ይህ ነው የኛ መሪ ሀገር እያፈረሰ ቤት የሚሰራ። ኦርቶዶክስን እና እስልምናን የሚያክል ትልቅ ተቋም እና ህዝብ እያባላ ፤ እያናቆረ ትንንሽ ቤቶችን የሚሰራ ፤ በትንንሽ ነገር ህዝብን ሀገርን የሚሸነግል ይህ ነው የኛ መሪ።
.******
የኛ መሪ ልዩ ነው! ኦሮሚያ በየቀኑ ወጣቶቿን ፤ አዛውንቶች ፤ ህፃናት ፤ ጎልማሶች ፤ ፈፅሞ ምንም በማያውቁት ነገር ፤ ኦነግ ናችሁ ፤ ሸኔ ናችሁ ፤ እየተባሉ በገዛ ቂያቸው ፤ በገዛ መንደራቸው ፤ በየቀኑ በአደባባይ እየተገደሉ ፤ የደም እንባ እያነቡ የኛ መሪ ትንንሽ ቤቶች እየሰራ ይሸነግለናል።
.*****
ይሄ ነው የኛ መሪ ትግራይን እያስራበ ፤ የትግራይ እናቶችን እያስለቀሰ የአማራን ህዝብ እና እናቶች እያስነባ ለዘመናት አብሮ የኖረን ህዝብ እያባላ አንድ ትንሽ ቤት ሰርቶ ድሀን የሚያጓጓ። ይሄ ነው የኛ መሪ ወጣቶችን ለጦርነት ዳርጎ እናቶችን ያለ ጣሪ አስቀርቶ የሌላውን ቤት ባዶ አድርጎ ትንንሽዪ ቤቶችን የሚሰራ ይሄ ነው የኛ መሪ።
.*****
ይህ ነው የኛ መሪ በአፋር ፤ በኦሮሚያ ፤ በሶማሌ ፤ በልዩ ልዩ ክልሎች ህዝብ እየተሰደደ ቤት ንብረቱን አጥቶ አደባባይ ወጥቶ እየለመነ የኛ መሪ ግን አሁንም ትንንሽ ቤቶችን በመስራት ትንንሽ ሀሳቦችን በትናንሽ መንደር ውስጥ እያመላለሰ የሚመራን ይሄ ነው የኛ መሪ።
.******
ይሄ ነው የኛ መሪ ኢትዮጵያን የምታክል ትንልቅ ሀገር ትንሽ አድርጎ ህዝቦቿን ለከፋ ስቃይ መከራ ዳርጎ የመንደር ቤቶችን ልስራላችሁ እያለ የሚያታልለን ይሄ ነው የኛ መሪ። ይሄ ነው የኛ አሳቢ። እንዲህ ያለ መሪ እውነት ከወዴት ይገኛል? ለመሆኑ በዚህ ሰውዪ ደስተኛው ? ያልልተነካው? እርሱ ማነው
Please wait, video is loading...