Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Revelations
Senior Member+
Posts: 33735
Joined: 06 Jan 2007, 15:44

ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች የከባድ መሳሪያ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተነገረ

Post by Revelations » 09 May 2022, 10:15

የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑት አካባቢዎች ላይ የከባድ መሳሪያ ጥቃት ከፍተው ለአጭር ጊዜ የቆየ ወታደራዊ ግጭት መካሄዱን ታማኝ ምንጮች ለቢቢሲ አረጋገጡ።

ጥቃቱ ተፈጸመ የተባለው እሁድ ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ሲሆን በራማ እና ባድመ አካባቢ ባለው የኤርትራ ጦር ላይ ሲሆን፣ ጥቃቱን ተከትሎ በትግራይ ኃይሎችን በኤርትራ ጦር መካከል የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገልጿል።

መቀለ የሚገኙ የቢቢሲ ምንጮች እንዲሁ ክልሉ ከኤርትራ ጋር በሚዋሰንበት ድንበር አካባቢ ግጭት ተቀስቅሶ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የከባድ መሳሪያ ጥቃቱ ከትግራይ ኃይሎች በኩል መከፈቱን ተከትሎ በስፍራው "ውጊያ ተካሂዷል" ብለዋል።

ነገር ግን የተኩስ ልውውጡ ለአጭር ጊዜ የቆየ መሆኑን እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው እግረኛን ያላካተተ በከባድ መሳሪያ የተደረገ እንደነበር ምንጩ ጨምረው ገልጸዋል።

የከባድ መሳሪያ ጥቃቱን ተከትሎ ለአጭር ጊዜ በተደረገው የተኩስ "የትግራይ ኃይሎች ወደ ኋላ አፈግፍገው ውጊያውም ቆሟል'' ሲሉ ተናግረዋል።

ጨምረውም ይህ ጥቃት "የህወሓትን ተንኳሽ ባሕሪይ የሚያሳይ ነው" ሲሉም አክለዋል።

ቢቢሲ ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት ከኤርትራ መንግሥት በኩል ይፋዊ ምላሽ ለማግኘት ሙከራ ቢያደርግም እስካሁን አልተሳካለትም።

የህወሓት ሊቀመንበር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት ለዓለም አቀፍ ተቋማት በጻፉት ይፋዊ ደብዳቤ ላይ በሰሜን ኢትዮጵያ ላለው ጦርነት አስቸኳይ መፍትሔ በማፈላለግ እንዲያግዙ እና በትግራይ ላይ ተጥሏል ያሉት ከበባ እንዲያበቃ ካልተደረገ "ሌላ አማራጭ" ለመፈለግ እንደሚገደዱ ገልፀው ነበር።

ነገር ግን ይህ "አማራጭ" ያሉት ምን እንደሆነ በደብዳቤው ላይ አልተብራራም።

ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ባስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ውስጥ የኤርትራ ሠራዊት ተሳታፊ የነበረ ሲሆን፣ በጦርነቱ ጅማሬ ወቅት የህወሓት ኃይሎች ተደጋጋሚ የሮኬት ጥቃቶችን በኤርትራ ላይ መፈጸማቸው ይታወሳል።

የትግራይ ኃይሎች በኢትዮጵያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ አማራና አፋር ክልል ተስፋፍቶ ለወራት የቆየ ሲሆን አስካሁን መቋጫ አላገኘም።

ከፌደራልና ከክልል ኃይሎች ጋር ፍጥጫ ውስጥ የሆኑት የህወሓት ኃይሎች፤ መንግሥት ሰብአዊ እርዳታ ያለገደብ ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ ያወጀውን ተኩስ አቁም ተከትሎ ጦርነቶች ጋብ ያሉ ቢመስሉም በድንገት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ተጉዘው የሠራዊቱን ዝግጁነት መጎብኘታቸው የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በቅርቡ ህወሓት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ለመሳተፍ ፍቃደኛ ያልሆኑ ልጆች ወላጆችን እያሰረ መሆኑን የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

https://www.bbc.com/amharic/news-613785 ... st+type%5D



gearhead
Member+
Posts: 5526
Joined: 08 Jun 2014, 16:29

Re: ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች የከባድ መሳሪያ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተነገረ

Post by gearhead » 09 May 2022, 10:47

የክልል መንግስታትን ለራሱ ግዛት ማስፋፊያ ጦርነቶች መማገድ የተሳነው የእብድ አማራ ፓለቲካ፣ የኤርትራን ወጣቶች ድጋሚ ለመማገድ እየቋመጠ ነው!!

Rev....such should be the headline!


Digital Weyane
Member+
Posts: 8538
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች የከባድ መሳሪያ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተነገረ

Post by Digital Weyane » 09 May 2022, 11:04

ኤርትራውያን በየአመቱ የነፃነት በአላቸውን ለማክበር በሚዘጋጁበት ወቅት ጁንታ ዎገኖቼ የበታችነትና የሽንፈት ስሜታቸውን የውሸት ወሬ በማሰራጨት ሊያስታግሱ ይሞክራሉ። :roll: :roll:





union
Member+
Posts: 6395
Joined: 14 Feb 2021, 15:24

Re: ከኤርትራ ጋር አዋሳኝ በሆኑ ቦታዎች የከባድ መሳሪያ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተነገረ

Post by union » 09 May 2022, 17:00

እመር ተገዳላይይይይይይይ

ተንከባላአአአአአአአአአይ

:lol: :lol: :lol: :lol:




Post Reply