Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 07 May 2022, 03:38

የኢትዮጵያ ችግር
ፖለቲካ አይደለም
ኢኮኖሚ አይደለም
ጦርነት አይደለም
ሰላም አይደለም
ሃይማኖት አይደለም
እውቀት አይደለም
ካልቸር አይደለም
ዳቦ አይደለም
አትክልት አይደለም
የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው
ኢትዮጵያ የሌላት መሪ ነው !

ለምንድን ነው ኢትዮጵያ በዚህ ሆነ በዚያ አንድ ወጥ የሆነ መሪነት አጥታ የዉሃ ላይ ኩበት የሆነችው?

የፖለቲካ መሪዎች ሰዎች ናቸው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው ልዩ የሆነ ስብዕና እና የፖለቲካ ባህሪ አላቸው። በዚያ ፐርሰናሊቲና ቢሄቪየር አማካይነት ነው አገሪቱን አይተው ወስነው፣ ይህ ይሁን፣ ያ አይሁን ብለው የሚያዙት የሚመሩት ።

እስከዛሬ ድረስ ፖለቲካል ሳይኮሎጂ የደረሰባቸው አራት አንድን የፖለቲካ መሪ የሚነዱ ፍላጎት ተለይተው ታውቀዋል። ልብ እንበል ከአቢይ አህመድ አንስቶ እስከ አንድ ተራ ካድሬ ስለ አገር አቀፍ አጀንዳም ሆነ ስለቀበሌው ጉዳይ ሲያስብ ከውስጥ ሆነው የሚነዱት ፍላጎትች ማለት ነው።

እነዚህ ፍላጎቶሽ
(1) ገንዘብ ወይም ሃብት
(2) ማንነትና የማንነት ክብር እውቅና ማግኘት
(3) ዝና እና ስኬታማ በመሆን አድናቆትን ማግኘት
(4) ባልስልጣን መሆንና ሃያል መሆን ናቸው ።

አሁን በነዚህ መለኪያዎች መሰረት ለምሳሌ የብልጽግና ፓርቲ ለምን መምራት እንዳቃተው እንመልከት፤
1
ስለዚህ አንድ የፖለቲካ መሪ የራሱ ፖለቲካዊ ሳይኮሎጂ ፣ የፖለቲካ ባህሪ አለው ብለናል። አንድ የፖለቲካ መሪ ገንዘብ ከሌለው ድሃ ከሆነ የመጅመሪያ ገፊ ፍላጎቱ መሰረታዊ ፍላጎት (ምግብ፣ ልብስ፣ ቤት)፣ ገንዘብና ሃብት ነው። ምናልባት ብልጽግና 5 ሚሊዮን 99% በዚህ የገንዘብ ፍላጎት የሚነዱ ናቸው። ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ትልቁ የመሪነት ችግር የሃብት የሙስና ችግር የሚሆነው። የአቢይ ተቀዳሚ ፍላጎት ገንዘብ ስላልሆነ ብዙሃኑን የበታች ታዛዦቹን ሌቦች ይላቸዋል ። በዚህ ምንክኛት እነሱም አያምኑትም፣ እሱም አያምናቸውም ።
2
ሁለተኛው የፖለቲካ መሪ ገፊ ፍላጎት ማንነቱ፣ ጎሳው፣ ብሄረተኝነቱ ወይም የኢትዮጵያ ብሄረትኝነቱ ናቸው ። እና ከዚህ ጋር የተያያዘው ዲግኒቲ፣ ክብር፣ በሌሎች ተቀባይነት ማግኘት ነው ። ማንነት ጠባብና ሌላውን የሚለይ ከሆነ ጎሳዊነት፣ ዘረኝነት ወይም ብሄረኘት ይሆናል፣ ያ ደሞ አግላይ ፍላጎት፣ የእኔ ከሌላው ይሻላል የሚል ዘረኘትን ያስከትላል። 5 ሚሊዮኑ ብልጽግናዎች በርዕዮተ አለም ደረጃ የሚያምኑት በጎሳ ማንነት ነው ። ሺ ግዜ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ ቢያወሩ ከገንዘብ ቀጥሎ የሚነዳቸው ሞቲቬሽን የጎሳ ማንነታቸው ነው ። ለዚህ ነው አቢይ ዋና ችግራቸው የብሄርና ያውራጃ ማንነት ነው ያለው። ይህ ማለት ደሞ አማራ ኦሮሞውን አያምንም ። ኦሮሞው አማራውን አያምንም። ዛሬ የትግሬ ብልጽግናን ማን ሊያምን ይችላል? ታዲያ ይህን የመሰሉ የጎሳ ጥርቅሞች እንዴት ወጥ የሆነ ኢትዮጵያዊ መሪነት ሲሰጡ ይችላሉ?
3
ሶስተኛው ለራስ ዋጋ ከመስጠት (ከሰልፍ ኤስቲም) ጋር የተያያዘ ሲሆን ዝና፣ መታወቅን ፍለጋ ነው። ያ ደሞ የስኬት መለኪያ ሆኖ ይወሰዳል። ለምሳሌ አቢይ ስኬታማ መሆንን በጣም ይፈልጋል። ለምን? ዝነኛ ለመሆን። ለምን? ሌጋሲ ቅርስ አሻራ ለመተው። ለምን? ስም ከመቃብር በላይ ስለሆነ። ለምን? ላለመረሳት ። ኢሞርታል ለመሆን። ከትውልድ ትውልድ ለመዘከር፣ ለመታውስ። ይህ ትልቁ የአቢይ ነጂ ፍላጎት ነው። ሰው በስራው በስኬቱ ሲታወስ ይኖራል። አቢይ በዚህ እጅግ የሚገፋ መሪ ነው። ሰልፍ ኤስቲምና የስኬት ፍላጎት ነው የሚገፋው ። እሱ በዚህ ተገፍቶ ፕሮጀክቶች ለመፈጸም ሲፈልግ የቀሩት ካድሬዎች ገፊ ፍላጎት ዝና ሳላሆነ የነሱን ፍጹም ትብብር አያገኝም ። ለዚህ የበላይ መሪዎች የበታቾቻውን በጥቅማ ጥቅም ለመግዛት የሚገደዱት ። አቢይ በንግግር፣ በስልጠና ሊያሸንፋቸው ቢሞክርም አልቻለም።
4
አራተኛውና ከፍተኛው ስልጣንና ሃይል መሻት ነው ። በግለሰብ ደረጃ የፓወር ፍላጎት ሳይኮሎጂ የሌላቸው መሪዎች ለስልጣን ግድ የላቸውም። ግን ሁልግዜ ስለስልታንና ሃይል የሚያሰሉ መሪዎች አንድ ነገር ለማደግ ሲሰበሰቡ የሚያስጨንቃቸው ያገር አጀንዳ ሳይሆን እስታተስ ማኔጅመንት ይባላል። ስለስልጣናቸው ሲጋጋጡ ነው ግዜው የሚጠፋው ። በተለይ የስልጣን ክፍፍል በጎሳ በሚቀመርበት ፓርቲና መንግስት ይህ እጅግ ግዙፉ ቀውስ ነው። ይህ ሁለተኛው ያቢይ ዋና ገፊ ሞቲቬሽን ነው ። ለምሳሌ በአቢይና በትግሬዎቹ መሃል አልታረቅ ያለው ይህ ነጂ የስልጣን ፍላጎት ነው። ልብ በሉ ትግሬዎቹ ሃብት ነበራቸው ። የራሳቸው ጎሳ የነካባቸው አልነበረም ። ለዝናም ድግ የላቸውም። ስልጣንና ሃይል ብቸኛ ፍላጎታቸው ነው። አቢይም ከልጅነቱ ጀምሮ ስልጣን እና ሃይል የሚፈልግ ሰው ነው ።
ይህ ብቻ አይደለም ...

አቢይ ብዙ ግዜ በሰልፍ ኤስቲምና ስኬት ዝና ላይ ያለ ምሪ ነው ። ለምሳሌ አንድ አወዛጋቢ እርምጃ ወስዶ በሌሎች መጠላት የማይፈልገው ስሙ እንዳይጠፋ፣ እንዳይጠላ፣ አሻራው ሌጋሲው እንዳይበላሽበት ነው።

ሁለት ቁጥር ውስጥ ካሉት የጎሳ ማንነት ክብር ፈላጊዎች ጋር ችግር አለው። ከኢትዮጵያ ብሄረተኞች ጋርም ችግር አለው። እሱ የአፊሊዬሽን ጥማተኛ ስላሆነ ። በቅርብ ሲናገር የጎሳ ብሄረተኛም የኢትዮጵያ ናሽናሊስት ምሆን መጥፎ ነው ። ጥሩ ነገር አርበኛ መሆን ነው ብሏል ። የኢትዮጵያ ናሺናሊስት አትሁኑ ያለ የመጀምሪያው የኢትዮጵያ መሪ ነው። ይህ ትልቅ ችግር ነው። የሱ ጥማት የራስ ከፍታና ዝና ስለሆነ!

ትልቁ ጥያቄ አቢይ ስለ ፓወር ያለው ሳይኮሎጂ ምንድን ነው የሚለ ነው። ለምንድን ነው የሚናገረውና የሚሰራው አንድ መሆን ያልቻለው? አቢይ ጠንካራ የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በሃይል አማካይነት ብዙ ነገር መለወጥ ሲችል ያ እንዳያደርግ ፐርሰናሊቲው ያግደዋል ። እሱ እንደ ዝነኛ አርቲስት መወደድን የሚሻ እንጂ ከማል አታቱርክ መሆን የሚችል ስብዕና የለውም ።

ለምሳሌ በዝና ጥማት የሚነዳ ሰው ለምን መደመርን ይፍለጋል? በስልጣንና ሃይል መገፋት የሌሎችን ፍቅር አያስገኝም። ኤፌክቲቭ እና ተግባሪ መሪ ምናልባት መፈራትን እንጂ በመወደድ ስመ ገናና እና ታዋቂ አያደርግም። ለዚህ ነው በአፉ ስለ ጠንካራ እርምጃዎች ተናግሮ በትግባር ወደ ኋላ የሚለው!!
አቢይ በመወደድ ዝነኛ መሆንን እንጂ በመፈራት ጠንካራ መሪ መባልን አይፈልግም! ፐርሶናሊቲው ያ ስላልሆነ!!!
Last edited by Horus on 08 May 2022, 01:49, edited 6 times in total.

Educator
Member
Posts: 1968
Joined: 03 Jun 2021, 00:14

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Educator » 07 May 2022, 08:19

Wow..
Assegid S. wrote:
07 May 2022, 05:39

Right
Member
Posts: 2723
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Right » 07 May 2022, 11:55

He mixes English and Amharic intensively.
He is a preacher with oratory gift to an elite audience that understands the English language.
But he is very good.
I have listened to audio of so many Amharic speakers. They can not finish a sentence with out throwing an English word in it.
Listen to the audio of old notable speakers they do not dilute foreign languages in their speech but quickly give an explanation if circumstances forces them to do so.
Hadis Alemayhu, Yedenkatchew Tesema, Mesfin Wold Mariam, Asrat Woldyes …they have a commanding knowledge of English language and Hadis & Yidnakachew masters Italian & French as well.
I wish politicians learn from it. I hate it when a head of state or a minster cannot finish a sentence without mixing two languages. It is even worst when a head of state abandon his own language and try to explain himself in a foreign language which he has no command.

Abdisa
Member+
Posts: 5732
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Abdisa » 07 May 2022, 13:11

I think Ethiopia's chief problem -- even its worst enemy -- is Ethiopian officials who receive money from external actors in exchange for serving the interests of foreign powers at the expense of their own national interest.

መምህር ዶ/ር ዘበነ ለማ during his speech in the video below recalled a story from a book about an Italian viceroy in Ethiopia who sent a message to Mussolini asking for money, for he had learned that bribing Ethiopian officials was intrinsically more effective to conquering the nation than waging a war.

This means that, even if Ethiopia has a great leader, so long as there exist corrupt government officials who would sell their mothers for a few dollars, a "one step forward, two steps back" situation is almost always inevitable.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 07 May 2022, 15:44

Assegid S. wrote:
07 May 2022, 05:39
Assegid s.

Thank you. እኔ ይህን ፓስተር ስሰማው ለመጀምሪያ ግዜዬ ነው! መልክቱ በጣም ተስማምቶኛል! እኔ ይህን ሃረግ ፖስት ያደረኩት ትላንት 'The psychological Assessment of Political leaders' የሚባል በመሪዎች ስብዕና (ፐርሶናሊቲ) እና በመሪዎች ፖለቲካዊ ባህሪ (ፖለቲካል ቢሄቪየር) ላይ የተደረገ ጥናት ሳነብ ንድድ ብሎኝ የላይኞቹ ቃላት የለጠፍኳቸው ። እኛ ስለብዙ ችግሮች እዚም እዛም እንላለን። ግን ፓስተሩ እንዳለው ያገራችን ችግር ተራው ሕዝብ (ሰፊው ሕዝብ) የደረሰበት ንቃተ ሃሳቤና ንቃተ ህሊና የደረሱ መሪዎች ስለሌሉን ነው ። ይህን ማጽሃፍ ሳነብ ልክ እንደ አሜርካኑ ዊድሮ ዊልሰን አቢይ አህመድ እንዴት እራሱ የራሱ ጠላት እንደ ሆነና እንዴት እራሱን ለውድቀት እያዘጋጀ መሆኑ እየታየኝ ነው ። ኢትዮጵያን ከጎሳ ህሳቤና ከጎሳ ስሌት፣ ከጎሳ ፍልስፍና ውጭ መምራት ካልቻለ አለምንም ጥርጥር የሚወድቅ መሪ ይሆናል።

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 08 May 2022, 01:35

ለምንድን ነው ኢትዮጵያ በዚህ ሆነ በዚያ አንድ ወጥ የሆነ መሪነት አጥታ የዉሃ ላይ ኩበት የሆነችው? የፖለቲካ መሪዎች ሰዎች ናቸው። እያንዳንዳቸው የራሳቸው ልዩ የሆነ ስብዕና እና የፖለቲካ ባህሪ አላቸው። በዚያ ፐርሰናሊቲና ቢሄቪየር አማካይነት ነው አገሪቱን አይተው ወስነው፣ ይህ ይሁን፣ ያ አይሁን ብለው የሚያዙት የሚመሩት ።
እስከዛሬ ድረስ ፖለቲካል ሳይኮሎጂ የደረሰባቸው አራት አንድን የፖለቲካ መሪ የሚነዱ ፍላጎት ተለይተው ታውቀዋል። ልብ እንበል ከአቢይ አህመድ አንስቶ እስከ አንድ ተራ ካድሬ ስለ አገር አቀፍ አጀንዳም ሆነ ስለቀበሌው ጉዳይ ሲያስብ ከውስጥ ሆነው የሚነዱት ፍላጎትች ማለት ነው።
እነዚህ ፍላጎቶሽ
(1) ገንዘብ ወይም ሃብት
(2) ማንነትና የማንነት ክብር እውቅና ማግኘት
(3) ዝና እና ሴታማ በመሆን አድናቆትን ማግኘት
(4) ባልስልጣን መሆንና ሃያል መሆን ናቸው ።
አሁን በነዚህ መለኪያዎች መሰረት ለምሳሌ የብልጽግና ፓርቲ ለምን መምራት እንዳቃተው እንመልከት፤
1
ስለዚህ አንድ የፖለቲካ መሪ የራሱ ፖለቲካዊ ሳይኮሎጂ ፣ የፖለቲካ ባህሪ አለው ብለናል። አንድ የፖለቲካ መሪ ገንዘብ ከሌለው ድሃ ከሆነ የመጅመሪያ ገፊ ፍላጎቱ መሰረታዊ ፍላጎት (ምግብ፣ ልብስ፣ ቤት)፣ ገንዘብና ሃብት ነው። ምናልባት ብልጽግና 5 ሚሊዮን 99% በዚህ የገንዘብ ፍላጎት የሚነዱ ናቸው። ለዚህ ነው በኢትዮጵያ ትልቁ የመሪነት ችግር የሃብት የሙስና ችግር የሚሆነው። የአቢይ ተቀዳሚ ፍላጎት ገንዘብ ስላልሆነ ብዙሃኑን የበታች ታዛዦቹን ሌቦች ይላቸዋል ። በዚህ ምንክኛት እነሱም አያምኑትም፣ እሱም አያምናቸውም ።
2
ሁለተኛው የፖለቲካ መሪ ገፊ ፍላጎት ማንነቱ፣ ጎሳው፣ ብሄረተኝነቱ ወይም የኢትዮጵያ ብሄረትኝነቱ ናቸው ። እና ከዚህ ጋር የተያያዘው ዲግኒቲ፣ ክብር፣ በሌሎች ተቀባይነት ማግኘት ነው ። ማንነት ጠባብና ሌላውን የሚለይ ከሆነ ጎሳዊነት፣ ዘረኝነት ወይም ብሄረኘት ይሆናል፣ ያ ደሞ አግላይ ፍላጎት፣ የእኔ ከሌላው ይሻላል የሚል ዘረኘትን ያስከትላል። 5 ሚሊዮኑ ብልጽግናዎች በርዕዮተ አለም ደረጃ የሚያምኑት በጎሳ ማንነት ነው ። ሺ ግዜ ስለ ኢትዮጵያ አጀንዳ ቢያወሩ ከገንዘብ ቀጥሎ የሚነዳቸው ሞቲቬሽን የጎሳ ማንነታቸው ነው ። ለዚህ ነው አቢይ ዋና ችግራቸው የብሄርና ያውራጃ ማንነት ነው ያለው። ይህ ማለት ደሞ አማራ ኦሮሞውን አያምንም ። ኦሮሞው አማራውን አያምንም። ዛሬ የትግሬ ብልጽግናን ማን ሊያምን ይችላል? ታዲያ ይህን የመሰሉ የጎሳ ጥርቅሞች እንዴት ወጥ የሆነ ኢትዮጵያዊ መሪነት ሲሰጡ ይችላሉ?
3
ሶስተኛው ለራስ ዋጋ ከመስጠት (ከሰልፍ ኤስቲም) ጋር የተያያዘ ሲሆን ዝና፣ መታወቅን ፍለጋ ነው። ያ ደሞ የስኬት መለኪያ ሆኖ ይወሰዳል። ለምሳሌ አቢይ ስኬታማ መሆንን በጣም ይፈልጋል። ለምን? ዝነኛ ለመሆን። ለምን? ሌጋሲ ቅርስ አሻራ ለመተው። ለምን? ስም ከመቃብር በላይ ስለሆነ። ለምን? ላለመረሳት ። ኢሞርታል ለመሆን። ከትውልድ ትውልድ ለመዘከር፣ ለመታውስ። ይህ ትልቁ የአቢይ ነጂ ፍላጎት ነው። ሰው በስራው በስኬቱ ሲታወስ ይኖራል። አቢይ በዚህ እጅግ የሚገፋ መሪ ነው። ሰልፍ ኤስቲምና የስኬት ፍላጎት ነው የሚገፋው ። እሱ በዚህ ተገፍቶ ፕሮጀክቶች ለመፈጸም ሲፈልግ የቀሩት ካድሬዎች ገፊ ፍላጎት ዝና ሳላሆነ የነሱን ፍጹም ትብብር አያገኝም ። ለዚህ የበላይ መሪዎች የበታቾቻውን በጥቅማ ጥቅም ለመግዛት የሚገደዱት ። አቢይ በንግግር፣ በስልጠና ሊያሸንፋቸው ቢሞክርም አልቻለም።
4
አራተኛውና ከፍተኛው ስልጣንና ሃይል መሻት ነው ። በግለሰብ ደረጃ የፓወር ፍላጎት ሳይኮሎጂ የሌላቸው መሪዎች ለስልጣን ግድ የላቸውም። ግን ሁልግዜ ስለስልታንና ሃይል የሚያሰሉ መሪዎች አንድ ነገር ለማደግ ሲሰበሰቡ የሚያስጨንቃቸው ያገር አጀንዳ ሳይሆን እስታተስ ማኔጅመንት ይባላል። ስለስልጣናቸው ሲጋጋጡ ነው ግዜው የሚጠፋው ። በተለይ የስልጣን ክፍፍል በጎሳ በሚቀመርበት ፓርቲና መንግስት ይህ እጅግ ግዙፉ ቀውስ ነው። ይህ ሁለተኛው ያቢይ ዋና ገፊ ሞቲቬሽን ነው ። ለምሳሌ በአቢይና በትግሬዎቹ መሃል አልታረቅ ያለው ይህ ነጂ የስልጣን ፍላጎት ነው። ልብ በሉ ትግሬዎቹ ሃብት ነበራቸው ። የራሳቸው ጎሳ የነካባቸው አልነበረም ። ለዝናም ድግ የላቸውም። ስልጣንና ሃይል ብቸኛ ፍላጎታቸው ነው። አቢይም ከልጅነቱ ጀምሮ ስልጣን እና ሃይል የሚፈልግ ሰው ነው ።
ይህ ብቻ አይደለም ...
አቢይ ብዙ ግዜ በሰልፍ ኤስቲምና ስኬት ዝና ላይ ያለ ምሪ ነው ። ለምሳሌ አንድ አወዛጋቢ እርምጃ ወስዶ በሌሎች መጠላት የማይፈልገው ስሙ እንዳይጠፋ፣ እንዳይጠላ፣ አሻራው ሌጋሲው እንዳይበላሽበት ነው።
ሁለት ቁጥር ውስጥ ካሉት የጎሳ ማንነት ክብር ፈላጊዎች ጋር ችግር አለው። ከኢትዮጵያ ብሄረተኞች ጋርም ችግር አለው። እሱ የአፊሊዬሽን ጥማተኛ ስላሆነ ። በቅርብ ሲናገር የጎሳ ብሄረተኛም የኢትዮጵያ ናሽናሊስት ምሆን መጥፎ ነው ። ጥሩ ነገር አርበኛ መሆን ነው ብሏል ። የኢትዮጵያ ናሺናሊስት አትሁኑ ያለ የመጀምሪያው የኢትዮጵያ መሪ ነው። ይህ ትልቅ ችግር ነው። የሱ ጥማት የራስ ከፍታና ዝና ስለሆነ!
ትልቁ ጥያቄ አቢይ ስለ ፓወር ያለው ሳይኮሎጂ ምንድን ነው የሚለ ነው። ለምንድን ነው የሚናገረውና የሚሰራው አንድ መሆን ያልቻለው? አቢይ ጠንካራ የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ በሃይል አማካይነት ብዙ ነገር መለወጥ ሲችል ያ እንዳያደርግ ፐርሰናሊቲው ያግደዋል ። እሱ እንደ ዝነኛ አርቲስት መወደድን የሚሻ እንጂ ከማል አታቱርክ መሆን የሚችል ስብዕና የለውም ።
ለምሳሌ በዝና ጥማት የሚነዳ ሰው ለምን መደመርን ይፍለጋል? በስልጣንና አይል መገፋት የሌሎችን ፍቅር አያስገኝም። ኤፌክቲቭ እና ተግባሪ መሪ ምናልባት መፈራትን እንጂ በመወደድ ስመ ገናና እና ታዋቂ አያደርግም። ለዚህ ነው በአፉ ስለ ጠንካራ እርምጃዎች ተናግሮ በትግባር ወደ ኋላ የሚለው!!
አቢይ በመወደድ ዝነኛ መሆንን እንጂ በመፈራት ጠንካራ መሪ መባልን አይፈልግም! ፐርሶናሊቲው ያ ስላልሆነ!!!

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Assegid S. » 08 May 2022, 10:21

* Educator, Right, and Abdisa ... thanks a lot for your comment.

* Horus, Your are welcome. ከአንተ ሃሳብ ጋር ከሞላ ጎደል እስማማለሁ፥ ለዚህም ነው ምልከታህን ለማጠንከር የዶር ዘበነን ቪዲዮ የለጠፍኩት።

ሰሞኑን ያነበብካቸው ጽሑፎች ጥሩ ግንዛቤ እንደጨመሩልህ አምናለሁ። እናም የኢትዮዽያ ችግር የበቃ መሪ ማግኘት አለመቻል ነው ብለን ከተስማማን፥ የሚቀጥለው ጥያቄ "መሪ ወይንም ደግሞ የበቃ መሪ ምን ዓይነት ነው?” የሚለው ይሆናል። በአንተ አስተያየትና ግንዛቤ … እጅግ ባጠረ መልኩ … የተዋጣለት መሪን እንዴት ትገልፀዋለህ? በኣንተ ሚዛን የበቃ መሪ ምን ዓይነት ነው? ቀድሞም ይሁን አሁን ከነበሩት መሪዎችስ መካከል፥ የመሪን ባህሪና ተግባር ተላብሶ ያየኸው ማንን ነው?

ይህ ጥያቄ ሰፊና ብዙ አከራካሪ ነጥቦችን ሊያስነሳ ስለሚችል በጣም ሰፊ (ከፅሁፍ ውጪ የንግግር) መድረክ እንደሚፈልግ አምናለሁ። ሆኖም ግን፦ ለምሳሌ እንዲሆን የእኔን አጭር ምልከታ ሳስቀምጥ:

የተዋጣለት መሪ ብዙዎች የሚከተሉት እንጂ ብዙዎችን የሚመራ አይደለም። ይህን የቆየ እምነቴንም ከዚህ ቀደም በ Vote a person that you follow, not that leads you (2017) በሚል ሀሳብ ገልጬዋለሁ።

የሀገር መሪ ባህሪና ተግባር ያየሁባቸው ግለሰቦች፦ ካለፉት … ነፍስ ይማር! ሮበርት ሙጋቤና Hugo Chavez (Venezuela) ሲሆኑ ... አሁን በህይወት ካሉት ደግሞ ቭላድሚር ፑቲንና ኢሳያስ አፈወርቄ ተጠቃሾች ናቸው። በእኔ ግለሰባዊ እምነት የመሪ ብቃት መለኪያ ሚዛን መሆን የሚገባው የሀገርና የህዝብ ደህንነት እንጂ የከፍተኛ ተቋማት ወረቀት(ዲግሪና ዲፕሎማ) ወይንም የተቀረው ዓለም ጥቅምና መሻት አይደለም።

P.S. በጣም አጭር ሀረግ መጠቀም ከፈቀድክ ለማለት እንጂ ... አለበለዚያ "ጠቅላይ ሚንስትር ኣብይ አህመድ ከዝና ፈላጊነት ወደ ጠንካራ መሪነት መለወጥ አለበት" የሚለው ፖስት ጥያቄዬን ይመልሰዋል።

መልካም ሁን Hurus.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 08 May 2022, 12:07

አሰግድ፣

ይህን የዛሬ ትንተናህን ሳነብ እየሳቁኝ ነበር፤ ለምን ካልክ እኔ አቢይ ጠንካራ መሪ መሆን አለበት የሚለው መደምደሚያ የደረስኩት በ4ቱ የመሪነት ሞቲቬሽኖች ተመርቼ ነው። ከዚያ በፊት አቢይ አርት ከመውደዱና ትራንስፎርማቲቨ አመራር የሚባል ሞዴል ውሰጥ ከመሆኑ ያለፈ ፕሮፋይል አልነበረኝም። እርግጥ እሱ እራሱን አገልጋይ መሪ (ሰርቨንት ሊደር) ነኝ ቢልም ማለት ነው ።

አንተ የምትለው የመሪ አይነት ብዙ ብዙ የተጻፈበት 'ታላቁ መሪ' 'ታላቁ ሰው ' 'ጀግና መሪ' የሚባለው ሞዴል ነው ። ያው አንተ እንዳልከው እነ ከማል አታቱርክ፣ ማኦ ሴቱንግ፣ ምኒልክ እያለ ይሄዳል። አሁን ላይ ቆመን ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ብቁ መሪ ምን ይመስላል ላልከው በኋላ በሰፊው እመለስበታለሁ ።

መሪና ተመሪ፣ መሪና ሕዝብ መሃል መኖር ስላለበት ዳይናሚክስ የእኔ እምነት አንድ ሕዝብ በአንድ ታሪካዊ ወቅት በደረሰበት የእድገት ደረጃ ልክ መሪውን ይወልዳል፣ መሪውን ያንጻል፣ ለዚያ ታሪካዊ ተልኮ ሳይኮሎጂው፣ ፐርሰናሊቲውና ባህሪው (ቢሄቪየሩ) ብቁ የሆነ ግለሰብ ተነስቶ የህዝቡን ችግርና ፍላጎት ያደራጅና ይመራል። ስለዚህ ዲያሌክቲካል ነው ። የህዝቡን፣ ያገሩን፣ የዘመኑ ቁልፍ ጥያቄ በውል ያልገባው ሰው ሺ ግዜ የተማረ ቢሆን መሪ ሊሆን አይችልም። በሌላ በኩል አንድ ሰው የህዝቡ ችግርና ፍላጎት ስላወቀ ብቻ ሊመራ አይችልም ። መሪነት ችግር መፍታት (ፕሮብሌም ሶልቪንግ) ስለሆነ ከፍተኛ አገር አቀፍ፣ አለም አቀፍ፣ ወዘተ መፍትሄዎች ዲዛይን የማድረግ፣ ሞዴል እማድረግ፣ ፓካኤጅ የማድረግ ችሎታ ይጠይቃል። እዚያ ላይ ነው ያልከው ጠንካራ መሪ፣ ታላቅ መሪ የሚባለው ባህሪ የሚመጣው።

ለምሳሌ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ አቢይ አህመድ የጎሳ ፍልስፍና ከኢትዮጵያዊነት ፍልስፍና አዋህዳለሁ የሚለውና በዚያም ሳቢያ የውሃ ላይ ኩበት መሆኑ የድክመቱ አንድ መለከያ ነው ። መጀምሪያ ተንካራ አገርና ጠንካራ መንግስት ላይ ቆሞ ነው የውስጥ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ችግሮችን ሊፈታ የሚችለው። እርግጥ እያንዳንዱ የአገሪቱ ሁኔት እንደየአገሩ ይለያያል። የተረጋጋ ሲስተም ባለበት መሪው ስራ አስኪያ ውይም ኤክዘከቲቭ ነው የሚሆነው ። እንደ ኢትዮጵያ ባለ ቀውስ ውስጥ መሪው አንድ ጠንካራ አገርና መንግስት የሚቀርጽ ሞዴል አቅርቦ ያ ያልከው ብዙ ሰው እንዲከተለው ማድረግ አለበት ።

ይቀጥላል!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 08 May 2022, 18:20

አሰግድ፣
አንድ ብቁ መሪ ምን ይመሳል? ላልከው እና መልሱ አጭር ይሁን ባልከው መሰረት በጥቅሉ ብቁ መሪ የሚመራውን ሕዝብ፣ ቡድን፣ ወይም ድርጅት መፍታት እሜፈልገውን ችግር አደራጅቶ ማስፈታት የሚችል ሰው ነው ብዬ አምናለሁ ።

ማለትም ያ ሕዝብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት ችግርና ፍላጎቱ ምን እንደ ሆነ መሪውም ማወቅ አለበት፣ ሕዝቡም ማወቅ አለበት ። ያ ችግር ቢያንስ 4 መፍትሄዎች አሉት፤ (1) አንድ አዲስ የሌለ ነገር መፍጠርን ይጠይቅ ይሆናል። ስለዚህ ያ መሪ አዲስ ነገር የመፍጠር ክሪኤቲቭ ችሎታ ያለው መሆን አለበጥ (2) ያ ችግር አንድ አሁን ያለን ነገር ማሳደግ፣ ማበልጸግ (ዴቬኦፕ) ማድረግን ይጠይቅ ይሆናል። ስለዚህ ያ መሪ ሕዝቡ የሚፈልገውን እድገት የማየት፣ የማቀድ፣ የማቀናበርና የመምራት ችሎታ እንዲኖረው ያስፈልጋል። (3) ያ ችግር አንድ አሁን ያለን ነገር፣ ውርስ፣ ቅርስ፣ ሃብት፣ ባህል ፣ አገር እንዳለ መጠበቅ፣ መከላከል ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ያ መሪ ህዝቡን አስተባብሮ ህልውናቸውን፣ የኑሮ ዘይቤአቸውን የማስጠበቅ ፍላጎትም ችሎታም እንዲኖረ ያስፈልጋል። (4) ያ ችግር አንድ ወይም ብዙ አሁን ያሉ ነገሮችን መለወጥ፣ በሌላ ሲስተም መቀየር የሚጠይቅ ሊሆን ይችላል። ይህ የለውጥ ፍላጎት ዘገምተኛም ሆነ ስር ነቀል ማለት ነው ። ስለዚህ ያ መሪ እነዚህን ለውጦች አገርና ህዝብ አስተባብሮ መምራት የሚችል መሆን አለበት ። በቃ እነዚህ ናቸው ።

ከዚህ ተነስተህ አቢይን ለመመዘን ትችላለህ፤

አቢይ አዲስ ነገር የሚፈጥር መሪ አይደለም፣ እስካሁን በየነው ። አዲስ ሲስተም አዲስ ስርዓት የሚፈጥሩ መሪዎች ወይ አዲስ የሌለ ድርጅት የሚቆረቁሩ ወይም በስር ነቀል ለውጥ ቀድሞ ያልነበረ ማህበረሰብ የሚመሰርቱ ናቸው

አቢይ ልማታዊ ወይም ዴቬሎፕመንታል መሪ ነው ለማለት ቢቃጣንም የሚያሳድገው ወያኔዎች የጀመሩት የጎሳ ሲስተም ስለሆነ የባሰ ችግር እንጂ መፍትሄ አላመጣም። ይህ ትልቁ የብልጽግና ፓርቲና ያቢይ ርዕዮተ አለም ድክመትና ውድቀት ነው ። የሚለማው ምንድን ነው? ስለ እድገት ብዙ ይባላል፤ ግን የሚያድገው ምንድን ነው? የሚያድገው ወያኔ የተከለው ችግኝ ነው ። በቃ ይህ ነው ያቢይ መሰረታዊ የመሪነት ብቁ አለመሆን!

ቅርስ ስለመጠበቅ አቢይ ከትግሬዎቹ እጅግ በጣም የተሻለ ነው ።

የመጨረሻው የለውጥ መሪ የሚባለው ነው። አቢይ ትራንስፎርማቲቭ መሪ አይደለም። በ4 አመት ውስጥ አንድም የጎሳ ሲስተም ላይ በሰረታዊ ትራንስፎርሜሽን አላመጣም።

አቢይ እራሱን ዘገምተኛ የለውጥ መሪ ነኝ ብሎ ያምናል። በቅርቡ ሪፎርም መደረግ አለባቸው ብሎ ማህበረሰቡ የሚያምንባቸው ለትግሬ ትቅም ተብለው የተፈጠሩ ሲስተሞች በሄራዊ ምክክር ወቅት ምን እንዴት እንደ ሚለወጡ የምናየው ይሆናል ። እኔ መደመር የሚባለው የአቢይ ሃሳብ እንደ ለውጥ አላየውም፣ መሪነት ተግባር ነው። መሪነት ውጤት ነው ከላይ በ4 መድቤ እንዳሳየሁት ማለት ነው ። መደመር ሃሳብ ነው፣ ብቃ!
Last edited by Horus on 09 May 2022, 16:56, edited 1 time in total.

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Assegid S. » 09 May 2022, 15:46

ሰላም Horus; ለሰጠኽኝ መልስ በጣም አመሰግናለሁ

በእኔ እምነት ዶ/ር ኣብይ ሲበዛ ቸልተኛ መሪ ነው። ችግር በራሱ የለውጥ ኡደት (evolution) ወደ መፍትሔ ይሸጋገራል የሚል አስተሳሰብ አለው ብዬ አምናለሁ። አንጥረኛ በእሳት አግሎ፣ በመዶሻ ነድሎ እንደገና ቅርፅና መጠን ካልሰጠው በስተቀር በጊዜ ሂደት ብቻ ሲያረጅና ሲዝግ ልክ ጥይት ወደ ማንኪያ፣ ታንክም ወደ ትራክተር ይለወጣል ብሎ እንደማሰብ ማለት ነው። ብዙ ማለት ብፈልግም ለዛሬ ግን: ሰው በእምነቱ (በሀይማኖቱ) እራሱን እንጂ ህዝብ (ሀገር) አያኖርም፣ አያስተዳድርም ብዬ ላብቃ። ይህንንም ያልኩበት ምክን ያት ስላለኝ ነው።

ከዚህ ባለፈ ግን ... ከየሀገራቸው ህዝብ ፍላጎትና አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተህ በአንተ ሚዛን መሪ ነው የምትለውን ግለሰብ (ግለሰቦች) ግን አልነገርከንም። ምናልባት ... በዛ ደረጃ ልትቀበለው የወደድከው መሪ ስለሌለ ይሆን?

Stay safe, Horus.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 09 May 2022, 17:22

Assegid S. wrote:
09 May 2022, 15:46
ሰላም Horus; ለሰጠኽኝ መልስ በጣም አመሰግናለሁ

በእኔ እምነት ዶ/ር ኣብይ ሲበዛ ቸልተኛ መሪ ነው። ችግር በራሱ የለውጥ ኡደት (evolution) ወደ መፍትሔ ይሸጋገራል የሚል አስተሳሰብ አለው ብዬ አምናለሁ። አንጥረኛ በእሳት አግሎ፣ በመዶሻ ነድሎ እንደገና ቅርፅና መጠን ካልሰጠው በስተቀር በጊዜ ሂደት ብቻ ሲያረጅና ሲዝግ ልክ ጥይት ወደ ማንኪያ፣ ታንክም ወደ ትራክተር ይለወጣል ብሎ እንደማሰብ ማለት ነው። ብዙ ማለት ብፈልግም ለዛሬ ግን: ሰው በእምነቱ (በሀይማኖቱ) እራሱን እንጂ ህዝብ (ሀገር) አያኖርም፣ አያስተዳድርም ብዬ ላብቃ። ይህንንም ያልኩበት ምክን ያት ስላለኝ ነው።

ከዚህ ባለፈ ግን ... ከየሀገራቸው ህዝብ ፍላጎትና አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተህ በአንተ ሚዛን መሪ ነው የምትለውን ግለሰብ (ግለሰቦች) ግን አልነገርከንም። ምናልባት ... በዛ ደረጃ ልትቀበለው የወደድከው መሪ ስለሌለ ይሆን?

Stay safe, Horus.
ብረትን ቀጥቅጦ ማንኪያ የሚያደርገው መሪኮ ከላይ ለዋጭ ወይም ትራንስፎርማቲቭ ያልኩት ሰው ነው ። አቢይ ያ ሰው አለመሆኑ ባሁን ግዜ ማለት ነው ስምምነት ላይ ነን።

መሪነት ተግባር ከሆነ በተግባር ላይ ያለው መሪ አቢይ ነው ። በእሱ ላይ ያለኝ ሃሳብ ግልጫለሁ ። ከዚያ ውጭ ያለ መሪ ሃሳቡን በወረቀት ላይ የገለጸ ብቻ ነው ፣ ያ ደሞ ሃሳብ ስለሆነ ኢምፒሪካሊ ለመተቸት አይቻልም ።

እኔ የዜጋ ፖለቲካ ፊሎሶፊ ተከታይ ነኝ ። ስለሆነም አንድ የኢትዮጵያ መሪ ኢትዮጵያን በጎሳ አደራጅቶ ይመራል ወይም ይለውጣል ብዬ አላምንም ። አቢይን እንደ ግለሰብ ይነዱታል ብዬ የማምነው ሞቲቭ ዝና (ስኬታማ መሆን፣ መታወቅ) ነው ብዬ አምናለሁ ። ከላይ ባስቀምጥኳቸው 4 የውጤት አይነቶች ተመስርቼ አቢይ አዲስ ስርዓት የሚፈጥር መሪ አይደለም ብያለሁ። አሁን ያለውን ከወያኔ የተረከበውን የጎሳ ፌዴራሊዝም አሳድጋለሁ የሚል መሪ ነው ብዬአለሁ ። በእስቲዋርድነት ደረጃ አንዳንድ ብሄራዊ ቅርሶችን ለመጠበቅ ፈቃደኛ እንደ ሆነ ዋሳይቷል። በመጨረሻም አቢይ ለውጥ ፈጣሪ ወይም ትራንስፎርማቲቭ መሪ አይደለም ብዬ አምናለሁ።

ዞሮ ዞሮ የጎሳ ፍልስፍና የፖለቲካ ማህበረሰብ ማደራጃ ስላልሆነ መጨረሻው ውድቀት ነው ። ማለትም ማሰብ ያለብን ከጎሳ ውጭ ሆነን በመሆኑ አሁን ያለው ስርዐት ሳይለወጥ ስለመሪነት ብዙ ማለት ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ነው።

ስለሆነ አገር አቀፍ ምክክሩ ምን እንደ ሚል አይተን ሁሉንም እንደመድማለን ።

ethiopianunity
Member+
Posts: 9075
Joined: 30 Apr 2007, 17:38

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by ethiopianunity » 09 May 2022, 18:11

በጣም የሚያሳዝነው ለምንድን ነው ኣድዋ የተከበረዉ በድብቅ ይመስል አዳራኧ ውስጥ የተከበረው? ለምን እንደ አገር ነጻነት ባደባባይ ያልተከበረው ? የሀይማኖት ሲሆን ግን ለመከፋፈል የሚያሳይ በሽ ነው ለዚህም ነው ዛሬም ያገሪቱ መሪዎች አጠራጣሪ ነው

Assegid S.
Member
Posts: 936
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Assegid S. » 10 May 2022, 08:32

ሰላም Horus; በድጋሚ አመሰግናለሁ ለመልስህ።

የጋራ ምክክሩ መድረክ ምን ይፈጥራል የሚለውን ... አንተ እንዳልከው በሂደት እናየዋለን። ነገር ግን እኔ በምክክሩ ውጤታማነት ላይ ከወዲሁ reservation አለኝ። ምክንያቶቼ ሦስትና ኣራት ቢሆኑም ኣንዱን ብቻ ለመጥቀስ ያህል፦ በመድረኩ ላይ የሚቀርበው ሁሉ (ከሞላ ጎደል) ጆንያ ነው። ተሞልቶ የሚመጣው የሀሳብ ጥሬ … ቢቆላ፣ ቢቀቀል የማይበስል … ግፋ ቢል ግለሳባዊ አልያም የውጭ አካላት ፍላጎትና ጥያቄ ነው። እናም መድረኩ የሚበላ መ'ና ሳይሆን የሚሰጠን የሚያባላ መና (ከንቱ) እንደሚሆን አልጠራጠርም።

በነገራችን ላይ፦ ሰለሀገራዊ ምክክሩ መድረክ ስታነሳ … የድርድሩ ጠረፔዛ (The Negotiation Table) በሚል ርዕስ ትላንትና ማታ ስሰራው ከነበረው ኣንድ ቀላል ፕሮጀክት ጋር ተመሳሰለብኝ። ገና ያላለቀ ቢሆንም ... ከምክክሩ መድረክ ጋር ይመሳሰላልና ፖስት አድረጌዋለሁ። ምን ማስተላለፍ እንደፈለጉ የቤቱ ቁሳቁስና ብርሃን ቢዙ ሰለሚተርክ፥ እኔ በዚሁ ላብቃ።

መልካም ቀን Hours

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Ethoash » 10 May 2022, 09:18

እኔ ደግሞ የኢትዬዽያ ችግኝ መሪነት የሚል መስሎኝ

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 10 May 2022, 23:40

አሰግድ፣
እኔም ስለ ምክክሩ የራሴ መለኪያ አጀንዳ አለኝ ። ለምሳሌ ቢያንስ በአገር አቀፍ ክርክር ደረጃ (1) ሰንደቅ አላማ ስለመለወጥ፣ (2) ሕገ መንግስት ስለማሻሻል፣ (3) ስለ ክልሎች መብትና ድንበር ጉዳይ፣ (4) ጠንከር ካለ ፓርላሜንታሪ ስርዓት ወደ ፕሬዚዳንታዊ መለወት፣ እና (5) የክልል ጦር ሃይሎች ሁሉ በኢትዮጵያ ሰራዊት ስር ማድረግ የሚሉት ጉዳዮች ካልተነሱ ከንቱ ግዜ ማጥፋት ነው የሚሆነው ።

ነገር ግን ሁል ግዜ ነገርን ነገር ያነሳዋል። ሁል ግዜ አንድ ነገር ሲሆን ሌላ ያልተጠበቀ ነገር ይሆናል ። በዚህ መሰረታው እውነታ ምክንያት ምርርሩ ቢከሽፍ እንኳ ብዙ አሁን የሌሉ የሃይል አሰላለፎችና ህዝባዊ ንቃቶችን ይዞ ይመጣል ። ከውይይቱ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያጣው ነገር የለም ። እናያለን!

እስከዚያ የትግሬ ባንዳ የጩሀት ወራት ደርሷልና በዚያ ፈታ ዘና እያልን እንቆያለን !!

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 23 Jun 2022, 00:35

እዚህ ሃረግ መጀምሪያ ላይ ያለው ሃሳቤ የዛሬ 7 ሳምንት ሜይ 7 2022 ነበር የተናገርኩት! ቴዲ አፍሮ ምስክሬ ነው!!!!

Abdisa
Member+
Posts: 5732
Joined: 25 Apr 2010, 19:14

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Abdisa » 23 Jun 2022, 05:03

Had PM Abiy maintained his initial stance against the delivery of weapons to the TPLF terrorist group disguised as "humanitarian aid," the problems the country is facing today could have been easily averted, but he lacked the thick skin necessary to withstand Western media's nasty smear campaign, so he succumbed to his own ego and let loose a legion of demons from Tigray to wreck havoc all over the country. He should've finished off the TPLF when he had the backing of East Africa's military super power, and it's not too late to rectify the rookie mistakes he has made if he decides to change course.

Horus
Senior Member+
Posts: 30652
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: የኢትዮጵያ ችግር መሪነት ነው

Post by Horus » 23 Jun 2022, 13:01

Abdisa wrote:
23 Jun 2022, 05:03
Had PM Abiy maintained his initial stance against the delivery of weapons to the TPLF terrorist group disguised as "humanitarian aid," the problems the country is facing today could have been easily averted, but he lacked the thick skin necessary to withstand Western media's nasty smear campaign, so he succumbed to his own ego and let loose a legion of demons from Tigray to wreck havoc all over the country. He should've finished off the TPLF when he had the backing of East Africa's military super power, and it's not too late to rectify the rookie mistakes he has made if he decides to change course.
አው ያ ሁሉ የሚሆነው አቢይ ኢትዮጵያዊያንን ሰንደቅ አላማችሁን አታውለብልቡ ማለት ሲያቆምና ከ84 ጎሳዎች የተወለዱ ህጻናትን የኦሮሞ ጎሳ መዝሙር ዘምሩ ማለት ሲያቆም ነው ! እኔ ልሳሳት እችላለሁ፣ ነገሩ አሁን ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ ነው! የኢትዮጵያ ህዝብ ፎቶውን ይዞ ባገርና አለም ላይ ቆሞ እንደ መሪው በተከላከለው ማግስት ታሪካዊ ሰንደቁን ስለያዘ በኦሮሞ ፖሊስ የተገደለ ቀን ነው ያቢይ ማንነት ገሃድ የወጣው! ከዚህ በኋላ አቢይን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያስታርቀው ሚስቱን የጴንጤ መዝሙዝ ማዘፈን ሳይሆን ትግሬዎች ያቆሙት የጎሳ ሰርዓት እንዲፈርስ ሕዝቡን ማስነሳት ከቻለ/ከፈቀደ ብቻ ነው ።

Post Reply