከተነሳ ዘንድ ... ምንም እንኳን ያነበብኩት ጥናታዊ ጽሑፍ ባይኖርም፥ ይህ የሰዎች የእንሾሽላ ጉዳይ (tattoo ጨምሮ) እና የዳንስ ውዝዋዜ ከእንስሳት መልክና እንቅስቃሴ ተቀድቶ ያደገ ይመስለኛል። እንሾሽላው ከእንስሳቱ ዥጉርጉር ቆዳና የላባ ልባስ ... ዳንሱም ከእንስሳቱ የደስታና ሀዘን (ቁጣ) እንዲሁም የአደን ባህሪ መገለጫ። ወደፊት ሰፋ ባለ መልኩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አንብቤ ይህን የግሌን እሳቤ እገመግምበታለሁ። አልያም የራሴን ጽሑፍ እፅፍበታለሁ 8)

መልካም ሁን Horus.

* Thanks a lot for the other (older) post too.

Post Reply