Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 7959
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

"ጀነራል አበባው ታደሰ ከኦሮሙማው መሪ አብይ አህመድ ጋር በመሆን በአማራ ላይ የጀመረው ደም አፋሳሽ ኦፕሬሽን" ሁሉም አማራ ሊያወግዘው ይገባል!!

Post by Wedi » 08 May 2022, 16:31

"ጀነራል አበባው ታደሰ ከኦሮሙማው መሪ አብይ አህመድ ጋር በመሆን በአማራ ላይ የጀመረው ደም አፋሳሽ ኦፕሬሽን" ሁሉም አማራ ሊያወግዘው ይገባል!!


Habtamu Ayalew Teshome

ጥንቃቄ!!
======
የሚበላኝን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው !!
---------- #ሼር #ሼር
አቫንቲ ሆቴል መሽጎ ሴራ ሲጎነጉን የከረመው ቡድን
1. ተመስገን ጥሩነህ … ከደህንነት
2. ጀነራል አበባው ታደሰ …… ከመከላከያ
3. ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ … ፌደራል ፖሊስ
-----------
በአብይ አህመድ አማራን ከፋፍሎ ለማስገበር ተልዕኮ የወሰዱት ምስለኔዎች…
1. ዶ/ር ይልቃል እና ዶ/ሰማ … ለጎጃም
2 . ዶ/ር ጌታቸው ጀንበር እና ሞላ መልካሙ …ለጎንደር
3. ዶ/ር ስዩም መኮንን እና መንገሻ አውራሪስ… ወሎ (ቤተ-አማራ)
4. አቶ ግርማ የሺጥላ እና አቶ ደሳለኝ … ሸዋ
-----------
በግንቦት ወር ሊሰራ የታቀደው …
--------------
የፋኖ አመራሮችን መከፋፈል፣ የተወሰኑትን መግደል፣ የተወሰኑትን ማሰር … ከወልቃይት የአማራ ልዩ ኃይል ፋኖ እና ሚሊሻውን ማስወጣት ።
--------------
የፌደራል ፖሊሱ ዘላለም መንግሥቴ የሚመራው "የምርመራ ቡድን በሚል" በአማራ ክልል በ5 ቦታዎች ላይ አፋኝና ገዳይ ቡድን ተዋቅሯል። ጊዜያዊ እስር ቤቶች ተዘጋጅተዋል። አፋኝ ቡድኑ የፋኖን መሪዎች እየያዘ ለምርመራ ቡድኑ ያስረክባል። እምቢ ካለ ገዳይ ቡድኑ እርምጃ እንዲወስድ ይደረጋል።

ጎንደር፣ ባህርዳር ፣ ወልዲያ ፣ ባቲ እና ዳንግላ ታርጌት ማዕከላት ናቸው።
--------------
ይህ ኦፕሬሽን የሚጀምረው ግንቦት 3 ቀን በጦርነቱ አስተዋፅዖ ያደረጉ አካላት ተሸለሙ የሚል ዜና ከተሰራጨ በኋላ ነው። ፋኖን ከፋፍሎ መምቻ ፣ ልዩ ኃይሉን መበተኛ እርስ በራስ እንዳይተማመን ማድረጊያ ምዕራፍ አንድ ሽልማት በሚል ሴራ እንዲጀምር መወሰናቸው በማያሻማ መረጃ ተረጋግጧል።

ለዚህ አደገኛ ሴራ የማይመቹ 400 የልዩ ኃይል አባላት ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ጀነራል ባዩ፣ ጀነራል፣ ጀነራል አበራ፣ ጀነራል ስዩም የመሳሰሉት ተመንጥረው ተሰናብተው የሽልማት ስነስርዓት ላይ እንዲገኙ እየተለመኑ ነው። ሽልማት የሚያሰጥ ውጤት ያመጡ ጀነራሎች ለምን ተባረሩ ? ምላሹ ግልፅ ነው……