Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 10186
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

ዳይፐር-ቀያሪው በለጠ ሞላ፥ የፓርቲ ጓዶቹን ከማገድ አልፎ እንደሚያስገድላቸው ሁሉ መጠራጠር አያስፈልግም‼‼

Post by sarcasm » 10 May 2022, 07:41

ዳይፐር-ቀያሪው በለጠ ሞላ፥ የፓርቲ ጓዶቹን ከማገድ አልፎ እንደሚያስገድላቸው ሁሉ መጠራጠር አያስፈልግም‼

በዴቭ ዳዊት


ዳይፐር-ቀያሪው በለጠ ሞላ፥ የሚንስትርነት ወንበሩ ማስጠበቂያ ብቸኛ ዋስተናው የአብን የሊቀመንበርነት "ስልጣኑ" ናት። እሷ ላይ ተፈናጥጦ የአማራን ትግል "ማመስ" ከቻለ ብቻ ነው በእነ አብይ አህመድ ዘንድ "The Useful Idiot" ሆኖ ሊያገለግላቸው የሚችለው። ስለሆነም፥ ይህቺን የግርድና ሚና ለመጫወት የምታገለግለውን የአብን የሊቀመንበርነት ወንበሩን ለማስጠበቅ፥ "ጓዶቹን" እስከማስገደል ከመሄድ እንደማይመለስ ግልፅ ነው።

በነገራችን ላይ የአብን ሰዎች አሜሪካ በመጡ ጊዜ ጋዜጠኛ አበበ በለው ለአብን የገቢ ማሰባሰቢያ ባዘጋጀው የቀጥታ ስርጭት ላይ በለጠ ሞላና ደሳለኝ ጫኔ ቀርበው የስልክ ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ይሰጡ ነበር። በመካከል አንድ ሰው አስደንጋጭ ጥያቄ ይዞ ብቅ አለ። ይኸውም "የጄነራል አሳምነው ፅጌ ቀብር ላይ አንድ የፓርቲ ጓድህ አብሯችሁ በላሊበላ ተገኝቶ ሳለ፥ የዚያ ጓዳ'ችሁ ፎቶ ተቆርጦ ከህዝብ እይታ እንዲሰወር፣ በጄኔራሉ ቀብር ላይም የአንድ አካባቢ ሰዎች በአድማ ያልተገኙ ያስመሰልክበት አካሄድ ፍፁም አሳፋሪ ክስተት ነው። ያንን ማድረግ ለምን ፈለግህ?" አለው። በለጠም ሲመልስ፦ "አዎ የተባለው ጓዳ'ችን በላሊበላ ተገኝቶ ነበር። ፎቶውን ቆርጠው የሰጡኝ ግን ሌሎች እዛው ላሊበላ የሚኖሩ ልጆች ናቸው" አለ። ጠያቂው አንድ ዕድል ብቻ ስለተሰጠው ይመስለኛል ለበለጠ ሞላ የስላቅና የተንኮል መልስ ተከታታይ ጥያቄ ሳያቀርብ ነገሩ በዚያው ተዳፈነ። በዚያ ሰሞን ህዝብን ከማረጋጋት ይልቅ የቀብር ላይ ፎቶዎችን ሲለጥፍና ጓዶቹን ሲያሳጣ፣ ዘለፋውና ወቀሳው ከግለሰቦች አልፎ አካባቢያዊ ቅርፅ እንዲይዝ የተጫወተውን ሚና፥ "ፎቶውን ቆርጠው የሰጡኝ ላሊበላ ያሉ ማንነታቸው የማይታወቅ ልጆች ናቸው" በማለት ያደረገው ማለባበስ የመሰሪነት ጥጉን ማሳያ ነው። በግሌ ሁለት ነገር ትኩረቴን ስቦት ነበር። የመጀመሪያው፥ በዚህ ልክ የፓርቲ ጓዱን ለመጉዳት፣ በወቅቱ የነበረውን ብአዴን-መር የጎጥ አጀንዳ ለማፋፋም መሄድ ከቻለ፥ ለአማራ ህዝብ ትግል የውስጥ-ነቀርሳ ሆኖ የመቀጠሉ ጉዳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ፥ በዚያ የቀጥታ ዝግጅት ላይ ይህ ጉዳይ ይፋ ሲደረግ ብዙኃኑ ሰው ነገሩን አቅልሎ ብቻ ሳይሆን "ከመጤፍ" ሳይቆጥረው ማለፉ ነው።

በነገራችን ላይ የብአዴን በለው የአብን በአጠቃላይ የአማራ ፖለቲካ አንዱ ደካማ ጎን የግለሰቦች በተለይም አመራር ነን የሚሉ ሰዎች የሚገቡበት ግላዊ ቁርሾዎች በፍጥነት ወደ ቡድናዊ ቁርሾዎችና መቆራቆዞች የሚቀየሩበት አካሄድ ሲሆን ይህ እርስበርስ መናከስ ዛዲግ አብረሃና በለጠ ሞላን የመሣሠሉ ሰርጎገቦች በላያቸው ላይ እንዲነግሱ፣ የአማራ ህዝብም ተቋም እንዳይመሰረት፣ ቢመሰረትም በቶሎ እንዲፈርስ አድርጎታል።

በዚህ አያያዝ ይህ የገነገነ ችግር በቀላሉ ይፈታል የሚል እምነት የለኝም‼‼

ዴቭ ዳዊት።




Please wait, video is loading...