ሀተታው ምንም አይነፋም፣ ቅራቅንቦ ነው፣ በሌላ አባባል እኔን አስገደደህ ሀጎስ የሚል ስም የያዘ መታወቂያ ከሰጠህ በሁዋላ እኔን መልሰህ ትግሬ ነህ እንደማለት ነው፣፣ ገባህ?
ሌላ የተለየ ማስረጃ ካለ አቅርብ
sarcasm wrote: ↑11 May 2022, 07:13You seem to assume that Tigray Region has taken Western Tigray from Amhara Region. That is not factually correct. Tigray Region did not take any land from Amhara Region. Regions and their boundaries were setup in the early 1990s. Before then, there were no regions. Tigray or Amhara have not changed thier boundaries since they were setup.
Haile Selassie's Gonder, Shoa, Wello and Gojam are not equal to current Amhara Region.
See the below excerpt from another thread:
ከአማራ ክልል በትግራይ ክልል ላይ የሚነሳውን የርስትና(የመሬት ይገባኛል) የማነት ጥያቄ በተመለከተ፤ ጥያቄውን ለመመለስ የተሞከረበት መንገድ ስህተትና በጣም አደገኛ መሆኑን አሁን ያስከተለውን የጥፋት መዘዝ እያየነው እንገኛለን፡፡
ክልሎች ህልውናቸውን ያገኙት በህገ መንግስቱ መሰረት ነው፡፡ ክልሎች የተዋቀሩት ደግሞ የህዝብ አሰፋፈር፣ ቋንቋ፣ ማንነት እና ፈቃድ በሚሉ ህገመንግስታዊ መስፈርቶች ላይ በመመስረት ነው፡፡ ስለሆነም ህገመንግስቱ ክልሎችን ከማወቀሩ በፊት በነበሩ ክ/ሀገሮች ውስጥ የነበሩ ህዝቦችን፤ ለምሳሌ ጎንደር፤ በውስጡ አማርኛ ተነጋሪዎች እና የሰፈሩበትን ቦታ፣ ትግርኛ ተናጋሪዎችና የሰፈሩበትን ቦታ፣ አገውኛ ተናጋሪዎችና የሰፈሩበትን ቦታ፣ ቅማንቶችና የሰፈሩበትን ቦታ ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መነሻነት ወደ አዲሶቹ ክልሎች እንዲካለሉ ሆነዋል፡፡ በሌላ አባባል ጎንደር (በቀደመው ጊዜ ቤጌምድርና ስሜን የሚባለውን) በክ/ሀገርነቱ ወቅት አማርኛ ተነጋሪ ህዝቦች ብቻ የሰፈሩበት አስተደደር አልነበረም፤ እንዲሁም “አማራ” የሚባል አስተዳደርም አልነበረም፡፡ ስለሆነም በጎንደር ክ/ሀገር ስር ከነበረ አስተደደር ወደ ትግራይ ክልል አስተዳደር የተዛወሩ ትግርኛ ተናጋሪዎች እና የሰፈሩበትን ቦታ፤ ቦታውን ብቻ መርጦ “ድሮ በጎንደር ክ/ሀገር ስር ስለነበረ የአማራው መሬት የአማራው ርስት ነው” ብሎ ጥያቄ ማንሳት ስህተት ነው፡፡
በዚህ በተሳሳተ አመክንዮ መሰረት ጥያቄው የሚቀጥል ከሆነ ጦርነት የማይለኮስበት ክልል አይኖርም፡፡ ለምሳሌ፡- አፋር የሚባል ክልል አይኖርም፡፡ ምክንያቱም ቦታው ከወሎና ከትግራይ ክ/ሀገሮች በተገኘ መሬት የተዋቀረ ስለሆነ፡፡ ቤንሻንጉልና ጉሙዝ የሚባል ክልል አይኖርም፡፡ ምክያቱም ከጎጃምና ወለጋ ክ/ሀገሮች በተገኘ መሬት የተዋቀረ ስለሆነ፡፡ ወዘተ…
ጥያቄውን ለመመለስ የተሞከረበት መንገድ፡-
ከአማራ ክልል የተነሳው የመሬት ወይንም የርስት ጥያቄ ስህተት እንደሆነ ከላይ ገልጫለሁ፡፡ ይሁን እንጂ የሚነሳ የማንነት ጥያቄ መኖር የለበትም ማለቴ ግን አይደለም፡፡ የማንነት ጥያቄ ማለት በአንድ በተወሰነ ቦታ፤ ለምሳሌ በወልቃይት፤ አብዛኛው ነዋሪ አማርኛ ተናጋሪ ሆኖ በትግራይ ክልል ውስጥ እንዲካተት ተደርጎ ከሆነ ጥያቄው ለማንነቴ ምላሽ በሚሰጠኝ ክልል ውስጥ ልተዳደር የሚል የመብት ጥያቄ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ የሚቀርብበት እና እልባት የሚያገኝበት መንገድ ደግሞ በህገመንግስቱ አንቀጽ 48 “የአከላለል ለውጦች” በሚል በተቀመጠው ሰላማዊ አግባብ መሰረት ብቻ መሆን አለበት፡፡
አንቀጹ የሚለው በአጭር ሲገለጽ፡- ጥያቄው ሲነሳ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ክልሎች በስምምነት ይፈጸማል፡፡ መስማማት ካልቻሉ የፈደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄው በቀረበለት በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል ይላል ፡፡
ከዚህ ከላይ ከተጠቀሰው ህገመንግስታዊ መንገድ ውጭ የአማራ ክልል አሁን በተያዘው የጦርነት መንገድ ለመፍታት መሞከሩ አደገኛ ስህተት ነው፡፡ አደገኛነቱ ደግሞ ለሌሎች ተመሳሳይ ጥያቄ ለሚኖራቸው ክልሎች “መፍትሄው ጉልበተኛ መሆን ነው!” የሚል የእርስ በርስ የጦርነት አዋጅ ስለሚሆን ነው፡፡
ህገመንግስቱ ለትግራይ እንዲበጅ ሆኖ የተቀረጸ ስለሆነ ዋጋ የለውም የሚባል ከሆነም፤ ስለዚህ መጀመሪያ ህገመንግስቱን በሰላማዊ መንገድ መቀየር ነው፡፡ አለበለዚያ የዚህ ሁሉ ዘመቻ ዳንኪራ ተልእኮው ህግም ድንበርም የማስከበር ሳይሆን የመተላለቅና ዘር የማጥፋት ይሆናል፡፡ ይሄም አያ ተቤው (አያ ተበጀ፡ ተስፋ ስንታየሁ በጻፈው “ጨዋታ-ጦቢያ በእየሩሳሌም” በሚል መጽሐፍ ላይ ያሉ ከጎንደር የፈለሱ ቤተ-እስራኤላዊ ገጸ ባህሪ ናቸው) እግዜርን ሲወቅሱት “አንተ ምናለብህ ቤትህን ሰው እማይደርስበት ቆጥ ላይ ሰቅለህ የተቆጣ በየት አድርጎ ያግኝህ!” እንዳሉት፤ አዳሜ ምን አለበት ግፋ በለው እሚለው ከወላፈኑ ርቆ በሌላው ደም ነው፡፡
1942-1974: 12 provinces or governates-general (taklai ghizat) by Imperial Ethiopian Government
Begemder, Gojjam, Wollo, Shewa (Shoa), Gamu-Gofa, Illubabor, Kaffa, Sidamo, Tigray, Welega, Hararghe, Arsi
1987 - early 1990s
The National Shengo established 30 regions, consisting of five autonomous regions, and twenty-five administrative regions.
The five autonomous regions were: Aseb, Dire Dawa, Eritrea, Ogaden, Tigray
The twenty-five administrative regions were:[7]
Addis Ababa, Arsi, Asosa, Bale, Borana, East Gojam, East Harerge, East Shewa
Gambela Ilubabor KefaMetekelNorth GonderNorth OmoNorth Shewa North Welo, Sidamo South Gonder, South Omo South Shewa South Wollo Welega West Gojam West Hararghe West Shewa